የአውሮፓ ማዕከል አዲስ ድረ ገጽ ለቀቀ

በማኅበረ ቅዱሳን ከሀገር ውጪ ከሚገኙት ማእከላት አንዱ የሆነው የአውሮፓ ማእከል ትምህርተ ሃይማኖትን የሚያስተላልፍበት እና አገልግሎቶቹን የሚያስተዋውቅበት አዲስ ድረ-ገጽ ለቀቀ።

የማዕከሉ ዓላማ በዚህ ድረ ገጽ ከአውሮፓ ነባራዊ ሁኔታ አንጻር ለምእመናን ይበልጥ የሚያስፈልጉ ትምህርቶችን እና የቤተ ክርስቲያን መረጃዎችን በሰፊው አጠናቅሮ ለአንባብያን በቀላሉ ማቅረብ ሲሆን ለአሁኑ ግን መጠነኛ ቁጥር ያላቸውን ትምህርቶች እና የማዕከሉን አጠቃላይ እንቅስቃሴ የሚያስረዱ ጽሑፎችን አቅርቧል።

በድረ-ገጹ ላይ ቢወጡ ሊያስተምሩ ይችላሉ የምትሏቸውን ጽሁፎች እንዲሁም አጠቃላይ አስተያየቶች ትልኩልን ዘንድ በትህትና እንጋብዛለን።

አነሳስቶ ያስጀመረን የቅዱሳን አምላከ ተግቶ ቃሉን ለማስተላለፍ እንችል ዘንድ ኃይልና ብርታቱን እንዲሰጠን ዘወትር በጸሎታችሁ አስቡን።