አቤልና ቃየል (ለልጆች) (ዘፍ.4፣1-15)

 

በአውሮፓ ማዕከል ትም/ እና ሐዋሪያዊ አገልግሎት ክፍል

ጥቅምት 19 ቀን 2006 ዓ.ም. 

አዳም እና ሔዋን በመጀመሪያ ቃየልን እና አቤልን ወለዱ። አቤልም በግ ጠባቂ ነበረ፤ ቃየል ምድርን የሚያርስ ነበረ። ሁለቱም ካላቸው ነገር ለእግዚአብሔር ስጦታ ወይም መሥዋዕት አቀረቡ። ቃየል ክፉ ልብ ነበረውና እግዚአብሔር አይበላው ብሎ ከአመረተው እህል ጥሩዉን ሳይሆን መጥፎዉ የማይረባውን መናኛውን እህል ለእግዚአብሔር መሥዋዕት አቀረበ። አቤል ልቡ ንፁህ ነበርና እግዚአብሔር ንጹሐ ባህርይ ማለት ነው ሲል ያላረጀውን በግ ፣ ጥርሱ ያልዘረዘረውን ንጹህ የአንድ አመት ጠቦት በግ ለእግዚአብሔር ንፁህ መሥዋዕት አቀረበ።

ልጆች እግዚአብሔር ጥሩ ሥራን ስለሚወድ ወደ አቤልና ወደ መሥዋዕቱ ተመለከተ። ነገር ግን ቃየል ጥሩ ሥራ ስላልሰራ ወደ ቃየልና ወደ መሥዋዕቱ አልተመለከተም። በዚህም ምክንያት ቃየል እጅግ ተናደደ ፊቱም ጠቆረ። እግዚአብሔርም ቃየል አለው ለምን ተናደድህ? ለምንስ ፊትህ ጠቆረ? መልካም ብታደርግ ፊትህ የሚበራ አይደለምን? መልካም ባታደርግ ግን ኃጢአት ንብል፣ ቅጣትም ይጠብቅሃል

ዚህም በኋላ ቃየል ተንኮል ስላሰበ ወንድሙን አቤልን ወደ ሜዳ እንሂድ አለው። በሜዳም ሳሉ   ቃየል ወንድሙ አቤል በደ ገደለው።

እግዚአብሔር ቃየ ተደቆ የሰራውን ስላወቀበት ወንድምህ አቤል ወዴት ነው ጠየቀው። ቃየልም አላውቅም፤ የወንድሜ ጠባቂ እኔ ነኝን? መለሰ። እግዚአብር እንዲህ ብሎ ገሰጸው/ተቆጣው። ምን አደረ? የወንድምህ የደሙ ድምፅፍሱ ከምድር ወደ እኔ ይጮኻል። አንተ የተረገምህ ነህ። በምድርም ላይ ኰብላይና ተቅበዝባዥ ትሆናለህ። ቃየል እግዚአብሔርን አለውኃጢአቴ ልሸከማት የማልችላት ታላቅ ናት። እነሆ ዛሬ ከምድር ፊት አሳደድኸኝ፤ ከፊትህም እሰወራለሁ፤ በምድርም ላይ ኰብላይና ተቅበዝባዥ እሆናለሁ፤ የሚያገኘኝም ሁሉ ይገድለኛል በማለት ተናገረ ቃየልም ቱ ምክንያት ተቅበዝባዥና ኮብላይ ሆነ።

አዳም ና ሔዋን ሌላ ወንድ ልጅን ወለ ስሙንም፦ ቃየ በገደለው በአቤል ፋንታ እግዚአብሔር ሌላ ዘር ተክቶልኛል ሲሉ ስሙን ሴት ው ጠሩ

አጠቃላይ ልጆች እግዚአብሔር መልካም ሥራ እንደሚወድ ከአቤል መማር እንችላለን። በተቃራኒው ከቃየል ደግሞ መልካም ያልሆነ ሥራ ከሰራን እግዚአብሔር ስራችንን እንደማይቀበልና ቅጣትም እንደሚጠብቀን እንማራለን። ስለዚህ እናተም ልጆች ክፉና እግዚአብሔር የማይወደውን ስራ ሳይሆን እንደ አቤል መልካም ስራ መስራት አለባችሁ።.

ልጆች እነዚህን ከታች የተዘረዘሩትን ጥያቄዎች መልሱ፤ 

. በመጀመሪያ አዳምና ሔዋን ማንን ወለዱ ? በመቀጠልስ ማንን ወለዱ?

. የታላቁ ሥራው ምን ነበረ? የታናሽ ወንድሙስ ሥራ ምን ነበር?

. ታላቁ ልጅና ታናሹ ልጅ በልባቸው ምን አሉ? ለእግዚአብሔርን ምን አቀረቡ ?

. እግዚአብሔር የማንን ሀሳብ እና ተግባር መረጠ?

. እግዚአብሔር ታላቁን ልጅ ምን አለው?

. ታላቁ ልጅ ታናሹን ወንድሙን ምን አደረገው ? ከእግዚአብሔር የሚደበቅ/የሚሰወር ነገር አለ?

. እግዚአብሔር ክፉ የሰራውን ሰው ምን አለው?

. በሞተው ልጅ ፋናታ ማን ተወለደ?

 

ወስብሐት ለእግዚአብሔር!!!