የጌታችን ትንሣኤ

ማርያም ግን እያለቀሰች መቃብሩ አጠገብ ቆመች፡፡ ስታለቅስም ሁለት መላእክት ነጭ ልብስ ለብሰው የጌታ ሥጋ በነበረበት ቦታ አንዱ በግርጌ አንዱ በራስጌ ተቀምጠዉ አየች፡፡ እነርሱም “አንቺ ሴት ስለምን ታለቅሻለሽ?” አሏት፡፡ እርሷም “ጌታዬን ከመቃብር ወስደውታል ወዴትም እንዳኖሩት አላውቅም አለቻቸው።” ይኸን ብላ ዞር ስትል ጌታችንን ቆሞ አየችው፤ ነገር ግን እርሱ እንደሆነ አላወቀችም ነበር። ጌታችንም “አንቺ ሴት ስለምን ታለቅሻለሽ? ማንንስ ትፈልጊያለሽ? አላት” እርሷም የአትክልት ቦታ ጠባቂ መስሏት “ጌታ ሆይ አንተ ወስደኸው እንደሆን ወዴት እንዳኖርኸው ንገረኝ እኔም እወስደዋለሁ” አለችው። ጌታችንም ማርያም ብሎ ጠራት እርሷም መምህር ሆይ ብላ መለሰችለት፤ ጌታችን ከሙታን በመነሣቱ እጅግ በጣም ደስ እያላት ለነ ቅዱስ ጴጥሮስ ልትነግራቸው ሄደች።

ልጆች እኛም ልክ እንደ መግደላዊት ማርያም አምላካችንን የምንወድና ትንሣኤዉን የምናምን ከሆነ ሕይወታችን በደስታ የተሞላ ይሆናል። እኛም እንደ መግደላዊት ማርያም በደስታ የጌታችንን ትንሣኤ እንድናከብር ስለፈቀደልን እግዚአብሔር የተመሰገነ ይሁን።

ልጆች ደህና ሰንብቱ!