ገዳማት እና የአብነት ትምህርት ቤቶችን ይርዱ።

በቀጥታ በኦንላይን በፔይፓል ወይንም በክሬዲት ካርድ እርዳታዎን ለመለገስ ከታች ያለውን Donate የሚለውን ይጫኑ።



 

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ሰ/ትቤቶች ማደራጃ መምሪያ በማኅበረ ቅዱሳን የአውሮፓ ማዕከል የገዳማትና ቅዱሳን መካናት ማስተባበሪያ ክፍል

ገዳማትና አብነት ትምህርት ቤቶችን በመርዳት

መንፈሳዊ ግዴታዎን ይወጡ!!!

  1. መግቢያ
  • ገዳማት እና አብነት ትምህርት ቤቶች የቤተ ክርስቲያናችን የህልውናዋ እስትንፋሶችና የውሳጣዊ ቁመናዋ መገለጫዎች ናቸው፡፡
  • ገዳማት:- የቤተ ክርስቲያናችን መንፈሳዊ አገልግሎት መሠረት፣ የአስተምህሮዋ (ዶግማዋ ፣ ቀኖናዋ እና ትውፊቷ)ምንጭ፣  የመንፈሳውያን መሪዎቿ መገኛ እና ለመላው ምዕመናን የመንፈሳዊ ጥንካሬ ማግኛ ቦታ ሲሆኑ፣
  • አብነት ትምህርት ቤቶች:- ደግሞ በኢትዮጵያ ማዕከላዊ መንግሥት በተመሠረተበት ጊዜ ቤተ ክርስቲያናችን ብዕር ቀርጻ፣ ብራና ፍቃና ቀለም በጥብጣ ዜጎችን  ስታስተምር ቀዳማዊ ትምህርት ሚኒስቴር በመሆን አገልግለዋል፡፡
  • በአሁኑ ጊዜ ከ 5000 በላይ የአብነት መምህራንና ከ 100000 በላይ የአብነት ተማሪዎች እንዳሉ ይገመታል።
  1. የገዳማትና አብነት ትምህርት ቤቶች መሠረታዊ ችግሮች
  • በሀገራችን የካቲት 25/1967 ዓ.ም በታወጀው የመሬት ለአራሹ አዋጅ ምክንያት አድባራትና ገዳማት ይተዳደሩበት የነበረው መሬት ማጣታቸው፣
  • ቋሚ የልማት ስራ እና የገቢ ምንጭ ስለሌላቸው ህልውናቸው ያለው በምዕመናን ልገሳ ላይ መሆኑ፣
  • ዘመናዊ ትምህርት ሲስፋፋ አብነት ትምህርት ቤቶች የሥልጣኔ በር ከፋቾች መሆናቸው ተዘንግቶ  ትኩረት የተነፈጋቸው መሆኑ እና ቀዳሚ የነበረውን ቦታቸውን ማጣታቸው፣
  • በተለያዩ ሙያዎች ተምረው የተመረቁት የአብነት ምሁራን  ለሙያቸው የሚመጥን ምደባና ክፍያ ካለማግነታቸውም በተጨማሪ ሌላ የኑሮ አማራጭ የሌላቸው መሆኑ፣
  • የቤተክርስቲያናችን ተነባቢ ቤተ መጻሕፍት የሆኑ ስመ ጥር ሊቃውንት ተተኪ ሳያፈሩ በጤናና እርጅና እያለፉ መሆናቸው፣
  • ምዕመኑ ለአብነት ተማሪዎች ከዚህ በፊት ሲያደርግ የነበረውን ትኩረትና ድጋፍ መቀነሱ፣
  • በቤተክርስቲያናችን የተማከለ /በገጠርና በከተማ፣ በአገር ቤት በውጭ ሀገራት/ እና የትምህርት ደረጃና አገልግሎትን ያማከለ የደምወዝ ክፍያ ለአብነት መምህራን እና ለአገልጋይ ካህናት አለመኖሩ የሚሉት ተጠቃሾች ናቸው፡፡
  1. ሱታፌ ማኅበረ ቅዱሳን ዘአውሮፓ ማዕከል

ይህንን መሠረታዊ የሆነ የአብነት ትምህርት ቤቶችና ገዳማት ችግር በዘላቂነት ለመፍታት  በማኅበረ ቅዱሳን የአውሮፓ ማዕከል በአውሮፓ የሚገኙ ምእመናንን በማስተባበር  በምሳሌነት ሊጠቀሱ የሚችሉ ድጋፎችን አድርጓል፡፡ በተደረገው ማስተባበር እንቅስቃሴ ድጋፍ ከተደረገላቸው ፕሮጀክቶች መካከል፡-

  1. የሞጣ ቅዱስ ጊዮርጊስ የመጽሐፍት ትርጓሜ ትምህርት  ቤት ህንፃ ግንባታ፣
  2. አቃቂ አባ ሳሙኤል ገዳም የከብት እርባታ ፕሮጀክት፣
  3. በአበልቲ ምዕራፈ ቅዱሳን ቅድስት ኪዳነ ምሕረት ገዳም የአብነት ተማሪዎች መኖሪያ፣
  4. የደብር ቅዱስ ደብረ ጽጌ ማርያም የአንድነት ገዳም የአብነት ተማሪዎች መኖሪያ እና እቃ ቤት እድሳት፣
  5. የደብረ ካስዋ ጉንዳጉንዲ ቅድስት ማርያም ገዳም ሁለገብ ህንጻ ግንባታ፣
  6. የምዕራፈ ቅዱሳን በልበሊት ኢየሱስ አንድነት ገዳም የመስኖ ልማት ፕሮጀክት፣
  7. የምስካበ ቅዱሳን ዑራኤል ወሳሙኤል ዘዋልድባ ገዳም ትምህርት ቤት ግንባታ፣
  8. ለአብነት መምህራንና ተማሪዎች ወርሃዊ የገንዘብ ድጎማ የሚኩት ተጠቃሾች ናቸው፣
  1. ምን እናድርግ ?

በማኅበረ ቅዱሳን የአውሮፓ ማዕከል ከዚህ በፊት ሲያደርግ እንደነበረው ሁሉ በዚህ ዓመትም በአውሮፓ የሚገኙ ምእመናን በማስተባበር  ከላይ የተገለጹትን መሠረታዊ ችግሮች በዘላቂነት ደረጃ በደረጃ ለመፍታት ድጋፍ ለማሰባሰብ እቅድ ይዟል።

በ2011 ዓ.ም በዳውሮ ኮንታ ሀገረ ስብከት ስር ለሚካሄደው የአብነት ትምህርት ቤት ግንባታው ከ 62500 ዩሮ በላይ ድጋፍ ለማድረግ ውቅድ ተይዟል። የፕሮጀክቱን ዝርዝር እዚህ ይመልከቱ

እርሶዎም የገዳማት  እና አብነት ት/ቤቶች መንፈሳዊ ፣ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታቸውን ለመጠበቅና ለትውልድ ለማስተላለፍ የበኩልዎን ድጋፍ እንዲያደርጉ  እና የበረከቱ ተሳታፊ እንዲሆኑ በእግዚአብሔር ስም እንጠይቃለን።

  1. አድራሻ

ለገዳማት እና አብነት ት/ቤቶች ድጋፉ ለማድረግ የሚከተሉትን ዘዴዎች ይጠቀሙ  :-

  1. በቀጥታ በባንክ ወደ ማኅበረ ቅዱሳን አውሮፓ ማእከል ሂሳብ በማስተላለፍ

Mahibere Kidusan In Europa

BAN : DE14 3704 0044 0307 803 700

BIC : COBADEFF

Reason : Donation gedamate code 001

Commercial Bank

Bank address : Maternusstr.5; 50996 Cologne, Germany

  1. ፔይ ፓልን በመጠቀም ወደ አውሮፓ ማዕከል ባንክ አካውንት በማስተላለፍ።

ለተጨማሪ መረጃ እና ጥያቄ በ eu.monasteries@eotcmk.org ይጻፉልን።