• እንኳን በደኅና መጡ !

ሀገረ ስብከቱ የመጀመርያውን ሥልጠና ሰጠ

በጀርመን ቀጣና ማዕከል መጋቢት 4 ቀን 2007 ዓ.ም. በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የደቡብ፣ ደቡብ ምሥራቅና ደቡብ ምዕራብ አውሮፓ ሀገረ ስብከት በአይነቱ ልዩ የሆነ እና የሰበካ ጉባዔ አባላትን አቅም ለማሳደግ የታለመ ሥልጠና በሀገረ ጀርመን በፍራንክፈርት ዙርያ የሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ መቀመጫ በሆነው በሩሰልስሀይም ከተማ የካቲት ፳፰ ቀን ፳፻፯ዓ.ም ሰጠ:: የሥልጠና መርሐግብሩን በጸሎትና በቡራኬ የከፈቱት ብፁዕ አቡኑ […]

የልጆች አስተዳደግ በውጭው ዓለም*

በላቸው ጨከነ (ዶ/ር) የካቲት 9 ቀን 2007 ዓ.ም. ልጆች ”ብዙ ተባዙ” በሚለው አምላካዊ ቃል መሠረት ከእግዚአብሔር የሚገኘ በረከቶች ናቸው። ቅዱስ ዳዊት “ልጆች የእግዚአብሔር ስጦታዎች ናችው”(መዝ ፻፳፮፥፫) እንዳለ። ቅዱሳን ፣ ጻድቃን፣ ጳጳሳት ፣ ካህናት፣ ነገሥታት እና መሣፍንት የሚገኙት ከዚሁ አምላካዊ በረከት ነው። በአለንበት ዘመን የአኗኗር ዘይቤ መቀየር ፣ የኑሮ ጫና እና የዓለም መቀራረብ የልጆችን አስተዳደግ ለሁሉም […]

ጾመ ነነዌ

ኤርምያስ ልዑለቃል (ዶ/ር) ጥር 26 ቀን 2007 ዓ.ም.  “የነነዌ ሰዎች በፍርድ ቀን ከዚህ ትውልድ ጋር ተነስተው ይፈርዳሉ ፤ በዮናስ ስብከት ንስሐ ገብተዋልና፡፡” (ማቴ ፲፪፥፵፩) ይህንን የተናገረው ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው፡፡ ጌታችን ለዚህ ትምህርቱ መነሻ ያደረገው የጻፎችን እና የፈሪሳውያንን ጥያቄ ነው፡፡ “መምህር ሆይ ከአንተ ምልክት ልናይ እንወዳለን” ቢሉት “ክፉና አመንዝራ ትውልድ ምልክት ይሻል ፤ ከነቢዩም […]

ጥምቀት እና በዓለ ጥምቀት

በዲ.ን ዶ.ር አለማየሁ ኢሳይያስ ጥር 8 ቀን 2007 ዓ.ም. ጥምቀት ጥምቀት የሚለው ቃል አጥመቀ (አጠመቀ ወይም ነከረ) ከሚለው የግእዝ ሥርወ ቃል የተገኘ ሲሆን ትርጉሙም መጠመቅ ፣ መነከር ፣ መደፈቅ ፣ ውኃ ውስጥ ብቅ ጥልቅ ማለት ነው ። ጥምቀት ከሌሎቹ ምሥጢራተ ቤተክርስቲያን በመጀመሪያ ላይ የሚፈጸም ምሥጢር ሲሆን ያለ ጥምቀት ከሌሎቹ ምሥጢራተ ቤተክርስቲያን መሳተፍ አይቻልም ። (ዮሐ. […]

የጥምቀት በዓል በለንደን እና በሊቨርፑል ከተሞች በአንድነት ይከበራል

በዩኬ ቀጠና ማዕከል ጥር 5 ቀን 2007 ዓ.ም. የ፪፻፯ ዓ.ም የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ የጥምቀት በዓል በታላቋ ብሪታኒያ በለንደን እና በሊቨርፑል ከተሞች በህብረት ይከበራል። በዓሉ በሰሜን ምዕራብ አውሮፓ ሀገረ ስብከት አዘጋጅነት ጥር ፲ እና ፲፩ ቀን ፪፻፯ ዓ.ም በለንደን ደብረ ጽዮን ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን እንዲሁም ጥር ፲፭ እና ፲፮ ቀን ፪፻፯ ዓ.ም በሰሜን ምዕራብ […]


ይህን በመጫን ይለግሱ

የቤተ ክርስቲያንን አገልግሎት ይደግፉ!



የስብከተ ወንጌል ማስፋፊያ  


ገዳማትና አብነት ት/ቤቶች 


የቴሌቪዥን እና ራዲዮ አገልግሎት 

ማስታወቂያ

Nothing Found

Sorry, no posts matched your criteria

©2019. Mahibere Kidusan Europe Center - All Rights Reserved. Website by MK-IT