ዜና

የሐዊረ ሕይወት መርሐ ግብር ከሀገረ ዴንማርክ(ኮፐንሃገን) ወደ ሀገረ ስዊድን (ሉንድ)

ከዴንማርክ ኮፐንሃገን ደብረ ምሕረት ቅዱስ አማኑኤል ቤተ ክርስቲያን በመነሳት ወደ ስዊድን፣ ሉንድ ደብረምጥማቅ ቅድስት ማርያም ቤተክርስቲያን ነሐሴ 16/2013 . (Aug.22/2021) የሐዊረ ሕይወት መርሐ ግብር ተካሄደ።

ሐዊረ ሕይወቱን ያዘጋጅው የዴንማርክ ግንኝነት ጣቢያ ከደ/// አማኑኤል እና ከሉንድ /// ማርያም /ሰበካ ጉባኤያት ጋር በመተባበር ነው። በዚህ መርሐ ግብር ላይ የሁለቱ አብያተ ክርስቲያናት ምእመናን እናበአጎራባች የሚገኙ አጥቢያዎች፣ አጠቃላይ 200 በላይ የሚሆኑ ምእመናን ተሳተፈዋል። የሁለቱም አጥቢያዎችአስተዳዳሪ መልአከ ምሕረት ቆሞስ አባ ዘሚካኤል ደሬሳ፥ መጋቤ ሃይማኖት ቀሲስ ኃይለ ማርያም አያሌው እናመልአከ መዊእ ቀሲስ ሃይለ ጊዮርጊስ አሰፋ ተገኝተው ቃለ እግዚአብሔር እና ምክር ሰጥተዋል።  

መርሐ ግብሩ እሐድ ጠዋት 06:00 ላይ ከኮፐሃገን ///አማኑኤል ቤተክርስቲያን በመነሳት ወደ ሉንድ /// ማርያም ቤተ ክርስቲያን ተደርጓል። በደብረ ምጥማቅም የኪዳን ጸሎት፥ የቅዳሴ ጸሎት በኋላ የሐዊረ ሕይወቱየመጀመሪያው ክፍል በጸሎተ ወንጌል ተጀምሮ በኮፐንሃገን የተስፋ ምሕረት //ቤት ዘማሪያን ያሬዳዊዝማሬያት እና የበገና መዝሙር አቅርበዋል።

ከዚያ በማስቀጠል በመልአከ ምሕረት ቆሞስ አባ ዘሚካኤልከመረጥኹት፣ጋራ ቃል ኪዳኔን አደረግኹ መዝ883″ በሚል ርእስ ትምህርተ ወንጌል ሰጥተዋል። በማያያዝም የደ/ምጥማቅ ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያንየአጥቢያው ምእመናን 30 ዓመታት በላይ ይጠቀሙበት የነበረውን ሕንጻ ኮንትራት፣ ለቀጣይ 100 ዓመታትመራዘሙን ምክንያት በማድረግ ሕንጻ ቤተ ክርስቲያኑን ለሰጡት የስዊድን ቤተክርስቲያን እና ላስተባበሩትየሰብካ ጉባኤ አባላት ምስጋና በማቅረብ ሊሠራ ስለታቀደው ደጀ ሰላም ገለጻ ተደርጓል፡፡ ደጀ ሰላሙ በአውሮፓያሉ ምእመናን በፍልሰታና በሌሎች ጊዜያት መጥተው ሱባኤ ሊይዙበት የሚችሉ በመሆኑ እቅዱ እንዲሳካየምእመናን ሁለንተናዊ ትብብር እንዲደረግለት ሰበካ ጉባኤው ጥሪውን አስተላልፏል።  


የሐዊረ
ሕይወት 2 ክፍል የሆነው ምክረ አበው  በመጋቢ ሃይማኖት ቀሲስ ሃይለ ማርያም እና በመልአከ መዊእቀሲስ ሃይለ ጊዮርጊስ አማካኝነት 2ሰዓት ያክል ተከናውኗል። በምክረ አበውም ምእመናን ጥሩ ግንዛቤአግኝተውበታል። በተጨማሪም  የተስፋ ምሕረት / ተማሪዎች የተለያዪ ሥነ ጹሑፎችን በኅብረት አቅርበዋል።

በመጨረሻም ሰለ ማኅበረ ቅዱሳን ማንነት፥ ሰለአመሠራረቱ እና ስለሚከናውናቸው መንፈሳዊ መርሐ ግብራትከተገለጸ በኋላ፣ ይህን ሐዊረ ሕይወት በማዘጋጀት ለተሳትፉ ባለድርሻ አካላት ሁሉ በእግዚአብሔር ስም ምስጋናበማቅረብ በደ/// ማርያም ቤተ ክርስቲያን አውደ ምሕረት ውስጥ የነበረው መርሐ ግብር ተጠናቋል፡፡ ሐዊረሕይወቱ የዴንማርክ /// አማኑኤል ቤተ ክርስቲያን አባላት ከሉንድ ///ማርያም ቤተክርስቲያን ወደኮፐንሃገን //ቅዱስ አማኑኤል ቤተ ክርስቲያን ባደረጉት በዝማሬ የታጀበ የመልስ ጉዞ ተፈጽሟል።

ወስብሐት ለእግዚአብሔር።

ግቢ ጉባኤ

ቨርችዋል ግቢ ጉባኤ በአውሮፖ በዚህ ይመዝገቡ:-
https://docs.google.com/forms/u/1/d/1kwZcBbi7PrnK1m-Iz6E8Njpdmy-sMURA8wf2pDWrR_k/viewform?edit_requested=true&pli=1 

በእንግሊዝ ሀገር የቨርችዋል ግቢ ጉባኤ ተማሪዎች ተመረቁ

ከዩኬ ንዑስ ማእከል 

ነሐሴ ፩ ቀን ፳፻፲፫ ዓ.ም

ተመራቂ የግቢ ጉባኤ ተማሪዎች (በከፊል) ከአባቶች ጋር

በማኅበረ ቅዱሳን አዉሮፓ ማእከል በዩናይትድ ኪንግደም ን/ማእከል አስተባባሪነት ላለፉት ሦስት ዓመታት ተከታታይ የቤተ ክርስቲያን ትምህርት ሲማሩ የነበሩ 11 የግቢ ጉባኤ ተማሪዎች ሐምሌ 24 ቀን 2013 ዓ/ም በአባቶች ቡራኬ ተመረቁ። በለንደን ደብረ ገነት ቅድስት ሥላሴ ቤተ ክርስቲያን አዳራሽ በተካሄደዉ በዚህ የተማሪዎች ምርቃት መርሐ ግብር ላይ ካህናት አባቶች፣ ተመራቂ ተማሪዎችና የተመራቂ ቤተሰቦች፣ ጥሪ የተደረገላቸዉ እንግዶች፣ የማኅበረ ቅዱሳን አባላት፣ ሌሎች የግቢ ጉባኤ እንዲሁም የሰ/ት/ቤት ተማሪዎች የተገኙ ሲሆን ሌሎች የአዉሮፓ ማእከል አባላት እና ታዳሚዎች መርሐ ግብሩን በዙም (Zoom) ተከታትለዋል። የአዉሮፓ ማእከል ሰብሳቢ ዲ/ን ፈንታ ጌቴ ለተመራቂዎች የ’እንኳን ደስ ያላችሁ’ መልእክት አስተላልፈዋል። በዚህም ተመራቂዎች ወደ ማኅበረ ቅዱሳን ተቀላቅለዉ የማኅበሩን አገልግሎት እንዲያግዙ ጥሪ አቅርበዋል።

ትምህርት በመልአከ ሰላም ቀሲስ አዲስ ሲሰጥ

በዚህ የምረቃ መርሐ ግብር ላይ፣ መልአከ ሰላም ቀሲስ አዲስ አበበ የለንደን ደብረ ገነት ቅድስት ሥላሴ ቤተ ክርስቲያን አገልጋይና የስብከተ ወንጌል ኃላፊ ትምህርት ሰጥተዋል። በተጨማሪም ተማራቂዎችና የፍሬ ሃይማኖት ሰ/ት/ቤት ተማሪዎች መዝሙር ያቀረቡ ሲሆን በግቢ ጉባኤ በመምህርነት ከሚያገለግሉት አባቶች መካከል መልአከ ሣህል ቀሲስ ዶ/ር ያብባል ሙሉዓለም እና ሊቀ ኅሩያን ቀሲስ ፍስሐ ለተመራቂዎች መልእክት አስተላልፈዋል።

 

ለተመራቂዎች የመስቀል ስጦታ በአባቶች ሲሰጥ

 

ለተመራቂዎች የመስቀል ስጦታ በአባቶች አማካኝነት ተበርክቷል። በን/ማእከሉ የተተኪ ትዉልድ እና ግቢ ጉባኤ ክፍል ተወካይ ለመርሐ ግብሩ ታዳሚዎች መልእክት ያስተላለፉ ሲሆን በዚህም ለግቢ ጉባኤዉ ስኬት አስተዋጽኦ ያደረጉትን መምህራንና ሌሎች አካላትን በሙሉ አመስግነዋል። ለምረቃ መርሐ ግብሩ የቤተ ክርስቲያኑን አዳራሽ ለፈቀደው የቤተ ክርስቲያኒቱ ሰበካ ጉባኤ ጽ/ቤት ምስጋናቸዉን አቅርበዋል።

የተተኪ ትዉልድ ንዑስ ክፍል ባለፈዉ ዓመት ዕድሜያቸዉ ሰባት ዓመት እና ከዚያ በላይ የሆኑ ከሦስት መቶ በላይ የሚደርሱ ህጻናትን፣ በየዕድሜያቸዉ ለይቶ የቤተ ክርስቲያንን ትምህርት በእንግሊዘኛ ቋንቋ ሲሰጥ መቆየቱን አስታዉሰዉ ትምህርቱን በተጠናከረ መልኩ ለማስቀጠል ምዝገባ እየተካሄደ መሆኑን ገልጸዋል። በግቢ ጉባኤ ንዑስ ክፍልም እንዲሁ አዳዲስ የአንደኛ ዓመት ተማሪዎችን ለመመዝገብ ዝግጅት ማጠናቀቁን ገልጸዉ ይህንን የምዝገባ መልእክት በማስተላለፍ ሁሉም አካላት እንዲተባበሩ ጠይቀዋል።

የ’ቨርችዋል’ ግቢ ጉባኤዉ በዩኬ በመጀመሩ ምክንያት የዘንድሮ ተመራቂዎች ሁሉም ከዩኬ ሲሆኑ፣ ከሁለት ዓመት በፊት ጀምሮ፣ ግቢ ጉባኤዉ በሌሎች የአዉሮፓ አገሮች ያሉ ተማሪዎችን ያካተተ በመሆኑ አሁን ላይ ወደ አዉሮፓ ግቢ ጉባኤነት ያደገ መሆኑን ገልጸዋል።

የግቢ ጉባኤ አንደኛ አመት ተማሪዎች ምዝገባ

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን።

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቶች ማ/መ/ ማኅበረ ቅዱሳን አውሮፓ ማእከል በዩኬ፣ በጀርመን እና በሌሎች የአዉሮፓ ሀገሮች በሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች እና ኮሌጆች የሚማሩ የቤተ ክርስቲያን ልጆችን የኢንተርኔት መገናኛዎችን በመጠቀም መሰረታዊ የቤተ ክርስቲያን ትምህርት በማስተማር ላይ የሚገኝ ሲሆን የመጪዉን የ2013 ዓ/ም ትምህርት ለመጀመር ዝግጅቱን አጠናቆ አዳዲስ የግቢ ጉባኤ ተማሪዎችን በመመዝገብ ላይ ይገኛል። በመሆኑም በዚህ የቨርቹዋል ግቢ ጉባኤ በመታቀፍ ለመማር የምትፈልጉ ኦርቶዶክሳውያን የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች የዚህ ዕድል ተጠቃሚ እንድትሆኑ እየጋበዝን ከዚህ በታች ያለዉን የጉጉል ፎርም ሊንክ በመክፈት እንድትመዘገቡ በእግዚአብሔር ስም እንጠይቃለን። https://docs.google.com/forms/d/e/1FAIpQLSdg2mI6K3033TDMnpqMMU0HqAVFywD4JrUC1W9rtnWdJX_UiQ/viewform

ሕጻናትን ማስተማር እንዴት እና ለምን?

ለሕጻናት መምህራን የተዘጋጀ ስልጠና :
https://us02web.zoom.us/j/86806058604

ከጀርመንና አካባቢው ሀገረ ስብከት የሕፃናትና የወጣቶች ክፍል

ጉዳዩ:- የህጻናት አስተማሪዎች ስልጠና Zoom-Meeting

መቼ: 1.Aug.2020 08:30 PM Paris

  • ወደ መርሐ ግብሩ ክፍል ውስጥ ለመግባት

Join Zoom-Meeting

ይህን መስፈንጠሪያ (Link) ይጠቀሙ

https://us02web.zoom.us/j/86806058604

ወይም የሚቀጥለውን ID በመስጠት ወደ መርሐ ግብሩ መግባት ይቻላል::

Meeting-ID: 868 0605 8604

One tap to join Audio:

ምናልባት በዙም አፕሊኬሽን በኢንተርኔት ከላይ በተጠቀሰው መረጃ መግባት ላስቸገራችሁ ለአማራጭ በቀጥታ ይህን ከታች ያለውን የነጻ የዙም ስልክ ቁጥር ደውለው በድምጽ ወደ መርሐ ግብሩ መግባት ይችላሉ:

Germany +49 69 3807 9883

Holland: +31 20 794 7345

Switherland: +41 44 529 92 72

Austria +43 72 011 5988

ግብረ-እስጢፋኖስ

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ማኅበረ ቅዱሳን የአውሮፓ ማዕከል ግብረ-እስጢፋኖስ የተሰኘ ልዩ የዲያቆናት መርሐ ግብር በመጋቢት 23 እና 24፣ 2012 ዓ.ም አዘጋጀ፡፡

በማዕከሉ ትምህርት ክፍል አስተባባሪነት የተካሄደው ይህ መርሐ ግብር በአውሮፓ የሚኖሩ ዲያቆናትን በአንድ ላይ በማሰባሰብ ዲያቆናት ከቤተ መቅደስ አገልግሎት ጀምሮ ምዕመናንን በስብከተ ወንጌል በማስተማር ወንጌልን ለማስፋፋት በሚደረገው ጥረት የላቀ ሚና እንዲኖራቸው ለማደረግ ያለመ ነበር፡፡ በመርሐ ግብሩም የኢጣልያንና አካባቢው ሀ/ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብጹዕ አቡነ ሕርያቆስ ለዲያቆናት ትምህርት፣ ተግሳጽ፣ ቡራኬ፣ እና ቃለ ምዕዳን የሰጡ ሲሆን ካህናት አባቶች መነኮሳት እና በተለያዩ የአውሮፓ ሀገራት የሚገኙ ከ 40 በላይ የሚሆኑ ወንድሞች ዲያቆናት ተሳትፈዋል፡፡ ለሁለት ቀን የተካሄደው ይህ ልዩ የዲያቆናት መርሐ ግብር የሰማዕቱ ቅዱስ እስጢፋኖስን ታሪክ፣ አገልግሎት በመዘከር እና ከሰማዕቱ እኛ ምን እንማራለን? የሚለውን ነጥብ ለተሳታፊዎች በማስገንዘብ ተጀምሯል፡፡ የክህነትን ሥርዓት እና ክብር በተመለከተ ትምህርት፣ ምክር በብጹዕ አቡ ሕርያቆስ የተሰጠ ሲሆን በቀሲስ ሰሙ ምትኩ (ዶ/ር) አማካኝነት ደግሞ ሰፊ የክህነት ምንነት የግንዛቤ ማብራሪያ በማድረግ የመጀመሪያ ቀን መርሐ ግበር ተጠናቋል፡፡

  

በሁለተኛው ቀን በነበረው ቆይታም የስብከተ ወንጌልን ትርጉም እና አስፈላጊነት፣ ስብከተ ወንጌል እንዴት መቼ እና የት? መካሄድ አለበት የሚለውን በተመለከተ በመልአከ ሳህል ቀሲስ ያብባል ሙሉዓለም (ዶ/ር) አማካኝነት ስልጠና ተሰጥቷል፡፡ በተጨማሪም ዲያቆናት በስብከተ ወንጌል አገልግሎት እንዳይሳተፉ የሚያደርጉ ችግሮችን ለመለየት በተሳታፊዎች መካካል ውይይት የተደረገ ሲሆን፦ በቂ የሆነ የመንፈሳዊ ዕውቀት አለመኖር፣ እራስን መደበቅ፣ ያልተገባ ፍርሃት፣ ስብከተ ወንጌልን መሠረት ያደረጉ የስልጠና ማዕከላትም ሆነ የመንፈሳዊ ኮሌጆች አለመኖር፣ እንዲሁም በአብነት ትምህርት ቤቶች ስብከተ ወንጌልን መሠረት ያደረገ የትምህርት እና የስልጠና ሥርዓት አለመኖሩ ከአብነት ትመህርቱ ጎን ለጎን የስብከተ ወንጌል ዲያቆናት ክህሎታቸውን እንዳያዳብሩ ያደረጓቸው ዐበይት ችግሮች መሆናቸው ተጠቅሷል፡፡ 

በመጨረሻም ወንድሞች ዲያቆናት እነዚህን ችግሮች ተቋቁመው በክህነት አገልግሎት ኃለፊነታቸውን እንዲወጡ ታታሪዎች፣ አንባቢዎች እና ሁሌም በጸሎት የሚተጉ መሆን እንደሚገባቸው መልአከ ምሕረት አባ ዘሚካኤል ደሬሳ ምክራቸውን እና ተሞክሯቸውን በማካፈል እንዲህ አይነቱ መርሐ ግብር ወደፊት በሰፊ ሁኔታ መተግበር እንዳለበት በማሳሰብ ስልጠናው በጸሎት ተፈጽሟል፡፡

ወስብሐት ለእግዚአብሔር ወለወላዲቱ ድንግል ወለመስቀሉ ክቡር።

አሜን፡፡

ትምህርትና ሐዋርያዊ አገልግሎት ክፍል

የኃዘን መግለጫ

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቶች ማ/መምሪያ ማኅበረ ቅዱሳን የአውሮፓ ማእከል: የታላቋ ብሪታኒያና የአየርላንድ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ ዕረፍት የተሰማንን ኃዘን እንገልጻን፡፡
የብጹዕነታቸው በረከት ይድረሰን እያልን፡ በተለየ ሁኔታም ለአህጉረ ስብከቱ ሠራተኞች እንዲሁም ምእመናን የቤተ ክርስቲያን አምላክ መጽናናትን እንዲያድለን እንመኛለን፡፡

በማኅበረ ቅዱሳን የአውሮፓ ማእከል

ገዳማትን እና የአብነት ት/ቤቶች ከኮሮና ወረርሽኝ ለመከላከል የሚደረገውን እንቅስቃሴ ይደግፉ

በዚህ ሊንክ መጠቀም ይችላሉ : ገዳማትን እና የአብነት ት/ቤቶች ከኮሮና ወረርሽኝ ለመከላከል የሚደረገውን እንቅስቃሴ ይደግፉ

በቱሉዝ ፈረንሳይ የቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ቅዳሴ ቤቱ ተከበረ፡፡

በቀሲስ አለባቸው በላይ ከፈረንሳይ ግንኙነት ጣቢያ  

በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ን የኢጣልያና አካባቢው ሀ/ስብከት በደቡብ ፈረንሳይ ቱሉዝ ከተማ የቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን የሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ሕርያቆስ በተገኙበት ቅዳሴ ቤቱ ተከበረ፡፡ ወደ አጥቢያ ቤተክርስቲያንነት ከማደጉ በፊት ‘የቱሉዝና አካባቢው ቅዱስ ሚካኤል ማኅበር’ በሚል ስያሜ የቆየ ሲሆን፤ አመሠራረቱም በመስከረም ወር 2008 ዓ.ም አሁን ነዋሪነቱን በአሜሪካን ሀገር ያደረገ ዶ/ር ኢንጅነር ኃይሉ በላይ የሚባል የቤተ ክርስቲያን አገልጋይ ለወራት ሥልጠና ወደ ከተማዋ በመጣበት አጋጣሚ ኢትዮጵያዊያንን ፈልጎ በማግኘትና በማስተባበር ነበር፡፡ ከ2 ወራት በኋላ ኅዳር ወር 2008 ዓ.ም ከፓሪስ መልአከ ጽዮን ቆሞስ አባ ወልደ ትንሳኤን በማምጣት የመጀመሪያው የቅዳሴ አገልግሎት ተከናውኗል፡፡ በተጨማሪም ክፍላትን በማዋቀር ማኅበሩ ቅርፅ እንዲኖረው የተደረገ ሲሆን፤ ከማኅበረ ቅዱሳን የፈረንሳይ ግንኙነት ጣቢያ ጋር በመተባበር ለአገልጋዮችም ተከታታይ ሥልጠናዎችን በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች በመስጠት አቅም የማጎልበት ሥራዎች ተሠርተዋል፡፡ ላለፉት አራት ዓመታት በየወሩ የቅዳሴ አገለግሎት በማከናወን፣ ሕጻናትን ክርስትና በማንሳት፣ ብዙ ምእመናን የምስጢራት ተካፋይ እንዲሆኑ ተደርጓል፡፡ አስፈላጊ የሆኑ መረጃዎችን ለሀ/ስብከቱ በማሳየት በብፁዕ አቡነ ሕርያቆስ መልካም ፈቃድ በቀን 15/06/2012 ዓ.ም የቅዱስ ሚካኤል ጽላት ገብቶ ማኅበሩ ወደ ቤተ ክርስቲያነት አድጓል፡፡  

C:\Users\User\Desktop\Mk France\Toulouse MMI\2020\87499442_679588912812286_2812710353425661952_n.jpg

በበዓሉ ዋዜማ ብዙ ቁጥር ያላቸው ምእመናን እና ካህናት ለሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ሕርያቆስ በቱሉዝ (Blagnac) ኤርፖርት ተገኝተው ደማቅ አቀባበል አድርገውላቸዋል፡፡ በብክብረ በዓሉ የማኅሌት፣ የትምህርትና እንዲሁም የቅዳሴ አገልግሎት በሊቀ ጳጳሱ መሪነት ተከናውኗል፡፡ ከቅዳሴ በኋላ ብፁዕ አቡነ ሕርያቆስ “አስቀድማችሁ መንግስቱንና ጽድቁን ፈልጉ” (ማቴ6፡33) በሚል ርዕስ መነሻነት በሰጡት ሰፋ ያለ ትምህርት፤ የምእመናኑን መጠናከርና እዚህ ደረጃ መድረስ በማውሳት በቀጣይም ለበለጠእ የጽድቅ ሥራ መበርታት እንዳለባቸው አሳስበዋል፡፡ በመጨረሻም ተተኪን ከማፍራት እና የተደራጀ አገልግሎት ከመፈጸም አንጻር በኖርዌይ እሳቸው በበላይ ጠባቂነት የሚመሩትን ደብር ተሞክሮ አነስተው፤ ተተኪ ካህናትን ማፍራት ላይ ትኩረት ሰጥቶ መስራት እንደሚገባ አባታዊ መመሪያ ሰጥተዋል፡፡ በመጨረሻም በብፁዕነታቸው ጸሎተ ምዕዳን የበዓሉ ፍጻሜ ሆኗል፡፡ 

C:\Users\User\Desktop\Mk France\Toulouse MMI\2020\87570752_199724234680697_4328006035571736576_n.jpg


ወስብሐት ለእግዚአብሔር፡፡

በጀርመን ካስል ደብረ ቀራንዮ መድኃኔ ዓለም ቤተክርስትያን ዐውደ ርዕይ ተካሄደ

በጀርመን ንዑስ ማእከል

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ማኅበረ ቅዱሳን በአውሮፓ ማእከል የጀርመን ንዑስ ማእከል አዘጋጅነት “ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተክርስቲያንን አስተምህሮዋን እንጠንቅቅ፤ ድርሻችንን እንወቅ” በሚል መሪ ቃል የካቲት 22 ቀን 2012 ዓ.ም. በካስል ደብረ ቀራንዮ መድኃኔ ዓለም ቤተ ክርስቲያን ዐውደ ርዕይ ተካሄደ።

ዐውደ ርዕዩን የካስል ደብረ ቀራንዮ መድኃኔ ዓለም እና የሐምቡርግ ደብረ መድኃኒት ኪዳነ ምሕረት ቤተ ክርስትያን አስተዳዳሪ መጋቤ ምሥጢር ኅሩይ ኤርምያስ (ዶ/ር) በጸሎት የከፈቱት ሲሆን፤ ከ50 በላይ ምዕመናን ተመልክተውታል። ዐውደ ርእዩ በዋናነትም በአራት ክፍሎች የተደራጀ ሲሆን ስለ ቤተክርስቲያናችን መሠረተ እምነት፣ ስለ ሐዋርያዊ አገልግሎት ምንነትና እና የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን የሐዋርያዊ አገልግሎት ጉዞ፣ በዓለምና በኢትዮጵያ በተለያዩ ክፍላተ ዘመን ስለነበረው የቤተ ክርስቲያን ተጋድሎ፣ እና ወቅታዊው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ተጋድሎ (በተለይም ከአክራሪ እስልምና ች እና ከፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ ጋር ያለው ተጋድሎ) በድምጽ ወምስል የታገዘ ገለጻ በዝርዝር ቀርቧል፡፡ 

የጀርመን ንዑስ ማዕከልም ለዝግጅቱ መሳካት ከጅማሬ እስከ ፍጻሜ ከፍተኛ ትብብር ያደረጉትን የደብሩን አስተዳዳሪ እና ሰበካ ጉባኤ፣ በዐውደ ርእዩ ላይ በገላጭነት የተሳተፉትን የደብሩን ሰንበት ትምህርት ቤት አባላት፣ ለዝግጅቱ መሳካት በተለያየ መልኩ እገዛ ያደረጉትን ምዕመናን በሙሉ አመስግኖ ይህ ቀና ትብብር ለወደፊትም እንደማይለየው ያለውን ጽኑ እምነት ገልጿል። 

በመጨረሻም መጋቤ ምሥጢር ዶ/ር ኅሩይ ኤርምያስ ከምንጊዜውም በላይ ለቤተክርስቲያን ህልውና በጋራ የምንቆምበት ጊዜ በመሆኑ ቅድስት ቤተ ክርስቲያንን ለመደገፍ ሁላችንም የበኩላችንን አስተዋጽዖ ልናደርግ እንደሚገባ አሳስበዋል። በተጨማሪም ደብሩ በአሁኑ ወቅት ያለበትን የሕንጻ ቤተክርስትያን ግዢ ዕዳ እንዳጠናቀቀ ማኅበረ ቅዱሳን በኢትዮጵያ የተለያዩ አካባቢዎች የሚያደርገውን የገዳማት እና የአብነት ት/ቤቶችን ልማት እንቅስቃሴ በተለያዩ መንገዶች እንደሚደግፍ ቃል በመግባት መርሐ ግብሩን በጸሎት ዘግተዋል፡፡