የደብረ መዊ ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያ ቅዳሴ ቤቱ ተከበረ

በአውሮፓ ማእከል ኅ/ኤ/ሚ ክፍል

መስከረም 9 ቀን 2009 ዓ.ም

በስዊድን ሉንድ ከተማ የደብረ መዊ ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያ በብፁዕ አቡነ ሙሴ የደ/ም/ም እና የሰሜን ምዕራብ አውሮፓ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ነሐሴ 29 ቀን 2008 ዓ.ም. ታቦተ ህጉ ተባርኮ ቅዳሴ ቤቱ ተከብሯል።

14205986_1069889456435877_5576623531079840071_o 14232022_1069885853102904_8227531442228237185_o

በበዓሉ ላይ ከኢትዮጵያ፣ከተለያዩ የአውሮፓ ሃገራትንና  ከስዊድን ካህናት አባቶች እና ዲያቆናት ወንድሞች የተገኙ ሲሆን በዕለቱ ብፁዕ አቡነ ሙሴ ባስተላለፉት መልዕክት ቤተክርንስቲያን መክፈት ትልቅ ጉልበትና ትጋትን የሚጠይቅ ቢሆንም ቤተክርስቲያኑን መጠበቅና ማሳዳግ የበለጠ ፀሎትና ትጋት የሚያስፈልገው መሆኑን አሳስበዋል። አያይዘውም ቤተክርስቲያኑን በነፃ ለሰጡት አካላት ምስጋና አቅርበዋል።

በአከባቢው የሚገኙ ምእመናን የ ቤተክርስቲያኑን አገልግሎት ላማስጀመር ለአንድ ዓመት በፀሎት፣ነዋየ ቅድሳትና ሌሎች ለ ቤ/ክ የሚያስፈልጉ ነገሮችን በማሟላት የቆዩ ሲሆን የእግዚአብሔር ፈቃድ ሆኖ ጥረታቸው ከፍፃሜ ደርሷል።

ይህ የደብረ መዊ ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያ በስዊድን ሀገር የሚገኙትን የኢ/ኦ/ተ አብያተ ክርስቲያናትን ቁጥር ወደ 3 አሳድጉአል።