Entries by Website Team

የማኅበረ ቅዱሳን 10ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ

መስከረም 3 ቀን 2004 ዓ.ም. በእንዳለ ደምስስ ሪፖርታዥ የማኅበረ ቅዱሳን 10ኛ ጠቅላላ ጉባኤ በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ስብከተ ወንጌል አዳራሽ ብፁዐን ሊቃነ ጳጳሳት፤ የጠቅላይ ቤተ ክህነት፤ የመምሪያ ሓላፊዎች፤ ቀሳውስትና ካህናት፤ የፌደራል ጉዳዮች የሃይማኖት ተወካዮችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት ነሐሴ 30 ቀን 2004 ዓ.ም.በድምቀት ተጀመረ፡፡ በእንዳለ ደምስስ መስከረም 3 ቀን 2004 ዓ.ም. ሪፖርታዥ የማኅበረ ቅዱሳን […]

ብፁዕነታቸው አዲሱን ዓመት አስመልክቶ ቃለ ምዕዳንና ቡራኬ ሰጡ፡፡

በዲ/ን ዮሴፍ ይኲኖ አምላክ ጳጉሜን 5 ቀን 2004 ዓ.ም. የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ዐቃቤ መንበረ ፓትርያርክና የአርሲ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ናትናኤል ለመላው ኢትዮጵያውያንና ኢትዮጵያውያት ባስተላለፉት መልእክት፡- “የዘመናት ጌታ እግዚአብሔር አምላካችን እንኳን ከዘመነ ዮሐንስ 2004 ዓ.ም. ወደ ዘመነ ማቴዎስ 2005 ዓ.ም. በሰላም አደረሳችሁ፤ ለሚቀጥለውም ዘመን በቸርነቱ ጠብቆ በሰላምና በጤና እንዲያደርሳችሁ ቤተ ክርስቲያናችን […]

የማኅበረ ቅዱሳን 10ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ ተጠናቀቀ

ጉሜን 5 ቀን 2004 ዓ.ም. በእንዳለ ደምስስ ነሐሴ 30 ቀን 2004 ዓ.ም. የተጀመረው የማኅበረ ቅዱሳን መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ በታቀደለትና በወጣለት መርሐ ግብር መሰረት በማካሔድ ጳጉሜን 2 ቀን 2004 ዓ.ም. ከለሊቱ 9፡00 ስዓት በድምቀት ተጠናቀቀ፡፡ ጳጉሜን 2 ቀን 2004 ዓ.ም.  ለሊት በተካሔደው  የጠቅላላ ጉባኤው ቀጣይ ውይይት በቀኑ መርሐ ግብር የአራት ዓመት ስልታዊ እቅድ ረቂቅ ላይ የተካሔደውን […]

ማኅበረ ቅዱሳን የሥራ አመራር ጉባኤ ምርጫ አካሄደ

በእንዳለ ደምስስ ጳጉሜን 2 ቀን 2004 ዓ.ም. ከነሐሴ 30 ቀን 2004 ዓ.ም. ጀምሮ እየተካሄደ የሚገኘው የማኅበረ ቅዱሳን 10ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ በመጠናቀቅ ላይ ነው፡፡ ጳጉሜን 1 ቀን 2004 ዓ.ም. ጠዋት በተካሄደው የጠቅላላ ጉባኤው ስብሰባ “በማኅበረ ቅዱሳን የአገልግሎት ጉዞ የአባላት ተሳትፎና የወደፊት ሁኔታ” በተመለከተ ጥናት የቀረበ ሲሆን በአባላት ሰፋ ያለ ውይይት ተካሂዷል፡፡ ከሰዓት በኋላ በቀጠለው ስብሰባም […]

ቅዱስ ሲኖዶስ ጸሎተ ምህላ እንዲደረግ ወሰነ

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤት ነሐሴ 30/2004 ዓ.ም. ለመገናኛ ብዙኅን በሰጠው መግለጫ ከጳጉሜ 1 ቀን 2004 ዓ.ም. እስከ መስከረም 10/2005 ዓ.ም. ድረስ ምእመናን ለሁለት ሱባኤያት በመላዋ ኢትዮጵያና በውጭ ሀገር በሚገኙ አህጉረ ስብከቶች በሚገኙ ገዳማት፣ አድባራትና አብያተ ክርስቲያናት ጸሎተ ምህላ እንዲደረግ ወስኗል፡፡ ቅዱስ ሲኖዶስ ጸሎተ ምኅላውን ያወጀበት ምክንያት ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ በነበሩበት […]

ቤተ ክርስቲያንና የፓትርያርክ ምርጫ

ነሐሴ 25 ቀን 2004 ዓ.ም. በዲ/ን ብርሃኑ አድማስ ቤተ ክርስቲያን አንዲት፣ ቅድስት፣ ኩላዊትና ሐዋርያዊት መሆኗን ጥንታውያን አብያተ ክርስቲያን ሁሉ ይቀበላሉ፤ በመሠረተ እምነታቸው ውስጥም አካትተው በጸሎትና በአስተምህሮ ይጠቀሙበታል፡፡የዚህ መሠረታዊ ምክንያቱ ደግሞ ከዘመነ ሐዋርያት ጀምሮ ይህ ትምህርት ቢኖርም ነገር ግን መልእክቱን በአግባቡ ካለመረዳት የተነሣ እነ አርዮስና መቅዶንዮስ በትውፊት ከሐዋርያት ጀምሮ የመጣውን የቅዱሳት መጻሕፍት ትርጓሜ መሠረት መቀበልን ቸል […]

“ዘይሁብ መርሐ ርቱዐ ለቤተ ክርስቲያን – ለቤተ ክርስቲያን ቅን መሪ የሚሰጥ”

(ጸሎተ ኪዳን – ዘሠርክ) በዲያቆን ያረጋል አበጋዝ ቤተ ክርስቲያን የምንላት ወልድ ዋሕድ ኢየሱስ ክርስቶስ ከፍጹምና ከማይነገር ፍቅሩ የተነሣ ሰው እስከ መሆን፣ ሰው ሆኖም በዚህ ዓለም ከኃጢአት በስተቀር እንደ ሰው መኖርን፣ ከዚያም በቀራንዮ ቅዱስ ሥጋውን እስኪቆርስላትና ክቡር ደሙን እስኪያፈስላት ድረስ የደረሰላትና የመሠረታት የምእመናን አንድነት (ጉባኤ) ናት። “ወነአምን በአሐቲ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን እንተ ላእለ ኩሉ ጉባኤ ዘሐዋርያት” የምንለው […]

ወቅታዊ ዜናዎች

የብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ ሥርዓተ ቀብር ተፈጸመ የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ቀብር ሥነ ሥርዓት መርሐ ግብር “የኢትዮጵያ መምህሯ እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ነው፡፡” ሕገ ቤተ ክርስቲያን ስለ ቅዱስ ሲኖዶስና ስለ ቅዱስ ፓትርያርክ ምን ይላል? ቅዱስ ሲኖዶስ አቃቤ መንበር ሰየመ ሌሎች ወቅታዊ የቤተ ክርስቲያን ዜናዎችን ለማንበብ “ዜና” በሚለው አምዳችን ሥር “ከዋናው ማእከል“ የሚለውን “ሜኑ” በመምረጥ በዋናው ማእከል ድረ […]

ስለ ቅዱስ ፖትርያርኩ ሥርዓተ ቀብር መግለጫ ተሰጠ

የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ፖትርያርክ፣ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ፣ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም፣ ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት፣ የዓለም አብያተ ክርስቲያናት ምክር ቤት ፕሬዚዳንት፣ የዓለም ሃይማኖቶች ለሰላም የክብር ፕሬዚዳንት ሥርዓተ ቀብር በማስመልከት ቅዱስ ሲኖዶስ መግለጫ ሰጠ፡፡

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ አረፉ

አምስተኛው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ ዶ/ር አቡነ ጳውሎስ ፓትርያርክ፣ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳሳ ዘአክሱም፣ ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት፣ የዓለም አብያተ ክርስቲያናት ፕሬዚዳንት ነሐሴ 10 ቀን 2004 ዓ.ም. ከንጋቱ 11:00 ሰአት ከዚህ ዓለም በሞተ ሥጋ ተለይተዋል። እግዚአብሔር አምላክ የቅዱስነታቸውን ነፍስ በደጋግ አባቶች አቅፍ ውስጥ ያኑርልን፣ አሜን