Entries by tc

“ወይንሳዕ መስቀለ ሞቱ ወይትልወኒ – የሞቱን መስቀል ተሸክሞ ይከተለኝ”

በዲ/ን ዶ/ር ቴዎድሮስ በለጠ መስከረም 16 ቀን 2010 ዓ.ም. ለስም አጠራሩ ክብር ይግባውና በቃል መነገሩ፣ በኅሊና መዘከሩ፣ በሰው ልብ መታሰቡ፣ በቅዱሳት መጻሕፍት መዘገቡ ከፍ ይበልና፣ ጌታችንንና አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እኛ ልጆቹ ፈቃዱን እያደረግን እንድንኖርና እርሱም ከመልካም ምግባራችንና ከበጎ ትሩፋታችን ብቻ የተነሳ ፍጹማን እንደማንሆን ያውቃልና፣ ከማያልቅ ልግስናው ከማይጓደል ምሕረቱ ዘመናትን እየመጸወተን ደስ የሚሰኝበትን ለእኛ እያደረገ […]

ሆሣዕና

በኤርምያስ ልዑለቃል መጋቢት 30 ቀን 2009 ዓ.ም. ሆሣዕና ቃሉ የዕብራይስጥ ሲሆን ትርጉሙም አሁን አድን ማለት ነው። በቅድስት ቤተ ክርስቲያን ሥርዓት መሠረት የታላቁ ዓቢይ ጾም ስምንተኛ እሑድ የሆሣዕና በዓል በድምቀት የሚከበርበት ዕለት ነው። በዚህ ዕለት ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በታላቅ ትህትና በአህያ ጀርባ ተቀምጦ ወደ ኢየሩሳሌም ያደረገውን ጉዞ የሚዘክር ቃለ እግዚአብሔር በስፋት ይደርሳል። በአራቱም ወንጌላውያን በቅዱስ ማቴዎስ፣ ማርቆስ፣ ሉቃስ […]

ቅድስት

በዲያቆን መስፍን ኃይሌ የካቲት 18 ቀን 2009 ዓ.ም የቤተክርስትያናችንን መዝሙር ንባቡን ከዜማው አስማምቶ አጠናክሮ ያስተላለፈልን ኢትዮጵያዊው ሊቅ ቅዱስ ያሬድ በጾመ ድጓው በዓቢይ ጾም ለሚገኙትን እሑዶች ሁሉ የተለየ መዝሙር ስለሠራላቸው እያንዳንዱ እሑድ በመዝሙሩ ስም ይጠራል ። በዚህም መሰረት የዚህ ታላቅ ጾም ሁለተኛው እሑድ ቅድስት ተብሎ ተሰይሟል። ቅድስት የሚለው ቃል ግሱ“ቀደሰ” ሲሆን ለየ አከበረ መረጠ የሚል ትርጉም […]

‹‹መስቀል ለእለ ነአምን መድኅን›› ቅዱስ ያሬድ

በመጋቢ ሀዲስ ምስጢረ ስላሴ ማናዬ መስከረም 16 ቀን 2009 ዓ.ም. ‹‹መስቀል ለእለ ነአምን መድኅን – መስቀል ለምናምን መድኃኒት ነው››። ስለነገረ መስቀሉ ከተናገሩ ሊቃውንት የኢትዮጵያው ሊቅ ቅዱስ ያሬድ ትልቅ ድርሻ አለው። በአምስቱም ድርሰቶቹ በሰፊው ስለ መስቀል ዘምሯል፣ ተናግሯል፣ አመስጥሯል። ከላይ ያነሳነውን ኃይለ ቃል የተናገረውም እርሱ ነው። ምክንያቱም የቅዱስ ያሬድ ድርሰቶች ስለ ነገረ ድኅነነት ያጠነጥናሉ። እግዚአብሔር በነገረ […]

የአውሮፓ ማእከል ፲፮ኛ ጠቅላላ ጉባኤ ተካሔደ

በአውሮፓ ማእከል ኅትመትና ኤሌክትሮኒክስ ሚዲያ ክፍል ሐምሌ 15 ቀን 2008 ዓ.ም. በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ማኅበረ ቅዱሳን የአውሮፓ ማእከል ፲፮ኛ ጠቅላላ ጉባኤ ከሐምሌ ፩-፫ ቀን ፳፻፰ ዓ.ም በስዊድን አገር ስቶክሆልም ከተማ ተካሔደ። በጠቅላላ ጉባኤው በተለያዩ የአውሮፓ አገሮች የሚኖሩ ከሰባ በላይ የማእከሉ አባላት፤ የዋናው ማእከልና የሰሜን አሜሪካ ማእከል ተወካዮች፤ እንደዚሁም ጥሪ […]

በጀርመን ድሶልዶርፍ የጻድቁ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ቤተ ክርስቲያን ቅዳሴ ቤቱ ተከበረ።

በጀርመን ን/ማእከል ኅትመትና ኤሌክትሮኒክስ ሚዲያ ክፍል ግንቦት 24 ቀን 2008 ዓ.ም. በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን በደቡብ ምሥራቅ እና ምዕራብ አውሮፓ ሀገረ ስብከት በጀርመን ድሶልዶርፍ የጻድቁ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ቤተ ክርስቲያን በሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ በብፁዕ አቡነ ሙሴ ሚያዚያ 16 ቀን 2008 ዓ.ም. በእለተ ሆሳዕና ተባርኮ ቅዳሴ ቤቱ ተከበረ።

ሀገረ ስብከቱ የመጀመሪያውን “ዝክረ ቅዱስ ያሬድ“ መርሐግብር አካሄደ

በጀርመን ን/ማእከል ኅትመትና ኤሌክትሮኒክስ ሚዲያ ክፍል ግንቦት 20 ቀን 2008 ዓ.ም. በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን በደቡብ፣ ምሥራቅ እና ምዕራብ አውሮፓ ሀገረ ስብከት የቤተ ክርስቲያናችን የዜማ አባት የሆነውን ቅዱስ ያሬድን ሕይወቱን እና ሥራዎቹን የሚዘክር “ዝክረ ቅዱስ ያሬድ“ የተሰኘ መርሐግብር በጀርመን ካርልስሩኸ ምዕራፈ ቅዱሳን አቡነ ተክለ ሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን ከግንቦት 12-14 2008 ዓ.ም. በደማቅ ስነ ሥርዓት […]

ትንሣኤ

በዲ/ን ብሩክ አሸናፊ ሚያዚያ 23 ቀን 2008 ዓ.ም. የጌታችንና የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ትንሣኤ ሲነገር አብሮ የሚነሣው በዕለተ ዓርብ ስለኛ ብሎ የተቀበለው ሞቱ ነው። አባታችን አዳም እና እናታችን ሔዋን በፈጸሙት በደል ምክንያት የሞት ፍርድ ተፈርዶባቸው ሳለ በበደላቸው ንስሐ ገብተው አምላካችንን በመለመናቸው፥ እርሱም የሰው ፍቅር አገብሮት በዕለተ አርብ በመስቀል ላይ ሞቶ ሶስት መዓልት እና ሶስት ሌሊት በከርሰ […]

የጀርመን ንዑስ ማእከል 3ኛውን የሐዊረ ሕይወት መርሐ ግብር አካሔደ

በጀርመን ን/ማእከል ኅትመትና ኤሌክትሮኒክስ ሚዲያ ክፍል ሚያዚያ 17 ቀን 2008 ዓ.ም. በማኅበረ ቅዱሳን አውሮፓ ማእከል የጀርመን ንዑስ ማእከል 3ኛውን የሐዊረ ሕይወት መርሐ ግብር በጀርመን ክሮፍልባህ ከተማ በሚገኘው ቅዱስ እንጦስ የግብጽ ገዳም ከሚያዝያ 7- 9 ቀን 2008 ዓ.ም አካሔደ። ሚያዝያ 7 ቀን 2008 ዓ.ም የመርሐ ግብሩ የመጀመሪያ ቀን የካርስሩህ ምእራፈ ቅዱሳን አቡነ ተክለ ሃይማኖት እና የክሮንበርግ […]

ኒቆዲሞስ

፩ መግቢያ በኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሥርዓት መሠረት የእምነቱ ተከታዮች ሁሉ እንዲጾሟቸው መጀመሪያቸውና መጨረሻቸው ተቀምሮ ጊዜና ወቅት ተወስኖላቸው የተደነገጉ ሰባት የዐዋጅ አጽዋማት አሉ። እነዚህም አጽዋማት በሐዋርያት ሲጾሙ የቆዩና ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን በቀኖና መጻሕፍት የአጿጿም ሥርዓታቸውን የሠሩላቸው ናቸው። ከእነዚህም ሰባት አጽዋማት አንዱና ዋናዉ ዐቢይ ጾም ነው። ይህ ጾም ክብር ምሥጋና ይግባዉና ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከተጠመቀ […]