• እንኳን በደኅና መጡ !

በጀርመን የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት ተመሰረተ።

በጀርመን ን/ማእከል  ጥር  13 ቀን 2010 ዓ.ም. በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን በም/ም/ደ/አውሮፓ ሀገረ ስብከት የሰ/ት/ቤ/ማ/መምሪያ አስተባባሪነት በጀርመን የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት ተመሰረተ። በሀገረ ስብከቱ የሰ/ት/ቤ/ማ/መምሪያ ኃላፊ መልአከ ኃይል አባ ዘድንግል አስተባባሪነት ከሰ/ት/ቤቶች አመራሮች ጋር በተካሄደው የመነሻ ስብሰባ የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት ለመመስረት የሚያስችሉ የተለያዩ ሥራዎችን የሚያከናውን አምስት አባላት ያሉት ኮሚቴ የተመረጠ ሲሆን የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት […]

በዓለ ልደቱ ለእግዚእነ ወአምላክነ ወመድኃኒነ ኢየሱስ ክርስቶስ

በበኩረ ፍሥሐ ቀሲስ ኃይለኢየሱስ ተመስገን ታኅሣሥ 28 ቀን 2010 ዓ.ም. “እስመ ናሁ እዜንወክሙ ዓቢየ ዜና ዘይከውን ፍሥሐ ለክሙ ወለኩሉ ሕዝብ “ሉቃ ፪ ፥፲ ለወልደ እግዚአብሔር ሁለት ልደታት እንዳሉት እናምን ዘንድ ይገባናል። አንዱ ከዘመን ሁሉ አስቀድሞ ከእግዚአብሔር አብ የተወለደው ልደት ነው። ሁለተኛውም ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም በኋላ ዘመን የተወለደው ልደት ነው፡፡ሃይማኖተ አበው ዘባስልዮስ ምዕራፍ ፴፬ ቁጥር ፮ […]

በአውሮፓ የሕፃናት እና ታዳጊዎች ሥርዓተ ትምህርት ተመረቀ

በእንግሊዝ ንዑስ ማእከል ኅዳር 13 ቀን 2010 ዓ.ም. በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሰ/ት/ቤ/ማ/መ/ ማኅበረ ቅዱሳን አውሮፓ ማእከል የተተኪ ትውልድ ሥልጠና ክፍል አስተባባሪነት የተዘጋጀ ከኢትዮጵያ ውጪ የሚኖሩ ሕፃናት እና ታዳጊዎችን ለማስተማር የሚያግዝ ሥርዓተ ትምህርት በእንግሊዝ አገር በለንደን ከተማ በደብረ ገነት ቅድስት ሥላሴ ቤተ ክርስቲያን ኅዳር ፫ ቀን ፳፻፲ ዓ.ም ተመረቀ፡፡

በጀርመን ኑረንበርግ ዐውደ ርእይ እና የስብከተ ወንጌል መርሐግብር ተካሄደ

በጀርመን ንዑስ ማእከል ጥቅምት 20 ቀን 2010 ዓ.ም. በደቡባዊቷ የጀርመን ከተማ ኑረንበርግ ጥቅምት 11 እና 12፣ 2010 ዓ.ም “አብረን እንሥራ ለውጥ እናመጣለን” በሚል መሪ ቃል የዐውደ ርእይ እና የስብከተ ወንጌል መርሐግብር ተካሄደ። ይህንን በማኅበረ ቅዱሳን የአውሮፓ ማእከል  የጀርመን ንዑስ ማእከል ከኑረንበርግ ቅድስት ሥላሴ ቤተ ክርስቲያን ሰበካ ጉባኤ ጋር በመተባበር ያዘጋጀውን ፍኖተ ቤተከርስቲያን፣ ገዳማት እና የአብነት ትምህርት ቤቶች […]

“ወይንሳዕ መስቀለ ሞቱ ወይትልወኒ – የሞቱን መስቀል ተሸክሞ ይከተለኝ”

በዲ/ን ዶ/ር ቴዎድሮስ በለጠ መስከረም 16 ቀን 2010 ዓ.ም. ለስም አጠራሩ ክብር ይግባውና በቃል መነገሩ፣ በኅሊና መዘከሩ፣ በሰው ልብ መታሰቡ፣ በቅዱሳት መጻሕፍት መዘገቡ ከፍ ይበልና፣ ጌታችንንና አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እኛ ልጆቹ ፈቃዱን እያደረግን እንድንኖርና እርሱም ከመልካም ምግባራችንና ከበጎ ትሩፋታችን ብቻ የተነሳ ፍጹማን እንደማንሆን ያውቃልና፣ ከማያልቅ ልግስናው ከማይጓደል ምሕረቱ ዘመናትን እየመጸወተን ደስ የሚሰኝበትን ለእኛ እያደረገ […]


ይህን በመጫን ይለግሱ

የቤተ ክርስቲያንን አገልግሎት ይደግፉ!



የስብከተ ወንጌል ማስፋፊያ  


ገዳማትና አብነት ት/ቤቶች 


የቴሌቪዥን እና ራዲዮ አገልግሎት 

ማስታወቂያ

Nothing Found

Sorry, no posts matched your criteria

©2019. Mahibere Kidusan Europe Center - All Rights Reserved. Website by MK-IT