በሆላንድ ሐዊረ ሕይወት ተካሔደ።

በሆላንድ ንዑስ ማእከል

መጋቢት 26 ቀን 2009 ዓ.ም

በማኅበረ ቅዱሳን አውሮፓ ማእከል የሆላንድ ንዑስ ማዕከል የመጀመሪያውን ሐዊረ ሕይወት በሆላንድ ሊቨልደ ግዛት በሚገኘው የግብፅ ኮፕት ቅዱስ ቴዎድሮስ ኦርቶዶክስ ገዳም መጋቢት ፱ ፳፻፱ ዓ.ም. አካሔደ።

ሐዊረ ሕይወቱ በአባቶች ጸሎት የተከፈተ ሲሆን በመቀጠልም የመጀመሪያ የሆነው የነገረ ክርስቶስ ትምህርት በመጋቤ ምስጢር ኅሩይ ኤርምያስ ተሰጥቷል። ከሰአት በኋላ ከተሳታፊዎች ለተነሱ መንፈሳዊ ጥያቄዎች በአባቶች በኩል መልስ ተመልሷል።ከዚያም በኋላ በዲ/ን መስፍን ኃይሌ ነገረ ቅዱሳን የሚመለከት ትምህርት ለጉባዔው ቀርቧል ።

“ማኅበረ ቅዱሳን እና አገልግሎቱ “ በተሰኘው ርዕስ ማኅበሩን የተመልከቱ ጉዳዮች በቀሲስ ዶ/ር ያብባል ሙሉአለም የአውሮፓ ማዕከል ሰብሳቢ ተገቢውን ማብራሪያ ተሰጥቶበታል።

በአጠቃላይ ወደ ፻ የሚጠጉ ምዕመናን ጉዞው ላይ የተሳተፉ ሲሆን በቀጣይ መርሀ ግብሩ ሰፋ ያለ ጊዜ ወስዶ ቢካሔድ መልካም መሆኑን አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።

በመጨረሻ በዚሁ ጉዞ በግብፅ ኮፕት ኦርቶዶክስ የኔዘርላንድና ቤልጄም ሊቀ ዻዻስ በብፁዕ አቡነ አርሲነ ቡራኬ የሐዊረ ፍኖቱ ማጠቃለያ ሆኗል ።

17359315_1375369232530017_9195612140934504521_o 17390778_1375370289196578_2626489877967785195_o 17358942_1375370049196602_1846207834315129326_o 17434496_1375370022529938_8981221075106631807_o 17358928_1375369782529962_5470858586464963287_o 17358924_1375369269196680_8966725266492399836_o