የጀርመን ንዑስ ማእከል 3ኛውን የሐዊረ ሕይወት መርሐ ግብር አካሔደ

በጀርመን ን/ማእከል ኅትመትና ኤሌክትሮኒክስ ሚዲያ ክፍል

ሚያዚያ 17 ቀን 2008 ..

germany-3-hhበማኅበረ ቅዱሳን አውሮፓ ማእከል የጀርመን ንዑስ ማእከል 3ኛውን የሐዊረ ሕይወት መርሐ ግብር በጀርመን ክሮፍልባህ ከተማ በሚገኘው ቅዱስ እንጦስ


የግብጽ ገዳም ከሚያዝያ 7- 9 ቀን 2008 ዓ.ም አካሔደ።

ሚያዝያ 7 ቀን 2008 ዓ.ም የመርሐ ግብሩ የመጀመሪያ ቀን የካርስሩህ ምእራፈ ቅዱሳን አቡነ ተክለ ሃይማኖት እና የክሮንበርግ ቅዱስ ዑራኤል ቤተ ክርስቲያን አስተዳዳሪ በሆኑት በመልአከ ስብሐት ተክሌ ሲራክ የመክፈቻ ጸሎት የተጀመረ ሲሆን፣ በጀርመን ንዑስ ማእከል ሰብሳቢ አቶ ወርቁ ዘውዴ የእንኳን ደህና መጣችሁ መልእክት ተላልፏል፡፡ በመቀተልም የወንጌል ትምህርት በዲ/ን ሄኖክ ኃይሌ ተሰጥቷል፡፡

በቀጣዩም ቀን ከቅዳሴ አገልግሎት በኋላ የዕለቱ መርሐ ግብራት በተያዘላቸው ጊዜ መሠረት ተካሂደዋል። በጠዋቱ መርሐ ግብር የመጀመሪያው የትምህርት ክፍል መልአከ ስብሐት ተክሌ ሲራክ ሰለ ዓብይ ጾም ሥርዓተ ማኅሌት በገለጻ እና በዜማ ለተሳታፊው አሰምተዋል፡፡

“€የተሐድሶ መናፍቃን ዋና ዋና ስሕተቶች እና የኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አስተምህሮ€” በሚል ርእስ በዲ/ን ሄኖክ ኃይሌ ትምህርት ተሰጥቷል፡፡ በዚህም ተሐድሶዎች ስለሚያነሱዋቸው ጥያቄዎች በተለይም ስለመዳን፣ ስለ ቅዱሳት ሥዕላት፣ ታቦት እና ስግደት በተመለከተ ሰፊ ትምህርት ተሰጥቷል፡፡ ከሰዓት በኋላ በነበረው መርሐ ግብር ማኅበረ ቅዱሳን በጠረፋማና ስብከተ ወንጌል ባልተስፋፋባቸው አህጉረ ስብከት እያከናወነ ስላለው የስብከተ ወንጌል ማስፋፊያ መርሐ ግብር በቪድዮ የተደገፈ ማብራሪያ ቀርቧል የትምህርት መርሐ ግብሩ ከሰዓት በኋላም ቀጥሎ በዲ/ን ዶ/ር ቴዎድሮስ በለጠ €œፈተና፣ ምንጩ እና መውጫዎቹ €œ” በሚል ርዕስ ሰፊ ትምህርት ተሰጥቷል።

ምሽት ላይ በነበረው መርሐ ግብርም በዲ/ን ሄኖክ ኃይሌ እነሆኝ የጌታ ባሪያ እንደ ቃልህ ይሁንልኝ” በሚል ርእስ የወንጌል ትምህርት ከተሰጠ በኋላ ከምእመናን ለቀረቡ ጥያቄዎች ዲ/ን ዶ/ር ቴዎድሮስ በለጠ እና በዲ/ን ሄኖክ ኃይሌ ምላሽ ሰጥተዋል።

germany-3-hh-2

 ቅዳሜ ጠዋት በቅዳሴ ተጀምሮ እስከ እኩለ ሌሊት በዘለቀው መርሐ ግብር ከላይ ከተጠቀሱት መርሐ ግብራት በተጨማሪም የገዳሙ አበምኔት እና በግብጽ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን የደቡብ ጀርመን ሊቀ ጳጳስ የሆኑት ብፁዕ አቡነ ሚካኤል በጉባኤው ላይ ተገኝተው ቡራኬ ሰጥተዋል፣ በጀርመን ንዑስ ማእከል ዘማርያን ያሬዳዊ ዝማሬዎችም ቀርበዋል።

በመጨረሻም ስለነበረው አጠቃላይ ዝግጅት እና ወደፊት መሻሻል ስለሚገባቸው ጉዳዮች ከተሳታፊዎች አስተያየት ተሰጥቶ በንዑስ ማእከሉ ሰብሳቢ አቶ ወርቁ ዘውዴ ለዝግጅቱ መሳካት አስተዋጽኦ ላደረጉ አካላት ምሥጋና በማቅረብ የቅዳሜው መርሐ ግብር ፍፃሜ አግኝቷል።

እሁድ ጠዋት ከግብጻውያን አባቶች እና ምእመናን ጋር በቅዳሴ በመሳተፍ ከምሳ ሰዓት በኋላ በተጠናቀቀው የሐዊረ ሕይወት መርሐ ግብር ላይ ከተለያዩ የጀርመን ከተሞች፣ እንዲሁም ከጣሊያን፣ ከሆላንድና ከስዊዘርላንድ የመጡ ከ220 በላይ ተሳታፊዎች ተገኝተዋል ከጉዞው ተሳታፊዎች ለማኅበረ ቅዱሳን የስብከተ ወንጌል ማስፋፊያ መርሀ ግብር እና ለቅዱስ እንጦንስ ገዳም የገንዘብ ድጋፍ ተደርጓል

የጀርመን ንዑስ ማእከል የሐዊረ ሕይወት መርሐ ግብርን ሲያካሒድ ለሦስተኛ ጊዜ ሲሆን ከአሁን በፊት የመጀመሪያው እና ሁለተኛውን መርሐ ግብራት በ2006 ዓ.ም እና 2007 ዓ.ም በተመሳሳይ ቦታ ማካሔዱ ይታወሳል