የሐዊረ ሕይወት መርሐ ግብር ከሀገረ ዴንማርክ(ኮፐንሃገን) ወደ ሀገረ ስዊድን (ሉንድ)
ከዴንማርክ ኮፐንሃገን ደብረ ምሕረት ቅዱስ አማኑኤል ቤተ ክርስቲያን በመነሳት ወደ ስዊድን፣ ሉንድ ደብረምጥማቅ ቅድስት ማርያም ቤተክርስቲያን ነሐሴ 16/2013 ዓ.ም (Aug.22/2021) የሐዊረ ሕይወት መርሐ ግብር ተካሄደ።
ሐዊረ ሕይወቱን ያዘጋጅው የዴንማርክ ግንኝነት ጣቢያ ከደ/ም/ቅ/ አማኑኤል እና ከሉንድ ደ/ም/ቅ/ ማርያም ቤ/ንሰበካ ጉባኤያት ጋር በመተባበር ነው። በዚህ መርሐ ግብር ላይ የሁለቱ አብያተ ክርስቲያናት ምእመናን እናበአጎራባች የሚገኙ አጥቢያዎች፣ አጠቃላይ ከ200 በላይ የሚሆኑ ምእመናን ተሳተፈዋል። የሁለቱም አጥቢያዎችአስተዳዳሪ መልአከ ምሕረት ቆሞስ አባ ዘሚካኤል ደሬሳ፥ መጋቤ ሃይማኖት ቀሲስ ኃይለ ማርያም አያሌው እናመልአከ መዊእ ቀሲስ ሃይለ ጊዮርጊስ አሰፋ ተገኝተው ቃለ እግዚአብሔር እና ምክር ሰጥተዋል።
መርሐ ግብሩ እሐድ ጠዋት 06:00 ላይ ከኮፐሃገን ደ/ም/ቅ/አማኑኤል ቤተክርስቲያን በመነሳት ወደ ሉንድ ደ/ም/ቅ/ ማርያም ቤተ ክርስቲያን ተደርጓል። በደብረ ምጥማቅም የኪዳን ጸሎት፥ የቅዳሴ ጸሎት በኋላ የሐዊረ ሕይወቱየመጀመሪያው ክፍል በጸሎተ ወንጌል ተጀምሮ በኮፐንሃገን የተስፋ ምሕረት ሰ/ት/ቤት ዘማሪያን ያሬዳዊዝማሬያት እና የበገና መዝሙር አቅርበዋል።
ከዚያ በማስቀጠል በመልአከ ምሕረት ቆሞስ አባ ዘሚካኤል “ከመረጥኹት፣ጋራ ቃል ኪዳኔን አደረግኹ መዝ88፥3″ በሚል ርእስ ትምህርተ ወንጌል ሰጥተዋል። በማያያዝም የደ/ምጥማቅ ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያንየአጥቢያው ምእመናን ከ30 ዓመታት በላይ ይጠቀሙበት የነበረውን ሕንጻ ኮንትራት፣ ለቀጣይ ለ100 ዓመታትመራዘሙን ምክንያት በማድረግ ሕንጻ ቤተ ክርስቲያኑን ለሰጡት የስዊድን ቤተክርስቲያን እና ላስተባበሩትየሰብካ ጉባኤ አባላት ምስጋና በማቅረብ ሊሠራ ስለታቀደው ደጀ ሰላም ገለጻ ተደርጓል፡፡ ደጀ ሰላሙ በአውሮፓያሉ ምእመናን በፍልሰታና በሌሎች ጊዜያት መጥተው ሱባኤ ሊይዙበት የሚችሉ በመሆኑ እቅዱ እንዲሳካየምእመናን ሁለንተናዊ ትብብር እንዲደረግለት ሰበካ ጉባኤው ጥሪውን አስተላልፏል።
የሐዊረ ሕይወት 2ኛ ክፍል የሆነው ምክረ አበው በመጋቢ ሃይማኖት ቀሲስ ሃይለ ማርያም እና በመልአከ መዊእቀሲስ ሃይለ ጊዮርጊስ አማካኝነት ለ2ሰዓት ያክል ተከናውኗል። በምክረ አበውም ምእመናን ጥሩ ግንዛቤአግኝተውበታል። በተጨማሪም የተስፋ ምሕረት ሰ/ት ተማሪዎች የተለያዪ ሥነ ጹሑፎችን በኅብረት አቅርበዋል።
በመጨረሻም ሰለ ማኅበረ ቅዱሳን ማንነት፥ ሰለአመሠራረቱ እና ስለሚከናውናቸው መንፈሳዊ መርሐ ግብራትከተገለጸ በኋላ፣ ይህን ሐዊረ ሕይወት በማዘጋጀት ለተሳትፉ ባለድርሻ አካላት ሁሉ በእግዚአብሔር ስም ምስጋናበማቅረብ በደ/ም/ቅ/ ማርያም ቤተ ክርስቲያን አውደ ምሕረት ውስጥ የነበረው መርሐ ግብር ተጠናቋል፡፡ ሐዊረሕይወቱ የዴንማርክ ደ/ም/ቅ/ አማኑኤል ቤተ ክርስቲያን አባላት ከሉንድ ደ/ም/ቅ/ማርያም ቤተክርስቲያን ወደኮፐንሃገን ደ/ም/ቅዱስ አማኑኤል ቤተ ክርስቲያን ባደረጉት በዝማሬ የታጀበ የመልስ ጉዞ ተፈጽሟል።