«የልጆች አስተዳደግ በዚህ ዘመን ተግዳሮቶቹ እና መፍትሔዎቹ» የሚል አዲስ መጽሐፍ በለንደን ተመረቀ

ሐምሌ 8 ቀን 2006 ዓ.ም. 

በአዲስ አበባ መምህርት በሆኑት / ፈሰሴ /ሃና እና በአውሮፓ ማእከል የዩኬ /ማእከል አባልና በታዳሽ ኃይል (Renewable energy ) ተመራማሪ  በሆኑት / በላቸው ጨከነ የተዘጋጀ አዲስ መጽሐፍ  ግንቦት  ፻፮ .. (18 May 2014) የሰሜን ምዕራብ አውሮፓ /ስብከት ስራ አስኪያጅ /አእላፍ ተወልደ ገብሩ እና ጥሪ የተደረጋላቸው እንግዶች በተገኙበት በታላቅ ድምቀት በለንደን ተመረቀ::

 

የመጽሐፉን አጠቃላይ ዓላማ በተመለከተ / በላቸው በዕለቱ ለተገኙት ታዳሚዎች ሲገልጹባለንበት ዘመን የአኗኗር ዘይቤ መቀየር፣ የኑሮ ጫና፣ የዓለም መቀራረብ በአሁኑ ወቅት የልጆችን አስተዳደግ ለሁሉም ወላጅ ለማለት በሚያስደፍር መልኩ ከባድ አድርጎታል። በተለይ ከኢትዮጵያ ውጪ ያለን ወላጆች ለሀገሩ ባህል እና ሕግ እንግዳነት፣ ከቤተ ዘመድ መራቃችን፣ የስራ ጫና፣ የጊዜ እጥረት እና የዓለም ነጋዴዎች ለልጆች የሚያቀርቡት ተለዋዋጭ ሸቀጥ የልጅ አስተዳደግን የበለጠ ውስብስብ አድርጎብናል። ይህን ችግር በመረዳት በኢትዮጵያም ሆነ ከኢትዮጵያ ውጪ ያሉ ወላጆች እንደ መርጃ እንዲያገለግላቸው፣ ለልጆቻቸው የሚያደርጉትን ነገር ሁሉ በሙሉ ልብ  እንዲያደርጉ እና ሳይንሳዊ መንገዶችን ከኢትዮጵያዊ ዕሴቶች ጋር በማጣመር እንዲጓዙ የልጆች አስተዳደግ በዚህ ዘመን ተግዳሮቶቹ እና መፍትሔዎቹ የሚለውን መጽሐፍ ለማዘጋጀት አስብን።በማለት መጽሐፉን ለማዘጋጀት ከአራት አመት በፊት እንደጀመሩት ገልጸዋል።

book cover dr belachew

መጽሐፉ በኢትዮጵያም ሆነ ከኢትዮጵያ ውጪ ያሉ ወላጆች በአሁኑ ወቅት በልጅ አስተዳደግ ያሉባቸውን ተግዳሮቶች በመዘርዘር መፍትሔዎችን ይጠቁማል። መጽሐፉ በልጆች አስተዳደግ ዙሪያ የተጻፉ መጻሕፍት እና የጥናት ወረቀቶች ከተዳሰሱ በኋላ መሠረታዊ ንድፈ ኃሳቦች በማስቀመጥ በመጠይቅ፣ በቃለ መጠይቅ እና በጋራ ውይይት ከልጆች፣ ከወላጆች እና የሥነ ልቦና ባለሞያዎች የተሰበሰቡ መረጃዎችን በመተንተን እና ተሞክሮዎችን በየምዕራፉ በማስቀመጥ የተዘጋጀ ነው።

በዕለቱምየልጆች ባሕርያት ከጽንሰት እስከ ወጣትነት እና የወላጆች ድርሻበውጪ ያሉ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን በልጆች አስተዳደግ ያሉባቸው ችግሮች እና መፍትሔዎችእና  “የዘመኑንቴክኖሎጂ (internet, phone, television, tablets,..) ለልጆቼ እንዴት ልጠቀም?” በሚሉና ከመጽሐፉ ውስጥ በተመረጡ ርዕሶች  ላይ በዩኬ በሚገኙ አንጋፋና ወጣት ምሁራን ሰፊ ገለጻና ውይይት ተካሂዷል።

ከገለጻው በኋላም ከእድምተኞች የተለያዩ ጥያቄዎችና አስተያየቶች ቀርበው ከተናጋሪዎቹ  መልስ እና ማብራሪያ ተሰጥቶባቸዋል። ይህ ትውልድ የማትረፍ ስራ በመሆኑ ተመሳሳይ ውይይቶች በተለያዩ ቦታዎች እና የእምነት ተቋማት መቀጠል እንዳለበት በመጽሐፍ ምረቃው ተሳታፊዎች ተደጋግሞ ተገልጿል:: ፈረሃ እግዚአብሔር ያለው እና በማንነቱ የሚኮራ ትውልድ ለማፍራት ከወላጆች ከቅድስት ቤተክርስቲያንና ከሚመለከታቸው ሁሉ ያላሰለስና ዘመኑን የዋጀ ጥረት ማድረግ እንደሚጠበቅ ያመላከተ ውይይቱ ነበር:: የደ/ገነት ቅድስት ሥላሴ ቤተ ክርስቲያን አስተዳዳሪ የሆኑት /ገነት ከፍያለው አስቻለው መጽሐፉን አስቀድመው ማንበባቸውን እና አጥቢያ ቤተክርስቲያናቸው በህጻናት ዙሪያ እየሰራች ላለችው ስራ ጥሩ መርጃ እንደሚሆን ጠቅሰው የመጽሐፉን ደራሲዎች አመስግነዋል።

አዘጋጆቸ ከዚህ በፊት የአማርኛ ቋንቋ እና የኢትዮጵያ እሴቶችን ለልጆች የሚያስተምር ዲቪዲ ለእንግሊዝኛ፣ ለፈረንሳይኛ እና ለጀርመንኛ ተናጋሪዎች አዘጋጅተው አበርክተዋል።