ሆሣዕና

በዲ/ን ብሩክ አሸናፊ

መጋቢት 23 ቀን 2010 ዓ.ም.

ሆሣዕና ማለት መድኃኒት ማለት ነው። ሆሣዕና ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በአህያ እና በውርንጫይቱ ላይ ተቀምጦ ከሕዝቡም ብዙዎች ልብሳቸውንና የዘንባባ ዝንጣፊ በመንገድ እያነጠፉለት የሚቀድሙትም የሚከተሉትም ሆሣዕና ለዳዊት ልጅ በጌታ ሥም የሚመጣ ቡሩክ ነው ሆሣዕና በአርያም እያሉ እያመሰገኑት ወደ ኢየሩሳሌም የገባበትና የለዋጮችን ገበታዎችና የርግብ ሻጮችን ወንበሮች ገልብጦ ቤተ መቅደሱን ያነጻበት እና ለአምልኮ ብቻ የቀደሰበት በዓል ነው።

ጌታችን ወደ ኢየሩሳሌም ሊገባ በቀረበ ጊዜ በደብረ ዘይት አጠገብ ከምትገኝ ቤተ ፋጌ ሲደርስ ሰው ሁሉ ከማዕሠረ ኃጢአት የሚፈታበት ጊዜ እንደደረሰ ለማጠየቅ ከደቀ መዛሙርቱ ሁለቱን በፊታችሁ ወዳለችው መንደር ሂዱ በዚያም አህያ ከውርንጫዋ ጋር ታስራ ታገኛላችሁ ፤ ፈታችሁ አምጡልኝ ፤ ማንም አንዳች ቢላችሁ ለጌታ ያስፈልጉታል በሉ ሲል ላካቸው። መንደር የሲዖል ፣ አህያይቱና ውርንጫይቱ የአዳምና የልጆቹ ፣ በመንደር መታሰራቸው አዳምና ልጆቹ በመርገመ ሥጋ በመርገመ ነፍስ ተይዘው በሲዖል በባርነት መኖራቸውንና ጌታችንም የሲዖል ባርነት አስወግዶ ነጻነትን የሚያድልበት ጊዜ እንደቀረበ ያጠይቃል። ዛሬም እኛ ልጆቹ በማዕሰረ ኃጢአት ተይዘን ከእርሱ ስንርቅ ከማዕሰረ ኃጢአት ፈትተው ወደርሱ የሚያቀርቡንን ካህናትን ሰጥቶናል። Read more

ዐቢይ ጾም

በታምራት ኃይሉ

የካቲት 5 ቀን 2010 ዓ.ም.

ጾም ማለት ሰውነትን ከሚያስፈልጋቸው ነገር ሁሉ መከልከል፣ ለሥጋ የሚመቸውን ነገር መተው ማለት ነዉ፡፡ ጌታችን መጾም ሳያስፈልገው የጾመው በጾም መሣሪያነት ዲያቢሎስን ድል ታደርጋላችሁ ሲለን ነው፡፡  እርሱ ድል አድርጎታል ካልጾሙ ካልጸለዩ ሰይጣንን ድል ማድረግ እንደማይቻል ጌታ አስተምሮናል፡፡ ጾም ፊትን ወደ እግዚአብሔር ማቅናት እንደሆነ በሰብአ ነነዌ ታውቋል እነዚህ ሰዎች ወደ እግዚአብሔር የተመለሱት በጾም ነውና፡፡ ኃጢያታቸዉ እጅጉን ገዝፎ ቅድመ እግዚአብሔር ስለደረሰ የጌትነቱ ቁጣ አስቀድሞ ከመምጣቱ በፊት ንስሐ እንዲገቡ መሐሪ እግዚአብሔር ነብዩ ዮናስን ላከላቸዉ፡፡ ህዝቡም የነብዩ ዮናስን ስብከት ሰምነተው በክፉ ሥራቸዉ ተጸጽተዉ ከሊሒቅ እስከ ደቂቅ ማቅ ለብሰው ጾሙ፣ ሕፃናትና  እንስሳትም የንስሀቸዉ ተካፋይ እንዲሆኑ አደረጉ፡፡ በዚህ ግዜ የፍጥረቱን መዳን እንጂ መጥፋቱን የማይወድ እግዚአብሔር ቁጣዉን በትዕግስት መዓቱን በምሕረት መልሶ በይቅርታ ጎበኛቸው ከተቃታዉ መቅሠፍት አዳናቸዉ (ዮና  ፫ ፡ ፭-፲ )፡፡ ወደ እግዚአብሔር በጾም በጸሎት የተመለሱ ድኅነትን እንዳገኙ ሁሉ ያልተመለሱ ደግሞ ጠፍተዋል፡፡ ለምሳሌ ሰብአ ሰዶም ገሞራ እንደ ነነዌ ሰዎች ወደ እግዚአብሔር ባለመመለሳቸዉ እሳት ከሰማይ ወርዶ አቃጥሎ አጥፍቶአቸዋል (ዘፍ ፲፱፡፳፫)፡፡  Read more

ዕረፍተ ሶልያና

በዲ/ን ዶ/ር ቴዎድሮስ በለጠ 

ጥር  21 ቀን 2010 ዓ.ም.

 

የቤተክርስቲያናችን ዓይን ሊቁ ቅዱስ ያሬድ ለአምልኮ መቅረዝ ለምስጋና ማኅቶት በሆነው የድጓ ድርሰቱ የእመቤታችንን የከበረ ዕረፍት ከዘመነ አስተርእዮ ምስጢር ጋር እያዛመደ እንዲህ አስፍሮታል።

∽†∽ “ጊዜ ዕረፍታ ለሶልያና፣ ወረደ ወልድ እም ዲበ ልዕልና፣ ጠሊሳነ ንግሥ ሶቤሃ ከደና ” ∽†∽

ድጓ: መነሻው “ድግ” ነው የሚሉ ዓይናማ ሊቃውንት “ድጋ ለቤተክርስቲያን” ብለው ድርሰቱ የተዋህዶ መደገፊያ መሆኑን ይነግሩናል። ምንጩን  ደግደገ ካለው አንስተው ድግዱግ በሚለው ደቃቅ ለማለት ስበው ረቂቅ ማለትም ነው ይላሉ ፤ እንደ ሊቃውንቱ ሀተታ ከጽሕፈቱ ረቂቅነት ከምልክቱ ብዛት የተነሣ የተሰጠው መጠሪያ ነው። በሌላ አገባብም በዘይቤው የዓመቱ መዝሙራት ተወጣጥተው ተሰብስበው ይገኙበታልና ድጓ እስትጉቡእ ወይም ስብስብ ማለትም ይሆናል።

ሊቁ በዚህ የድጓ ድርሰቱ፦ የነቢያቱን የትንቢት ማረፊያ፣ የሐዋርያቱን የስብከት መነሻ፣ የነገረ ድኅነት ጥልቅ ማብራሪያ፣ የሆነውን ነገረ ማርያምን በልዩ መንገድ ያስረዳናል። በተለይም የሥላሴ ማደሪያ የቤተ ክርስቲያን አንደበት ለሥጋ ለባሽ ሁሉ ትምክኅት የሆነች እመቤታችን በዘመነ አስተርእዮ በጥር ፳፩ ቀን የተከናወነው የከበረ “ዕረፍተ ሶልያና” በምን ክስተት እንዳለፈ እንዳንዘነጋው ሁሉን ከሚያስብ ከማይዘነጋ ልጇ እንድታማልደን እየተማጸነ ጭምር አብራርቶ ይዘግባል። Read more

በዓለ ልደቱ ለእግዚእነ ወአምላክነ ወመድኃኒነ ኢየሱስ ክርስቶስ

በበኩረ ፍሥሐ ቀሲስ ኃይለኢየሱስ ተመስገን

ታኅሣሥ 28 ቀን 2010 ዓ.ም.

“እስመ ናሁ እዜንወክሙ ዓቢየ ዜና ዘይከውን ፍሥሐ ለክሙ ወለኩሉ ሕዝብ “ሉቃ ፪ ፥፲

ለወልደ እግዚአብሔር ሁለት ልደታት እንዳሉት እናምን ዘንድ ይገባናል። አንዱ ከዘመን ሁሉ አስቀድሞ ከእግዚአብሔር አብ የተወለደው ልደት ነው። ሁለተኛውም ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም በኋላ ዘመን የተወለደው ልደት ነው፡፡ሃይማኖተ አበው ዘባስልዮስ ምዕራፍ ፴፬ ቁጥር ፮ ክፍል ፭። Read more

“ወይንሳዕ መስቀለ ሞቱ ወይትልወኒ – የሞቱን መስቀል ተሸክሞ ይከተለኝ”

በዲ/ን ዶ/ር ቴዎድሮስ በለጠ

መስከረም 16 ቀን 2010 ዓ.ም.

ለስም አጠራሩ ክብር ይግባውና በቃል መነገሩ፣ በኅሊና መዘከሩ፣ በሰው ልብ መታሰቡ፣ በቅዱሳት መጻሕፍት መዘገቡ ከፍ ይበልና፣ ጌታችንንና አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እኛ ልጆቹ ፈቃዱን እያደረግን እንድንኖርና እርሱም ከመልካም ምግባራችንና ከበጎ ትሩፋታችን ብቻ የተነሳ ፍጹማን እንደማንሆን ያውቃልና፣ ከማያልቅ ልግስናው ከማይጓደል ምሕረቱ ዘመናትን እየመጸወተን ደስ የሚሰኝበትን ለእኛ እያደረገ በቸርነቱ ያኖረናል:: ከእርሱና ከዓላማው ጋር ጸንተን እንድንኖርም እንዲህ ሲል በቅዱስ ወንጌል አዝዞናል:: “ዘይፈቅድ ይትልወኒ ይጽላዕ ነፍሶ ያጥብዕ ወይንሳዕ መስቀለ ሞቱ ወይትልወኒ (እኔን መከተል የሚወድ ቢኖር፥ ራሱን ይካድ መስቀሉንም ተሸክሞ ይከተለኝ) ወምንተ ይበቁዖ ለሰብእ ለእመ ኩሎ ዓለመ ረብሐ ወነፍሶ ኃጉለ (ሰው ዓለሙን ሁሉ ቢያተርፍ ነፍሱንም ቢያጐድል ምን ይጠቅመዋል?)” (ማቴ. 16:24-26)።

Read more

ጰራቅሊጦስ

በቀሲስ ኃይለኢየሱስ ተመስገን

ግንቦት 26 ቀን 2009 ዓ.ም.

በቅዳሴ ጸሎት ካህናት ከሚጸልዩት ጸሎት ውስጥ “ወቡሩክ መንፈስ ቅዱስ ጰራቅሊጦስ መጽንዒ ወመንጽሔ ኩልነ” የሚል እናገኛለን ሁላችንን የሚያነጻ፣ የሚያጸና መንፈስ ቅዱስም ቡሩክ ነው ማለት ነው። በዚህ ጸሎት ላይ ጰራቅሊጦስ የሚለው ቃል ከሦስቱ አካላት አንዱ ለኾነው ለእግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ መጠሪያ እንደሆነና የሚያነጻ፣ የሚያጸና መሆኑን ይገልጣል። Read more

ቀርቦሙ እግዚእ ኢየሱስ ወሖረ ምስሌሆሙ (ጉዞ ከእግዚአብሔር ጋር) ሉቃስ 24÷13­-45

በቀሲስ ኃይለኢየሱስ ተመስገን

ሚያዚያ 21 ቀን 2009 ዓ.ም.

ክርስቶስ ተንሥአ እሙታን ……………. በዓቢይ ኃይል ወሥልጣን

አሰሮ ለሰይጣን …………………………..አግአዞ ለአዳም

ሰላም ……………………………………… እም ይእዜሰ

ኮነ…………………………………………..ፍሥሐ ወሰላም

“ክርስቶስ በታላቅ ኃይልና ሥልጣን ከሙታን ተለይቶ ተነሣ ፤ ዲያብሎስን አሰረው አዳምን ነጻ አወጣው ፤ ሰላም ከዛሬ ጀምሮ ሰላም ሆነ”

13.ወይእተ ዕለእንዘ የሐውሩ ክልኤቱ እምውስቴቶሙ ሀገረ እንተ ርኅቅት እምኢየሩሳሌም መጠነ ስሳ ምዕራፍ እንተ ስማ ኤማኁስ።

ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የትንሳኤ በኵር ሆኖ ከሙታን መካከል በተነሣበት ዕለት በሰንበተ ክርስቲያን ከመቶ ሃያዎቹ የክርስቶስ ቤተሰቦች ውስጥ ሁለቱ ደቀ መዛሙርት ከኢየሩሳሌም 60 ምዕራፍ ያህል ወደምትርቀው ኤማኁስ ወደምትባለው መንደር ሲሄዱ ስላጋጠማቸው ወንጌል የሚነግረንን አባቶቻችን ያስተማሩንን እንመለከታለን።

ቅዱስ ሉቃስ በጻፈው ወንጌል የተጠቀሰው የቀልዮጳ ስም ብቻ በመሆኑ(ሉቃስ 24÷18) ሁለቱ የኤማኁስ መንገደኞች ራሱ ወንጌላዊው ቅዱስ ሉቃስ እና ቀልዮጳ እንደሆኑ ይነገራል። አባቶቻችንም ሉቃስን ዘውእቱ ቀልዮጳ/ሉቃስ ማለት የቀልዮጳ ሌላ ስም ነው/ በማለት ሁለቱ የኤማኁስ መንገደኞች ሉቃስና ኒቆዲሞስ ናቸው ብለው በወንጌል ትርጓሜ ላይ አስቀምጠዋል።  Read more

ሆሣዕና

በኤርምያስ ልዑለቃል

መጋቢት 30 ቀን 2009 ዓ.ም.

ሆሣዕና ቃሉ የዕብራይስጥ ሲሆን ትርጉሙም አሁን አድን ማለት ነው። በቅድስት ቤተ ክርስቲያን ሥርዓት መሠረት የታላቁ ዓቢይ ጾም ስምንተኛ እሑድ የሆሣዕና በዓል በድምቀት የሚከበርበት ዕለት ነው። በዚህ ዕለት ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በታላቅ ትህትና በአህያ ጀርባ ተቀምጦ ወደ ኢየሩሳሌም ያደረገውን ጉዞ የሚዘክር ቃለ እግዚአብሔር በስፋት ይደርሳል። በአራቱም ወንጌላውያን በቅዱስ ማቴዎስ፣ ማርቆስ፣ ሉቃስ ና ዮሐንስ ይህንኑ የፍጹም ትህትና እና የፍቅር ጉዞ አስመልክቶ የተጻፉ የወንጌል ክፍሎች  (ማቴ 21፥1-17 ፣ ማር 11፥1-10 ፣  ሉቃ 19፥28-44 ፣ ዮሐ 12፥9-19) በቅድስተ ቤተ ክርስቲያን ዑደት እየተደረገ በአራቱም አቅጣጫዎች ይነበባሉ። Read more

ምኵራብ

ዲያቆን አለባቸው በላይ

የካቲት 25 ቀን 2009 ዓ.ም

 

ቅዱስ ወንጌል እንደሚነግረን በምኵራብ ያገለግሉ ዘንድ የተሾሙ ካሕናተ አይሁድ እና የጥቅም ተጋሪዎቻቸው ኃላፊነታችውን ረስተው፣ዓላማችውን ዘንግተው ቅዱስ የሆነውን የእግዚአብሔርን ቤት መንፈሳዊ ገበያነቱ ቀርቶ የሥጋ ገበያ፤ ቅጽረ ምኵራብን የወንበዴዎች መናኻሪያ (ማቴ 21:13፤ ሉቃ19:46) አድርገውት ነበር። በዚህ ምክንያት በቤቱ ተገኝቶ ጸሎት ማድረስ፤ መባእ ማቅረብ፤ ከፈጣሪ ጋር መገናኘት የማይቻልበት ሁኔታ ተፈጥሮ ነበር። ስለዚህ ነው አምላክ ወልደ አምላክ ኢየሱስ ክርስቶስ በምኵራብ ተገኝቶ ካህናቱን እና ሻጭ ለዋጮችን በመገሰጽ፤ በመግረፍ፤ ገበያውን በመበተን ቤቱን ያነጻውና ክብርና ልዕልናዋን በተግባር ያስተማረው። Read more

ቅድስት

ዲያቆን መስፍን ኃይሌ

የካቲት 18 ቀን 2009 ዓ.ም


የቤተክርስትያናችንን መዝሙር ንባቡን ከዜማው አስማምቶ አጠናክሮ ያስተላለፈልን ኢትዮጵያዊው ሊቅ ቅዱስ ያሬድ በጾመ ድጓው በዓ ጾም ለሚገኙትን እሑዶች ሁሉ የተለየ መዝሙር ስለሠራላቸው እያንዳንዱ እሑድ በመዝሙሩ ስም ይጠራል በዚህም መሰረት የዚህ ታላቅ ጾም ሁለተኛው እሑድ ቅድስት ተብሎ ተሰይሟል። ቅድስት የሚለው ቃል ግሱቀደሰሲሆን ለየ አከበረ መረጠ የሚል ትርጉም ይይዛል። ቅድስት ማለት የተየች የተመረጠች የከበረች ማለት ነው። ቅዱስ የሚለው ቃል እንደ የአገባቡ ለፈጣሪም ለፍጡርም ያገለግላል። ለፈጣሪ ሲነገር እንደ ፈጣሪነቱ ትርጉሙ ይሰፋል ይጠልቃል ለፍጡር ሲነገር ደግሞ እንደ ፍጡርነቱ እና እንደ ቅድስናው ደረጃ ትርጉሙ ሊወሰን ይችላል። እግዚአብሔርን ቅዱስ ስንል የባህሪ የሆነ ፣ኃጢአት የማይስማማው ፣ለቅድስናው ተወዳዳሪ ካካሪ የሌለው፣ ወደር የማይወጣለት ፣ዘለዓለማዊ የሆነ ማለታችን ሲሆን ፍጡራንን ግን ቅዱሳን ስንል ቅድስናቸው የጸጋ የሆነ ፤ከእግዚአብሔር ያገኙት ፤እንደነጭ ልብስ ጽድቁም ኃጢአቱም እንደ ዝንባሌአቸው የሚስማማቸው፤ ለቅድስናቸው ማዕረግ ደረጃ የሚወጣለት እንደ ገድል ትሩፋታቸው መጠን ሊጨምርም ሊጎድልም የሚችል ማለታችን ነው። ከፍጡራን መካከል ለእግዚአብሔር የተለዩ ሁሉ በጸጋ የቅድስናው ተሳታፊ ሊሆኑ ይችላሉ። መላእክት፣ ሰዎች፣ መካናት፣ ዕለታት ፣አልባሳት፣ ንዋያት ሁሉ ለእግዚአብሔር እስከ ተለዩ ድረስ ከቅድስናው በረከት ይሳተፋሉ እንደ የደረጃቸው ቅዱሳን ተብለው ይጠራሉ።

Read more