ትንሣኤ
/in ክርስቲያናዊ ሕይወት /by Website Teamበዲ/ን ብሩክ አሸናፊ ሚያዚያ 23 ቀን 2008 ዓ.ም. የጌታችንና የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ትንሣኤ ሲነገር አብሮ የሚነሣው በዕለተ ዓርብ ስለኛ ብሎ የተቀበለው ሞቱ ነው። አባታችን አዳም እና እናታችን ሔዋን በፈጸሙት በደል ምክንያት የሞት ፍርድ ተፈርዶባቸው ሳለ በበደላቸው ንስሐ ገብተው አምላካችንን በመለመናቸው፥ እርሱም የሰው ፍቅር አገብሮት በዕለተ አርብ በመስቀል ላይ ሞቶ ሶስት መዓልት እና ሶስት ሌሊት በከርሰ […]
የጀርመን ንዑስ ማእከል 3ኛውን የሐዊረ ሕይወት መርሐ ግብር አካሔደ
/in ዜና /by Website Teamበጀርመን ን/ማእከል ኅትመትና ኤሌክትሮኒክስ ሚዲያ ክፍል ሚያዚያ 17 ቀን 2008 ዓ.ም. በማኅበረ ቅዱሳን አውሮፓ ማእከል የጀርመን ንዑስ ማእከል 3ኛውን የሐዊረ ሕይወት መርሐ ግብር በጀርመን ክሮፍልባህ ከተማ በሚገኘው ቅዱስ እንጦስ የግብጽ ገዳም ከሚያዝያ 7- 9 ቀን 2008 ዓ.ም አካሔደ። ሚያዝያ 7 ቀን 2008 ዓ.ም የመርሐ ግብሩ የመጀመሪያ ቀን የካርስሩህ ምእራፈ ቅዱሳን አቡነ ተክለ ሃይማኖት እና የክሮንበርግ […]
ኒቆዲሞስ
/in ክርስቲያናዊ ሕይወት /by Website Team፩ መግቢያ በኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሥርዓት መሠረት የእምነቱ ተከታዮች ሁሉ እንዲጾሟቸው መጀመሪያቸውና መጨረሻቸው ተቀምሮ ጊዜና ወቅት ተወስኖላቸው የተደነገጉ ሰባት የዐዋጅ አጽዋማት አሉ። እነዚህም አጽዋማት በሐዋርያት ሲጾሙ የቆዩና ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን በቀኖና መጻሕፍት የአጿጿም ሥርዓታቸውን የሠሩላቸው ናቸው። ከእነዚህም ሰባት አጽዋማት አንዱና ዋናዉ ዐቢይ ጾም ነው። ይህ ጾም ክብር ምሥጋና ይግባዉና ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከተጠመቀ […]
“ኦ ገብር ኄር ወምእመን ዘበውኁድ ምእመነ ኮንከ ዲበ ብዙኅ እሠይመከ” ማቴ. ፳፭፥፳፫።
/in ክርስቲያናዊ ሕይወት /by Website Teamበመ/ር ሳሙኤል ተስፋዬ ሚያዚያ 1 ቀን 2008 ዓ.ም. የዐቢይ ጾም ስድስተኛ ሳምንት ገብር ኄር ይባላል። ገብር ኄር ማለት ታማኝ አገልጋይ ማለት ነው። ስለ ታማኝ አገልጋይ አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዚህ ዓለም ስንኖር ለፈጣሪያችን ያለንን ታማኝነትና የምናገኘውን ዋጋ በመዋዕለ ሥጋዌው አስተምሯል። ቅዱስ ያሬድ ለዜማ መክፈያነት የዐቢይ ጾምን ሳምንታትን ሲከፍል ገብር ኄርን ተጠቅሟልና እኛም ስለ ገብር ኄር ጥቂት […]
ደብረ ዘይት
/in ክርስቲያናዊ ሕይወት /by Website Teamበአባ ዘሚካኤል ደሬሳ መጋቢት 24 ቀን 2008 ዓ.ም. ደብረዘይት የዓቢይ ጾም እኩሌታ ነው ። በእለቱም ስለ ዳግም ምጽአት ይነገራል። ስለ ምጽአት ነቢዩ ዘካርያስ «በዚያን ቀን እግሮቹ በኢየሩሳሌም ትይዩ በምሥራቅ በኩል ባለው በደብረ ዘይት ላይ ይቆማሉ…አምላኬ እግዚአብሔር ከቅዱሳኑ ጋር ይመጣል…አንድ ቀን ይሆናል…. በዚያም ቀን የሕይወት ውኃ ከኢየሩሳሌም ይወጣል፤ እኩሌታው ወደ ምሥራቁ ባሕር እኩሌታውም ወደ ምዕራቡ ባሕር […]
የቤተ ክርስቲያንን አገልግሎት ይደግፉ!
ማስታወቂያ
Nothing Found
Sorry, no posts matched your criteria