• እንኳን በደኅና መጡ !

የጣሊያን ንዑስ ማእከል አውደ ርእይ አካሄደ

በጣሊያን ንዑስ ማእከል ሰኔ 25 ቀን 2009 ዓ.ም. ማኅበረ ቅዱሳን የጣሊያን ንዑስ ማእከል ግንቦት ፲፱ እና ፳ ፳፻፱ ዓ/ም ከሮም ደብረ ጽዮን ቅድስት ማርያም እና ቅዱስ ኡራኤል ቤተክርስቲያን ጋር በመተባበር “ አብረን እንስራ ለውጥም እናመጣለን!” በሚል መሪ ቃል ዐውደ ርእይ አካሄደ። ዐውደ ርእዩ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በሕገ ልቡና በሕገ ኦሪትና በሕገ ወንጌል ያደረገችው ጉዞ፣ የገዳማትና አብነት […]

በኖርዌይ ንዑስ ማእከል የመጀመሪያው ሐዊረ ሕይወት ተካሄደ

በኖርዌይ ንዑስ ማእከል ሰኔ 20 ቀን 2009 ዓ.ም. በማኅበረ ቅዱሳን አውሮፓ ማእከል፣ የኖርዌይ ንዑስ ማእከል ከክርስቲያንሳንድ ቅድስት ማርያም ቤተክርስቲያን ጋር በመተባበር በሀገረ ኖርዌይ የመጀመሪያውን የሐዊረ ሕይወት መርሐ ግብር በክርስቲያንሳንድ ከተማ መጋቢት ፳፫ እና ፳፬  ቀን ፳፻፱ ዓ.ም አካሔደ። በሐዊረ ሕይወቱ ላይ ከክርስቲያንሳንድ ከተማ እና በአቅራቢያው ከሚገኙ ሌሎች ከተሞች የተሰባሰቡ ቁጥራቸው ከ40 እስከ 50 የሚደርሱ ምእመናን ተሳትፈዋል።

የጀርመን ንዑስ ማእከል አራተኛውን የሐዊረ ሕይወት አካሄደ

በጀርመን ንዑስ ማእከል ሰኔ 20 ቀን 2009 ዓ.ም. የጀርመን ንኡስ ማእከል ከመጋቢት ፲፯ እስከ መጋቢት ፲፱ ቀን ፳፻፱ ዓ.ም አራተኛውን የሐዊረ ሕይወት መርሐ ግብር በጀርመን የግብፅ አቡነ እንጦንስ ገዳም አካሄደ፡፡ በዚህ ሐዊረ ሕይወት ከጀርመን እና ከሌሎች አውሮፓ ሀገራት የተውጣጡ ካህናት፣ ዲያቆናት እና ምዕመናን የተሳተፉ ሲሆን በጠቅላላ የተጓዦች ብዛት 250 ነበር።  የጕዞ መነሻውን መጋቢት ፲፯ ከቀኑ 11 ሰዓት ከፍራንክፈርት […]

የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ ክርስቲያን መዝሙራት ከየት ወዴት በሚል ለሦስተኛ ጊዜ የተዘጋጀ የግንዛቤ ማስጨበጫ መርሐግብር በእንግሊዝ ለንደን ከተማ ተካሄደ።

በእንግሊዝ ንዑስ ማእከል ሰኔ 16 ቀን 2009 ዓ.ም. በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ ክርስቲያን ስም የሚወጡ መዝሙራት ቁጥር እየተበራከቱ ቢሄዱም በተለይ በቅርብ ጊዜ የወጡ አንዳንድ መዝሙራት ግን ከያሬዳዊ ዜማ ይልቅ ለዓለማዊ ዘፈን ያደሉ መሆናቸዉን ተከትሎ ማኅበረ ቅዱሳን ባካሄደዉ ጥናት እየታዩ ያሉትን ችግሮችና የመፍትሔ ሐሳቦችን በመረጃ በማስደገፍ አቅርቦ ነበር። የዚህ ጥናት ዉጤት በተለያዩ የሀገር ዉስጥና የዉጭ ሀገራት ጉባኤያት ላይ የቀረቡ ሲሆን በማኅበረ […]

ጰራቅሊጦስ

በቀሲስ ኃይለኢየሱስ ተመስገን ግንቦት 26 ቀን 2009 ዓ.ም. በቅዳሴ ጸሎት ካህናት ከሚጸልዩት ጸሎት ውስጥ “ወቡሩክ መንፈስ ቅዱስ ጰራቅሊጦስ መጽንዒ ወመንጽሔ ኩልነ” የሚል እናገኛለን ሁላችንን የሚያነጻ፣ የሚያጸና መንፈስ ቅዱስም ቡሩክ ነው ማለት ነው። በዚህ ጸሎት ላይ ጰራቅሊጦስ የሚለው ቃል ከሦስቱ አካላት አንዱ ለኾነው ለእግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ መጠሪያ እንደሆነና የሚያነጻ፣ የሚያጸና መሆኑን ይገልጣል።


ይህን በመጫን ይለግሱ

የቤተ ክርስቲያንን አገልግሎት ይደግፉ!



የስብከተ ወንጌል ማስፋፊያ  


ገዳማትና አብነት ት/ቤቶች 


የቴሌቪዥን እና ራዲዮ አገልግሎት 

ማስታወቂያ

Nothing Found

Sorry, no posts matched your criteria

©2019. Mahibere Kidusan Europe Center - All Rights Reserved. Website by MK-IT