የአውሮፓ ማእከል 14ኛ ጠቅላላ ጉባኤ ተካሄደ

በአውሮፓ ማዕከል የብዙኀን መገናኛ እና ቴክኖሎጂ አገልግሎት ክፍል

ሐምሌ 18 ቀን 2006 ..

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ማኅበረ ቅዱሳን አውሮፓ ማእከል 14 ጠቅላላ ጉባኤውን ከሐምሌ 11 እስከ 14 ቀን 2006 .. በኢጣልያ ዋና ማእከል ሮሜ ከተማ አካሄደ።

በጉባኤው በአውሮፓ ልዩ ልዩ ሀገራት የሚገኙ ከሰማንያ በላይ አባላት፤ ከዋናው ማእከልና ከሰሜን አሜሪካ ማእከል የተላኩ ልዑካን እንዲሁም በሮሜ ከተማ ነዋሪ የሆኑ ምእመናን ተሳትፈውበታል።

አርብ ሐምሌ 11 ቀን ከምሽቱ 12:00 ሰዓት ጀምሮ ህጽበተ እግር ተካሂዶ መርሐ ግብሩ በጸሎት ከተከፈተ በኋላ የማእከሉ ሰብሳቢ / ሰሎሞን አስረስ የእኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል። ከዚህ በመቀጠልበለቅሶ የሚዘሩ በደስታ ያጭዳሉ በሚል ርዕስ ትምህርተ ወንጌል በመምህር ሚሥጢረ ስላሴ ማናዬ ከተሰጠ በኋላ የጉባኤው ተሳትፊዎች የእርስ በርስ ትውውቅ ተካሂዶ የአርቡ መርሐ ግብር በጸሎት ተፈጽሟል።

ቅዳሜ ሐምሌ 12 ቀን ጠዋት መርሐ ግብሩ በጸሎተ ወንጌል ከተፈተ በኋላ ነገ በሚሆነው አትመካ፤ ቀን የሚያመጣውን አታውቅምናበሚል ርዕስ በመምህር ሚሥጢረ ስላሴ ትምህርተ ወንጌል ተሰጥቷል።  ከዚህ ቀጥሎም 2006 .. የአገልግሎት ዘመን የእቅድ ክንውን ሪፖርት ቀርቦ ሰፊ ውይይት ተደርጎበታል። 

2006 ECበውይይቱም በዚህ የአገልግሎት ዘመን ማእከሉ የነበሩትን ጠንካራ ጎኖች አጠናክሮ እንዲቀጥልባቸው፤ በዚህ ዓመት ታቅደው ያልተከናወኑ ወይም ከእቅድ በታች የተከናወኑትን ደግሞ በሚቀጥለው ዓመት  አጠናክሮ እንዲፈጽማቸው ጉባኤው ውሳኔ አሳልፏል። 

የቅዳሜ ከሰዓቱ መርሐ ግብር አሐዱ የተባለው ጉባኤው የተካሄደባትን ሮሜ ባገናዘበው የማእከሉ መዘምራን ወረብ ነበር። መዘምራኑወእምዝ መሃሩ ወአስምዑ ቃለ እግዚአብሔር፤ ውስተ ብሔረ ሮም መርሖሙ መርሖሙ እግዚአብሔር – “ወደ ሮም አገር እግዚአብሔር መርቷቸዋልና፤ በዚያም የእግዚአብሔርን ቃል አሰምተው አስተማሩ።የሚለውን ወረብ ለጉባኤው አቅርበዋል። ወረቡን ተከትሎ የማኅበሩ አገልግሎት በአኀጉሩ በሚፋጠንበት ዙሪያ አጠር ያለ ገለጻ ቀርቦ አባላቱ በቡድን በቡድን በመሆን ውይይት አድርገውበታል። በውይይቱ የተነሱ ሃሳቦችንም የቡድን ተወካዮች ለጉባኤው አቅርበዋል፤ የትኩረት አቅጣጫዎችም ተለይተዋል። 

ከዚህ በመቀጠል በቅዱሳት መካናት ልማት እና ማሕበራዊ አገልግሎት የቦርድ ጸሐፊ በአቶ ምትኩ ዘለቀበገዳማት ልማትና የአብነት /ቤቶች ድጋፍ የአውሮፓ ማእከል ድርሻበየሚል ርዕስ ስለገዳማትና አብነት /ቤቶች ሰፊ ገለጻ ተደርጓል። በገለጻው ላይም የተተገብሩ ፕሮጀክቶች ሪፖርትና 2006 .. የታቀዱና እየተተገበሩ ያሉ ፕሮጀክቶች ዘገባ ለጉባኤው ቀርቧል። የጉባኤው ተሳታፊዎችም የተለያዩ ጥያቄዎችን አንስተው በአቶ ምትኩ እና በቅስቀሳ እና ገቢ አሰባሳቢ ክፍል ኃላፊው በዲ/ ደረጀ ግርማ ምላሽ ተሰጥቶባቸዋል። ገለጻውን ያካሂዱት ወንድሞች አውሮፓ ማእከል እያደረገው ያለው ድጋፍ አበረታች መሆኑን ገልጸው ወደፊትም ከዚህ የበለጠ አጠናክሮ እንዲቀጥልበት አሳስበዋል።

Dn Mershaቅዳሜ ምሽት ላይ የዋናው ማእከል ልዑክ / / መርሻ አለኸኝ የቤተ ክርስቲያን አገልግሎታችን ወቅቱን ያገናዘበ እንዲሆን ልንከተላቸው የሚገቡ ሥልቶች ላይ ያተኮረ ሰፊ ገለጻ ሰጥተዋል። ከዚህ በመቀጠልም የሰሜን አሜሪካ ማእከል ልዑክ /ጽዮን ቀሲስ በላቸው ወርቁ ሰፊ የአገልግሎት ልምዳቸውን እና ምክራቸውን ለታዳሚው አካፍለው የእለተ ቅዳሜ መርሐ ግብር በጸሎት ተፈጽሟል። 

ከጸሎተ ቅዳሴ መልስ የእለተ እሑድ መርሐ ግብር የቀጠለ ሲሆን፤ በመጀመሪያ 2007 .. የአገልግሎት ዘመን እቅድ በጀት ቀርቦ ሰፊ ውይይት ተደርጎበት በጉባኤው ጸድቋል። ለእቅዱ መሳካትም የዋናው ማእከል እና የአሜሪካ ማእከል ልዑካን ሁሉም አባላት ተግተው እንዲያገለግሉ ያሳሰቡ ሲሆን፣ አባላቱም ለእቅዱ ተፈጻሚነት የየድርሻቸውን እንደሚወጡ ቃል ገብተዋል። እንዲሁም የማእከሉ አገልግሎት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየሰፋ በመምጣቱ ማእከሉ የሙሉ ጊዜ ጸሐፊ እንደሚያስፈልገው የተገለጸ ሲሆን ለዚህም መሳካት አባላት እና ሌሎችም ባለድርሻ አካላት የየበኩላቸውን አስተዋጽኦ እንዲያበረክቱ የሥራ አስፈጻሚ ጉባኤው ሃሳቡን አቅርቦ፤ ጉባኤውም ውይይት ካደረገ በኋላ በሙሉ ድምጽ ሃሳቡን ተቀብሎ አጽድቆታል።

በመርሐ ግብሩ ላይ በልዩ ልዩ ምክንያት ከሀገራቸው ተሰደው ያሉ ኢትዮጵያውያን ሊደረግላቸው ስለሚገባው መንፈሳዊ እርዳታ ጉባኤው በሰፊው መክሯል። ከዚህ በማስከተል በማኅበሩ መተዳደሪያ ደንብ መሠረት የአገልግሎት ዘመኑን የፈጸመውን የማእከሉን ሥራ አስፈጻሚ በአዲስ ተክቷል

በእሑድ ምሽት መርሐ ግብር ላይም የዋናው ማእከል መልዕክት በተወካዩ በዲ/ / መርሻ አለኸኝ ለጉባኤው ቀርቧል። በማኅበሩ የተፈጸሙ አገልግሎቶች እና እየተተገብሩ ያሉ የገዳማት እና አብነት /ቤቶች ፕሮጀክቶች፣ የስብከተ ወንጌል ማሥፋፊያ ፕሮግራም እንዲሁም በመስፋፋት ላይ ያለው የማኅበሩ የቴሌቭዥን እና ሬዲዮ ስርጭት በመልዕክቱ ተዳሰዋል። የአውሮፓ ማእከል ገዳማት እና አብነት /ቤቶችን በመደገፍ በኩል ላበረከተው ጉልህ አስተዋጽኦ በምሥ/ጎጃም ሀገረ ስብከት ከሞጣ ደብረ ገነት /ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን የምሥክር ወረቀት እና ስጦታ ተበርክቶለታል። የሞጣ ///ጊዮርጊስ የላይ ቤት ትርጓሜ ትምህርት ቤት ከአውሮፓ ማዕከል በተደረገ ላቅ ያለ ድጋፍ ግንባታው ተጠናቆ በቅርቡ ርክክብ መደረጉ ይታወሳል።

በዋናው ማእከል መልዕክት እንደተገለጸው ማኀበሩ 46 ማእከላት በሀገር ውስጥ፣ 4 ማእከላት እና 10 ግንኙነት ጣቢያዎች ከሀገር ውጪ እንዲሁም 340 በላይ ግቢ ጉባኤያት አሉት።

MT K Belachewበመጨረሻም የሰሜን አሜሪካ ማእከል ተወካይ //ቀሲስ በላቸው ወርቁ ሁሉቱ ማእከላት አብረው በጋራ ሊተገብሯቸው ስለሚችሉ የአገልግሎት ዘርፎች እና ሊለዋወጧቸው ስለሚገቡ ልምዶችና ተሞክሮዎች ሰፊ ገለጻ አድርገዋል።

በጉባኤው ማጠቃለያ እንደተገለጠው የዘንድሮው ጠቅላላ ጉባኤ በእጅጉ የተሳካ እና በማእከሉ የጠቅላላ ጉባኤ ታሪክ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ተሳታፊ የተገኘበት ሲሆን ዝግጅቱም በአግባቡ የተከናወነ እንደ ነበር የማእከሉ ሰብሳቢ / ሰሎሞን አስረስ ገልጸዋል።Dn Solomon

እንደ ሰብሳቢው ገለጻጉባኤው የማእከሉን አገልግሎት በሚያጠናክሩና አባላት በያሉበት ኾነው በቤተ ክርስቲያን አገልግሎት ላይ ሊያደርጉት ስለሚገባው ተግባራዊ ሱታፌ እንዲወያዩ በማሰብ የተተለመ ነበር። አባለት በቀረቡላቸው የመወያያ ርእሰ ጉዳዮች ዙሪያ ጠቃሚ ውይይት በማድረግ ያሳለለፏቸው ውሳኔዎች ተግባራዊ እንዲኾኑ ክትትል ይደረጋልብለዋል።

በጉባኤው አዘጋጅ ኮሚቴ በተያዘለት መርሐ ግብር መሠረት የጉባኤው ታዲሚዎች ሰኞ ሐምሌ 14 ቀን ቅዱሳን ሐዋርያት ቅዱስ ጴጥሮስ እና ቅዱስ ጳውሎስ ሰማእትነት የተቀበሉባቸውን ስፍራዎች ጨምሮ ሌሎችንም በጥንታዊቷ የሮሜ ከተማ የሚገኙ ታሪካዊ ቦታዎችን ጎብኝተዋል።

GA 2006 Participants

ቀጣዩ 15 የማእከሉ ጠቅላላ ጉባኤ በፊንላንድ ዋና ከተማ ሄልሲንኪ እንዲከናወን ተወስኗል።

ወስብሐት ለእግዚአብሔር