“መዝሙሮቻችን ከየት ወዴት” በሚል ርዕስ በመዝሙራት ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ መርሐ ግብር ተካሄደ

በእንግሊዝ ንዑስ ማዕከል

ነሐሴ 5 ቀን 2008 ..

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ማኅበረ ቅዱሳን አውሮፓ ማዕከል የዩኬ (እንግሊዝ) ንዑስ ማዕከልመዝሙሮቻችን ከየት ወዴት” በሚል ርእስ ሐምሌ ፳፬ ቀን ፳፻፰ ዓ.ም የኖቲንግሃምና የአቅራቢያ ከተሞች ካህናትና ምእመናን፣ የሰንበት ት/ቤት መዘምራንና የንዑስ ማእከሉ አባላት በተገኙበት በኖቲንግሃም ከተማ የግንዛቤ ማስጨበጫ መርሐ ግብር አካሄደ።

uknew3

የመርሐ ግብሩ ዋና ዓላማም በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ስም እየታተሙ ገበያ ላይ የሚዉሉ የአማርኛ መዝሙራት ከያሬዳዊ ዜማ ጋር ያላቸውን ግንኙነት ማጥናትና የመፍትሔ አቅጣጫዎችን ማመላከት ሲኾን በዕለቱ በሦስት ዋና ዋና አርእስት ላይ ያተኮሩ ጥናታዊ ጽሑፎች ቀርበዋል፡፡ በእያንዳንዱ ገለጻ ላይም በአራቱ ወንጌላውያን ስም የተሰየሙ የቡድን ውይይቶች ተካሒደዋል።

uknews2 uknews1

በመርሐ ግብሩ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ዜማ፤ በአማርኛ መዝሙራት የይዘት ችግሮች እና በቅዱስ ያሬድ ታሪክና ዜማዎቹ ላይ ያተኮረ ጥናታዊ ዘገባ በሊቀ ዲያቆናት ልዩ ወዳጅ፤የአማርኛ መዝሙራት በተለያዩ አዝማናትበሚል ርእስ በመጋቤ ሠናይ ሳምሶን ሰይፈ፤ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ስም የወጡ መዝሙራትና የመናፍቃን መዝሙራት ተመሳሳይነት፦ምን እናድርግበሚል ርእስ በዲ/ን ዶ/ር አዳነ ካሣ ጥናታዊ ጽሑፎች ቀርበዋል።

የመጀመሪያዉ ዙር የግንዛቤ ማስጨበጫ መርሐ ግብር በጥር ወር ፳፻፰ ዓ.ም በበዓለ ጥምቀት ዋዜማ በበርሚንግሃም ከተማ ተዘጋጅቶ የነበረ ሲኾን በኖቲንግሃም ከተማ የተዘጋጀው ይህ መርሐ ግብር ሁለተኛው ዙር ነው። በጉባኤው ላይ የተገኙ ምእመናን በማጠቃለያዉ ላይ በሰጡት አስተያየት መሠረትም በ፳፻፱ ዓ.ም ሦስተኛ ዙር መርሐ ግብር በለንደን ከተማ ለማካሔድ ዕቅድ ተይዟል።

በመጨረሻም ዚህ ዝግጅት መሳካት በማኅበረ ቅዱሳን የአዉሮፓ ማዕከል ትምህርት ክፍል የጥናት ጽሑፉን በማበርከትና ሥራዉ በማበረታታት፣ የዩኬ ን/ማዕከል አባላት ሥራዉን በማቀናጀትና በማስተባበር፣ በተለያዩ አብያተ ክርስቲያናት በአገልግሎት ላይ የሚገኙ ካህናት አባቶች፣ ወንድሞች ዲያቆናት እንዲሁም ብዙ ምዕመናን ፍተኛ አስተዋጽኦ ያበረከቱ ሲሆን በገንዘባቸዉ፣ በሃሳባቸዉ እና በተለያየ ሁኔታ ትብብር ላደረጉ ምእመናን ሁሉ ንዑስ ማዕከሉ በእግዚአብሔር ስም ከፍ ያለ ምስጋና አቅርቧል