• እንኳን በደኅና መጡ !

ማኅበረ ቅዱሳን ማን ነው?

ማኅበረ ቅዱሳን ማን ነው? ምንስ እየሠራ ነው?   የተዛባ አመለካከት የማይጋርደው ገሐድ እውነታ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ሊቃውንት ብራና ዳምጠው፤ ቀለም በጥብጠው፣ ብዕር ቀርጸው በየአብያተ ክርስቲያናቱ የመቃብር ቤቶች ውስጥ በማስተማር ትውልዱ የሀገር መሪ፣ የቤተክርስቲያን አለኝታ፣ የእግዚአብሔር ቅን አገልጋይ እንዲሆን ያበረከቱት አገልግሎት ከዘመን ዘመን እየተሸጋገረ ለትውልድ ሲተላለፍ የኖረና የሚኖር ነው፡፡ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ለሀገራችን ሥልጣኔ […]

የጌታችን ትንሣኤ

ልጆች ስለ ጌታ ከሞት መነሣት ሰምታችሁ ታውቃላችሁ? እስቲ ትንሽ ስለ ትንሣኤው ልንገራችሁ:: ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን አይሁድ ዓርብ ቀን በሐሰት ሰቅለው ከገደሉት በኋላ ዮሴፍና ኒቆዲሞስ ሥጋውን ከመስቀል ላይ አውርደው በንጹህ በፍታ ገንዘው በአትክልት ቦታ በሚገኝ አዲስ መቃብር ውስጥ ቀበሩት። ትልቅ ድንጋይም አንከባለው የመቃብሩን አፍ ዘጉት። በአይሁድ የታዘዙ ብዙ ጭፍሮች (ወታደሮች) የጌታችንን መቃብር ይጠብቁ ነበር። ልጆች፣ […]

ኢትዮጵያዊዉ ጃንደረባ

በዓለም የክርስትና ታሪክ የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ቀዳሚውን ስፍራ የያዘችና ሐዋርያዊት ለመሆንዋ ምስክር ከሚሆኑ ታላላቅ የቤተ ክርስቲያን አባቶች መካከል ባኮስ ቀዳማዊ ነው። ኢትዮጵያውያን ከዘመነ ብሉይ ጀምሮ ሕዝበ እግዚአብሔር ከሚባሉ እስራኤል ጋር በአምልኮተ እግዚአብሔር የሚኖሩ ሕዝብ ስለመሆናቸው ቅዱስ መጽሐፍ ይመሰክራል። አያሌ የታሪክ መዛግብትና የአርኪዮሎጂ ምርምር ውጤቶችም ይህንን እውነት ያረጋግጣሉ። እኛም በዚህ የቅዱሳን ታሪክ ዓምድ፣ ጌታችን አምላካችንና መድኃኒታችን […]

ዕውቀት እንዳይሞት

ቤተ ክርስቲያን ሰማይና ምድር ከመፈጠራቸው በፊት ነበረች። ዓለማት ከተፈጠሩ በኋላ በዓለመ መላእክት፣ በዓለመ መሬት በሕገ ልቡና እና በሕገ ኦሪት እግዚአብሔር በመረጣቸው ነቢያትና ካህናቱ አማካኝነት ሰዎችን ከእግዚአብሔር ጋር ስታገናኝ ኖራለች። በዘመነ ሐዲስ ደግሞ በደመ ክርስቶስ ተዋጅታ ሕገ ወንጌልን ስትናኝ እና አምልኮተ እግዚአብሔርን ስታስፋፋ ኖራለች። በነዚህ አዝማናት ሁሉ ስለ እርሷ ሳይፈሩና ሳያፍሩ አንገታቸውን ለሰይፍ፣ ጀርባቸውን ለግርፋት፣ እግራቸውን […]

ሕይወት በባዕድ ምድር (፪ጴጥ. ፪፥፰)

የርዕሳችን መነሻ የሆነው በ፪ኛ ጴጥሮስ ምዕራፍ ፪ ላይ የምናገኘው ታሪክ ነው። “ጻድቅ ሎጥም እያየና እየሰማ፣ አብሮአቸውም እየኖረ በክፉ ሥራቸው ዕለት ዕለት ጻድቅት ነፍሱን ያስጨንቃት ነበር።” ፪ጴጥ. ፪፥፰ ሎጥ ኃጢአትን የዕለት ከዕለት ተግባራቸው ካደረጉ ሰዎች ጋር ለመኖር የተገደደው በዘፍ ፲፫ ላይ እንደምናነበው ከአጎቱ ከአብርሃም ጋር ይኖርበት የነበረው ቦታ ስለጠበባቸው በእረኞቻቸው መካከልም እየተፈጠረ የነበረው ጥላቻ ወደ እነርሱ […]


ይህን በመጫን ይለግሱ

የቤተ ክርስቲያንን አገልግሎት ይደግፉ!



የስብከተ ወንጌል ማስፋፊያ  


ገዳማትና አብነት ት/ቤቶች 


የቴሌቪዥን እና ራዲዮ አገልግሎት 

ማስታወቂያ

Nothing Found

Sorry, no posts matched your criteria

©2019. Mahibere Kidusan Europe Center - All Rights Reserved. Website by MK-IT