ስለ ቅዱስ ፖትርያርኩ ሥርዓተ ቀብር መግለጫ ተሰጠ

የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ፖትርያርክ፣ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ፣ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም፣ ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት፣ የዓለም አብያተ ክርስቲያናት ምክር ቤት ፕሬዚዳንት፣ የዓለም ሃይማኖቶች ለሰላም የክብር ፕሬዚዳንት ሥርዓተ ቀብር በማስመልከት ቅዱስ ሲኖዶስ መግለጫ ሰጠ፡፡

መግለጫውን የሰጡት ብፁዕ አቡነ ሕዝቅኤል የቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤት ዋና ጸሓፊ፣ የከፋ ቤንችና ማጂ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ሲሆኑ በመግለጫቸውም “ቅዱስነታቸው ሐሙስ ነሐሴ 10 ቀን 2004 ዓ.ም. ከንጋቱ 11፡00 ሰዓት ከዚህ ዓለም በሞተ ሥጋ መለየታቸውን በዕለቱ መግለጻችን ይታወቃል፡፡ በቀጣይነትም የቅዱስነታቸውን የቀብር ሥነ ሥርዓት አፈጻጸም ጊዜና ቦታ በተከታታይ የሚገለጽ መሆኑን በሰጠነው ማሳሰቢያ መሠረት የቀብር ሥነሥርዓቱ ሐሙስ ነሐሴ 17 ቀን 2004 ዓ.ም. በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል እንደሚፈጸም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፡፡ እስከዚያው ድረስ ምእመናንና ምእመናት በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት ስብከተ ወንጌል አዳራሽ በመገኘት ሃዘናቸውን መግለጽ የሚችሉ መሆኑን እንገልጻለን” ብለዋል፡፡

ሙሉውን ጽሑፍ የማኅበረ ቅዱሳን ዋና ማእከል ድረ ገጽ ላይ ለማንበብ ይህን ይጫኑ

 


ከቅዱስ ፓትርያርኩ እረፍት ጋር የተያያዙም ሆነ ሌሎች የቤተ ክርስቲያን ዜናዎችን ለማንበብ ዜና በሚለው አምዳችን ስር “ከዋናው ማእከል” የሚለውን “ሜኑ” መምረጥና የዋናው ማእከል ድረ ገጽ ላይ ያሉ ጽሁፎችን በቀጥታ ማንበብ ይችላሉ።