Entries by Website Team

ሆሣዕና (ለሕፃናት)

በቤካ ፋንታ 03.08.2012 በኢየሩሳሌም በምትገኝ በአንድ ትንሽ መንደር ውስጥ ነው የምኖረው፡፡ ከተወለድኩ አምስት ዓመት ሞልቶኛል፡፡ በዕለተ ሰንበት በቤት ውስጥ እየተጫወትሁ፣ እናቴም በጓዳ ሥራ እየሠራች ሳለን በድንገት የብዙ ሰዎች የዕልልታ ድምፅ በሰፈሩ ውስጥ ሰማን፡፡ እናቴም በፍጥነት ከጓዳ ሮጣ ወጥታ ‹‹ልጄ! ልጄ! ነይ እንሒድ!›› ብላ አዝላኝ እየሮጠች ከቤት ወጣች፡፡ በኹኔታው ተገርሜአለሁ፡፡ በሰፈር ውስጥ ያሉ ጓደኞቼ ዅሉ በእናቶቻቸው ጀርባና በአባቶቻቸው ትከሻ ላይ ኾነው […]

ግብረ-እስጢፋኖስ

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ማኅበረ ቅዱሳን የአውሮፓ ማዕከል ግብረ-እስጢፋኖስ የተሰኘ ልዩ የዲያቆናት መርሐ ግብር በመጋቢት 23 እና 24፣ 2012 ዓ.ም አዘጋጀ፡፡ በማዕከሉ ትምህርት ክፍል አስተባባሪነት የተካሄደው ይህ መርሐ ግብር በአውሮፓ የሚኖሩ ዲያቆናትን በአንድ ላይ በማሰባሰብ ዲያቆናት ከቤተ መቅደስ አገልግሎት ጀምሮ ምዕመናንን በስብከተ ወንጌል በማስተማር ወንጌልን ለማስፋፋት በሚደረገው ጥረት የላቀ […]

የኃዘን መግለጫ

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቶች ማ/መምሪያ ማኅበረ ቅዱሳን የአውሮፓ ማእከል: የታላቋ ብሪታኒያና የአየርላንድ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ ዕረፍት የተሰማንን ኃዘን እንገልጻን፡፡የብጹዕነታቸው በረከት ይድረሰን እያልን፡ በተለየ ሁኔታም ለአህጉረ ስብከቱ ሠራተኞች እንዲሁም ምእመናን የቤተ ክርስቲያን አምላክ መጽናናትን እንዲያድለን እንመኛለን፡፡ በማኅበረ ቅዱሳን የአውሮፓ ማእከል

በቱሉዝ ፈረንሳይ የቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ቅዳሴ ቤቱ ተከበረ፡፡

በቀሲስ አለባቸው በላይ ከፈረንሳይ ግንኙነት ጣቢያ   በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ን የኢጣልያና አካባቢው ሀ/ስብከት በደቡብ ፈረንሳይ ቱሉዝ ከተማ የቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን የሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ሕርያቆስ በተገኙበት ቅዳሴ ቤቱ ተከበረ፡፡ ወደ አጥቢያ ቤተክርስቲያንነት ከማደጉ በፊት ‘የቱሉዝና አካባቢው ቅዱስ ሚካኤል ማኅበር’ በሚል ስያሜ የቆየ ሲሆን፤ አመሠራረቱም በመስከረም ወር 2008 ዓ.ም አሁን ነዋሪነቱን በአሜሪካን ሀገር ያደረገ ዶ/ር ኢንጅነር ኃይሉ […]

በጀርመን ካስል ደብረ ቀራንዮ መድኃኔ ዓለም ቤተክርስትያን ዐውደ ርዕይ ተካሄደ

በጀርመን ንዑስ ማእከል በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ማኅበረ ቅዱሳን በአውሮፓ ማእከል የጀርመን ንዑስ ማእከል አዘጋጅነት “ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተክርስቲያንን አስተምህሮዋን እንጠንቅቅ፤ ድርሻችንን እንወቅ” በሚል መሪ ቃል የካቲት 22 ቀን 2012 ዓ.ም. በካስል ደብረ ቀራንዮ መድኃኔ ዓለም ቤተ ክርስቲያን ዐውደ ርዕይ ተካሄደ። ዐውደ ርዕዩን የካስል ደብረ ቀራንዮ መድኃኔ ዓለም እና የሐምቡርግ ደብረ […]

የቤተልሔም እንስሳት

ታኅሣሥ 2003 , ስምዐ ጽድቅ እንደምን ሰነበታችሁ ልጆች ልጆች ቤተልሔምን ታውቋታላችሁ?ቤተልሔም ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተወለደባት ከተማ ናት። እና ልጆች የቤተልሔም እንስሳት ጌታችን መወለዱን በሰሙ ጊዜ እጅግ ተደስተው “ምን ይዘን እንሂድ? ምንስ እናበርክት?”በማለት በሬዎች፥በጎች፥ጥጃዎች፥ህያዎችና ሌሎች እንስሳት ተሰብስበው መወያየት ጀመሩ። ፀሐይ ልጆቿን ጨረቃንና ከዋክብትን ጠርታ “ልጆቼ ሆይ ዛሬ ታላቅ ደስታ በኢየሩሳሌም ሀገር በቤተልሔም ከተማ ተፈጽሟል።የዓለም ፈጣሪ […]

“ስብሐት ለእግዚአብሔር በሰማያት ወሰላም በምድር ሥምረቱ ለሰብእ፤ በሰማያት ምስጋና ተደረገ በምድርም እርቅ ተወጠነ ‹‹ሰላም ሆነ፡፡›› (ሉቃ. ፪፥፲፬)

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን፡፡ እንኳን ለብርሃነ ልደቱ በሰላም አደረሳችሁ! ለአዳም የሰጠውን ተስፋ ሊፈጽም በነቢያት አድሮ ያናገረው ትንቢት ሲደርስ ሰው የሆነ አምላክ የተወለደበት ዕለት (የልደት በዓል) እነሆ ደረሰና እኛም በዓሉን አክብረን ከበረከተ ልደቱ እንድንሳተፍ አበቃን፡፡ አምላካችን ለእኛ ላደረገልንና ለሚያደርግልን የቸርነት ሥራው ሁሉ ከምስጋና በቀር ሌላ አቅም ኖሮን መክፈል የምንችለው ነገር የለንም፡፡ ምክንያቱም […]