ዓውደ ዓመት
ዓውደ ዓመት ለባርኮ ባርኮ ዓውደ ዓመት (2)
ንኢ ማርያም በምህረት ወሳህል (4)
መስቀልከ ይኩነነ ቤዛ
መስቀልከ ይኩነነ ቤዛ (2)
ይኩነነ ቤዛ (4) መስቀልከ ይኩነነ ቤዛ(2)
ትርጉም፡ መስቀልህ ቤዛ (መድኃኒት) ይሁነን
አክሊለ ፅጌ
አክሊለ ፅጌ ማርያም ቀፀላ መንግስቱ ለጊዮርጊስ (2)
ኧኸ ክበበ ጌራ ወርቅ(2) አክሊለ ፅጌ (2)
ትርጉም፡ የጊዮርጊስ የዘውዱ ጌጥ አንቺ ነሽ
ማርያም ፊደል
ማርያም ፊደል የሁሉ መማሪያ (2)
በንፅህና በንፅህና ተፅፋለችና (4)
ፄና አልባሲሁ
ፄና አልባሲሁ (2) ለገብረ መንፈስቅዱስ ከመ ፄና ስኂን (2)
አልበስዎ ዘሜላት (2) ዘወረደ ውስተ ገነት (2)
ያልጠፋነው
ያልጠፋነው ከእግዚአብሔር ምህረት የተነሳ ነው (2)
ቸርነቱ ከቶ አያልቅምና ርህራሄው ከቶ አያልቅምና ይገባዋል ክብርና ምስጋና(4)
መድኃኔዓለም አዳነን
መድኃኔዓለም አዳነን በማይሻር ቃሉ (2)
ኧኸ ደስ ይበለን (2) እልል በሉ (2) አዳነን በማይሻር ቃሉ (2)
ኃይል የእግዚአብሔር ነው
ኃይል የእግዚአብሔር ነው ማዳን የእግዚአብሔር ጥበብ የእግዚአብሔር (2)
አንመካም በጉልበታችን እግዚአብሔር ነው የኛ ኃይላችን (2)
የኪዳን ጽላት
የኪዳን ጽላት የተሰወረ መና ያለብሽ ደብተራ ምስዋዕ አንቺ ነሽ (2)
ይኸውም መና የተባለው (2) በድንግል ማርያም ያደረው የእግዚአብሔር ልጁ ነው (2)
ዐይኑ ዘርግብ
ዐይኑ ዘርግብ ልብሱ ዘመብረቅ (2)
ሚካኤል ሐመልማለ ወርቅ ( 4)
ተዋሕዶ ንጽሕት
ተዋሕዶ ንጽሕት ቅድስት እምነታችን (2)
ኑሪ ለዘላለም ተከብረሽ በአምላካችን (2)
ኩሉ ዘፈቀደ
ኩሉ ዘፈቀደ ገብረ እግዚአብሔር (2)
በሰማይኒ ወበምድርኒ ወበባሕርኒ ወበኩሉ ቀላያት ቀላያት(4)
ክብሮሙ ለመላእክት
ክብሮሙ ለመላእክት ከመመንኮራኮር ወረደ መላእከ እግዚአብሔር (2)
ኀበ ማርያም ድንግል ዘተናገሮ ለሙሴ በኀበ እፀ ጳጦስ (2)
ቤዛ ኩሉ
ቤዛ ኩሉ ዓለም ዮም ተወልደ (2)
ቤዛ ኩሉ ዓለም ዩም ተወልደ (4)
የዓለም መድኃኒት ዛሬ ተወለደ (2)
የዓለም መድኃኒት ዛሬ ተወለደ (4)
በኮከብ መጽኡ
በኮከብ መጽኡ መጽኡ ሰብአሰገል (2)
ለአማኑኤል (4) ይስግዱ ሰብአሰገል (2)
በኮከብ መጡ መጡ ሰብአሰገል (2)
ለአማኑኤል (4) ሊሰግዱ ሰብአሰገል (2)
ተክለ ሃይማኖት
ተክለ ሃይማኖት የዓለም ብርሃን ናቸው (2)
ይሄው ለዘለዓለም ያበራል ስራቸው (2) ያበራል ስራቸው (2)
ነአምን በአብ
ነአምን በአብ ወነአምን በወልድ (2)
ወነአምን (4) ነአምን በመንፈስ ቅዱስ (4)
እናምናለን በአብ እናምናለን በወልድ (2)
እናምናለን (4) እናምናለን በመንፈስ ቅዱስ (4)
በእደ ዮሐንስ
በእደ ዮሐንስ ተጠምቀ ኢየሱስ ናዝራዊ (2)
ኧኸ ሰማያዊ (4) ሰማያዊ ኢየሱስ ናዝራዊ (2)
መጽአ ቃል
መጽአ ቃል እምደመና ዘይብል ዘይብል (2)
ዝንቱ ውእቱ ወልድየ ዘአፈቅር (4)
መጣ ቃል ከደመና እንዲህ የሚል (2)
የምወደው የማፈቅረው ልጄ ይህ ነው (4)
ኅዲጎ ተሰዓ
ኅዲጎ ተስዓ ወተሰዓተ ነገደ ነገደ(2)
ኧኸ ማዕከለ ባህር (4) ቆመ ማዕከለ ባህር(2)
ትርጉም፡ ዘጠና ዘጠኙን ነገድ ትቶ በባህር መካከል ቆመ
ጾም
ጾም ወፀሎት ወተፋቅሮት (2)
ሃይማኖት ወምፅዋዕት ታድህን እሞት(2) ታበፅዕ መንግስተ ሰማያት (2)
ኪዳንኪ ኮነ
ኪዳንኪ ኮነ (3) ኪዳነምሕረት (2)
ለኃጥአን ቤዛነ ለኃጥአን ተስፋነ ኪዳንኪ ኮነ (2)
ቃልህን ሰምቼ
ቃልህን ሰምቼ ሕይወትን እንዳገኝ (2)
ማስተዋልና ጥበብን ስጠኝ (4)
ሠራዊተ መላእክቲሁ
ሠራዊተ መላእክቲሁ (2)
ኧኸ ለመድኃኔዓለም (2) ይቀውሙ (4)
ሰአሊ ለነ
ሰአሊ ለነ(6)
ኧኸ ማርያም እመ ብዙኀን (4)
ለምኝልን(6)
ኧኸ ማርያም የሁሉም እናት (4)
ሆሳዕና እምርት
ሆሳዕና እምርት እንተ አቡነ ዳዊት (2)
ቡርክት እንተ ትመጽእ መንግሥት (2)
ወምድርኒ
ወምድርኒ ትገብር ፋሲካ (2)
ተሐጺባ በደመ ክርስቶስ(4)
ምድር ፀዳች ሐሴት አደረገች (2)
በክርስቶስ ደም በእውነት ታጠበች (4)
ትንሣኤከ
ትንሣኤከ ለእለ አመነ (2)
ብርሃነከ ፈኑ ዲቤነ (4)
ትንሣኤህን ለምናምን ለኛ (2)
ብርሃንህን ላክልን ወደ እኛ (4)
ልዑል እግዚአብሔር
ልዑል እግዚአብሔር (2) ምስጋና ይገባሃል (2)
ለዚህች ዕለት ለዚህች ሰዓት በሰላም በጤና አደረስከን (2)
ርኢክዋ
ርኢክዋ ለቤተ ክርስቲያን አፍቀርክዋ ለቤተ ክርስቲያን (2)
ዘኢትዮጵያ (2) ቤተ ክርስቲያን (2)
አየኋት ቤተ ክርስቲያንን ወደድኳት ቤተ ክርስቲያንን (2)
የኢትዮጵያ (2) ቤተ ክርስቲያን (2)
ተወልዳለችና
ተወልዳለችና የጌታ እናት ለእኛ መድኅኒት (2)
እናወድሳት እናመስግናት እንውደዳት (2) የአምላክን እናት (2)
መሠረተ ዜማ
መሠረተ ዜማ ወጠነ (2) ያሬድ ካህን (2)
ያሬድ (3) ያሬድ ካህን ጥዑመ ልሳን (2)
ለተክለ ሃይማኖት
ለተክለ ሃይማኖት ጻድቅ መጠነ በዝኀ ሕማሙ(2)
ትዌድሶ ደብረ ሊባኖስ ገዳሙ (2)
የመጀመሪያ ሁለት ስንኞችን ብቻ ለልጆች ማስጠናት (በድምፅ ያለው ረጅም ነው )
አንትሙሰ ንበሩ
አንትሙሰ ንበሩ አንትሙሰ ንበሩ ሀገረ ኢየሩሳሌም (2)
እስከትለብሱ ኃይለ እምአርያም (4)
እናንተ ግን ቆዩ በኢየሩሳሌም ሀገር (2)
እስከምታገኙ ኃይልን ከሰማይ (4)
ዝማሬ ዳዊትን
ዝማሬ ዳዊትን ተልዕኮ አርድእትን ቅዳሴ መላእክትን (2)
የተቀበልክ አምላክ (4) የኛንም ዝማሬ ተቀበል (2)
ሚካኤል ስዩም
ሚካኤል ስዩም ስዩም ሊቀ መላእክት (2)
መዝገበ ርህራሄ (3) ወየዋሃን (2)
ጊዮርጊስ ኃያል
ጊዮርጊስ ኃያል ኃያል መስተጋድል(2)
ኧኸ ገባሬ ተአምር (2)ኮከበ ክብር(2)
ዐረገ በስብሐት
ዐረገ በስብሐት ዐረገ በእልልታ በስብሐት በእልልታ ዐረገ ዐረገ በእልልታ (2)
ሞትን ድል አድርጎ የሰራዊት ጌታ ዐረገ ዐረገ በእልልታ (2)
ጴጥሮስኒ
ጴጥሮስኒ ወጳውሎስ ፀንዑ በእምነቶሙ (2)
ወበእምነቶሙ (3) ወረሱ መንግሥተ ሰማያት (2)
ትርጉም፡ ጴጥሮስና ጳውሎስ በእምነታቸው ፀኑ
በእምነታቸው መንግሥተ ሰማያትን ወረሱ
የአብ ፀጋ
የአብ ፀጋ የወልድ ቸርነት የመንፈስ ቅዱስም አንድነት (2)
ይደር በሁላችን እንድናገኝ ሕይወት(2)
ይቤላ ህፃን ለእሙ
ይቤላ ሕፃን ለእሙ ኢትፍርሂ እም ኢትፍርሂ እም ነበልባለ እሳት(2)
ለአናንያ ወአዛርያ ወሚሳኤል ዘአድኀኖሙ ውእቱ ያድህነነ(2)
ሕፃን እናቱን አላት እናቴ ሆይ አትፍሪ (2) የእሳቱን ነበልባል (2)
አናንያን አዛርያን ሚሳኤልን ያዳናቸው እኛንም ያድነናል (2)
እግዚአብሔር
እግዚአብሔር ብርሃኔና መድኃኒቴ ነው (2)
የሚያስደነግጠኝ የሚያስፈራኝ ማነው( 2) አምላኬ መመኪያየ ነው (2)
ቀዋምያን ለነፍሳት
ቀዋምያን ለነፍሳት እሙንቱ ሊቃናት ዑራኤል ወሩፋኤል(2)
ይትፌነው ለሣህል (2) እም ኀበ ልዑል(2)
ለነፍሳት የቆሙ እነዚህ መላእክት ዑራኤል ወሩፋኤል(2)
ከልዑል ዘንድ ለይቅርታ (2) ይላካሉ ከልዑል (2)
በስመ ዚአከ
በስመ ዚአከ ይትፌስሁ ዮም (2)
ታቦር ወአርሞንዔም (4)
ሃሌ ሉያ ለአብ
ሃሌ ሉያ ለአብ ሃሌ ሉያ ለወልድ ለመንፈስ ቅዱስ (2)
ስላሴ ዋህድ በካህናተ ሰማየ ህብራቲሆሙ (2)