Entries by Alemnew Shiferaw

የዘመናት ለውጥ ለክርስቲያኖች የደወል ድምፅ ነው።

ጌታቸው በቀለ ዘመን ዘመን የሚለው ቃል አንድ ዓመትን ያመለክታል። በብዙ ሲሆን ዘመናት ይባላል። ይህም ከአንድ ዓመት በላይ የሆነ ጊዜን ለማሳየት ነው። በዘመን ውስጥ ዕለታት እና ወራት አሉ። አንድ ዓመት ማለት መሬት አንድ ጊዜ በፀሐይ ዙሪያ ለመዞር የሚፈጅባት ጊዜ ነው፡፡ ይህም 365 ከ1/4 (ሦስት መቶ ስድሳ አምስት ቀን ከሩብ) ዕለታት ይፈጃል፡፡ አሁን ባለንበት የዓለማችን ግንዛቤ ምድር […]

በሀገረ ጀርመን የካስል ደብረ ቀራንዮ መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን ቅዳሴ ቤት ተከበረ

ኅዳር 5 ቀን 2011 ዓ.ም በጀርመን ንዑስ ማዕከል በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በጀርመንና አካባቢው ሀገረ ስብከት የካስል ደብረ ቀራንዮ መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን ጥቅምት 24 እና 25 ቀን 2011 ዓ.ም. በሀገረ ስብከቱ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ዲዮናስዮስ ቡራኬ ቅዳሴ ቤቱ ተከበረ። ይህ የሕንጻ ቤተ ክርስቲያን በካህናት እና ምዕመናን ብርቱ ጥረት የተገዛ መሆኑ ታውቋል። በበዓሉም ላይ ተጋባዥ […]

በእንግሊዝ የ2ኛው ዙር ሐዊረ ህይወት ተካሄደ

በዩኬ ንዑስ ማዕከል በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤ/ማ/ መምሪያ ማኅበረ ቅዱሳን አዉሮፓ ማዕከል የዩናይትድ ኪንግደም ንዑስ ማዕከል ያዘጋጀው የ2ኛው ዙር ሐዊረ ሕይወት መርሐግብር ሰኔ 2 ቀን 2010 ዓ.ም. በታላቋ ብሪታንያ በነቲንግሃም ከተማ በቅድስት ልደታ ለማርያም ቤተክርስቲያን ተካሄደ። በጉባዔው ላይ ከተለያዩ የእንግሊዝ ከተሞች የተሰባሰቡ 50 ያህል ህፃናት እና ከ230 በላይ የሚሆኑ ካህናትና ምዕመናን ተሳትፈዋል። መርሐ ግብሩም በካህናት አባቶች […]

የቴክኖሎጂ ውጤቶች ና የሉላዊነት ጫና በልጆች አስተዳደግ

በላቸው ጨከነ ተስፋ (ዶ/ር) መግቢያ “ልጆች የእግዚአብሔር ስጦታ ናቸው። ” (መዝ፻፳፮፥፫)  ከእግዚአብሔር የተሰጡንን በረከት በሚገባው ተንከባክቦ፣ አስተምሮ  እና ጠብቆ ማሳደግ የወላጆች ትልቅ ሥራ ነው። ቅዱስ መጽሐፍ “እንግዲህ እነዚህን ቃሎች በልባችሁና በነፍሳችሁ አኑሩ። ልጆቻችሁንም አስተምሯቸው። በቤትህም ስትቀመጥ በመንገድም ስትሄድ ስትተኛም ስትነሳም አጫውቷቸው። እርሷንም እንዲሰጣቸው እግዚአብሔር ለአባቶቻችሁ በማለላቸው ምድር እንደ ሰማይ ዘመን በምድር ላይ ዘመናችሁ የልጆቻችሁም ዘመን […]

በፊንላንድ ለመጀመሪያ ጊዜ ሐዊረ ሕይወት ተካሄደ።

በማኅበረ ቅዱሳን አውሮጳ ማዕከል በፊንላንድ ግንኙነት ጣቢያ አስተባባሪነት የሐዊረ ሕይወት መርሐ ግብር ለመጀመሪያ ጊዜ በፊንላንድ ሄልሲንኪ ከተማ ውስጥ በሚገኘው የፊንላንድ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን የባህል ማዕከል እሑድ ግንቦት ፭ ቀን ፳፻፲ ዓ.ም  ተካሄደ።  በመርሐ ግብሩ ላይ የሄልሲንኪ ደብረ አሚን አቡነ ተክለ ሃይማኖት ቤተክርስቲያን ካህናትን እና ተጋባዥ መምህራንን ጨምሮ  የደብሩ ሰንበት ት/ቤት መዘምራን፣ ከሄልሲንኪ እና ከሌሎችም ከተሞች የመጡ […]

“መዝሙሮቻችን ከየት ወዴት” በሚል ርዕስ በመዝሙራት ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ መርሐ ግብር ተካሄደ

በእንግሊዝ ንዑስ ማዕከል ነሐሴ 5 ቀን 2008 ዓ.ም. በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ማኅበረ ቅዱሳን አውሮፓ ማዕከል የዩኬ (እንግሊዝ) ንዑስ ማዕከል “መዝሙሮቻችን ከየት ወዴት” በሚል ርእስ ሐምሌ ፳፬ ቀን ፳፻፰ ዓ.ም የኖቲንግሃምና የአቅራቢያ ከተሞች ካህናትና ምእመናን፣ የሰንበት ት/ቤት መዘምራንና የንዑስ ማእከሉ አባላት በተገኙበት በኖቲንግሃም ከተማ የግንዛቤ ማስጨበጫ መርሐ ግብር አካሄደ።

በማኅበረ ቅዱሳን አዉሮፓ ማዕከል የዩኬ(እንግሊዝ) ንዑስ ማዕከል አስተባባሪነት የተዘጋጀዉ ጉባዔ ተጠናቀቀ

በእንግሊዝ ንዑስ ማዕከል ሐምሌ 29 ቀን 2008 ዓ.ም. በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ ቤቶች ማ/ መምሪያ ማኅበረ ቅዱሳን አዉሮፓ ማዕከል የዩኬ (እንግሊዝ) ንዑስ ማዕከል ከሁለት አጥቢያ አቢያተ ክርስቲያናት ጋር በመተባበር አዘጋጅቶት የነበረዉ የስብከተ ወንጌል ጉባዔ በተሳካ ሁኔታ ተከናውኗል። ጉባዔው ሰኔ ፳፭ እና ፳፮ ቀን ፳፻፰ ዓ.ም በበርሚንግሃም ደ/መድኃኒት ቅዱስ አማኑኤል እንዲሁም ሐምሌ ፪ እና […]