Entries by Website Team

“እውነት እውነት እልሀለሁ ሰው ከውሃና ከመንፈስ ካልተወለደ በቀር ወደ እግዚአብሔር መንግሥት ሊገባ አይችልም።” ዮሐ ፫፡፭

በይበልጣል ጋሹ ጥር ፲ ቀን ፳፻፭ ዓ.ም. ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመዋዕለ ስጋዌው በምድር በነበረበት ዘመን ከፈጸማቸው እና ለሰው ልጅ ከሰጣቸው ሚስጢራት  አንዱ ጥምቀት ነው። “ጥምቀት” የሚለው ቃል አጥመቀ ከሚለው የግዕዝ ግሥ የተገኘ ሲሆን ትርጉሙም፣ መነከር፣ መዘፈቅ፣ መደፈቅ፣ መላ አካልን በውሃ ውስጥ ማስገባት ማለት ነዉ። በሚስጢራዊ ትርጉም ደግሞ ብዙ ምሳሌዎች አሉት። ከምሳሌዎች መካከልም፦ የአብርሃም ከሃገሩ […]

ሕፃን ተወልደ ለነ ወልድ ተውኅበ ለነ፤ ሕፃን ተወለደልን ወንድ ልጅም ተሰጠን፡፡ ኢሳ 9፣6 (ውዳሴ ማርያም ዘሰኑይ)

ዲ/ን ውብዓለም ደስታ ታኅሣስ ፳፰ ቀን ፳፻፭ ዓ.ም. አዳም ትእዛዘ እግዚአብሔርን ተላልፎ አትብላ የተበለውን ዕፀ በለስ በልቶ በሞተ ሥጋ ሞተ ነፍስ፤ በርደተ መቃብር ርደተ ገሃነም ተፈርዶበት ከገነት ከወጣ በኋላ፤ እግዚአብሔርን ያህል ጌታ፤ ገነትን ታህል ቦታ አጥቼ ቀረሁን እያለ ሲያዝን፤ ጌታ ኀዘኑን አይቶ ልመናውን ሰምቶ ‹‹በኀሙስ እለት ወበመንፈቃ ለእለት እትወለድ እምወለተ ወለትከ፣ ወእትቤዘወከ በመስቀልየ ወበሞትየ፤በአምስት ቀን […]

ቅድስት ወለተ ጴጥሮስ

አባቷ  ባሕር አሰግድ እናቷ  ደግሞ  ክርስቶስ አዕበያ  ይባላሉ። ትውልዷ ከዳሮ /ምስራቅ ኢትዮጵያ/ ወገን ነው። ወንድሞቿ ዮሐንስና ዘድንግል በንጉሥ  ሱስንዮስ ጊዜ ታላላቅ ባለስልጣናት ነበሩ። እናት አባቷ  በህግ በስርዓት ካሳደጓት በኋላ ሥዕለ ክርስቶስ የሚባል የስስኑዮስ የጦር አበጋዝ ቢትወደድ  አግብታ 3 ልጆች መውለድዋን ገድሏ ይናገራል። ይህ ቢትወደድ ይኖርበት የነበረው ግንብ ቤት ፍራሽ እስከ አሁን ድረስ በጋይንት ስማዳ ይታያል።

በስውር የሚያይ አባትህም በግልጥ ይከፍልሃል (ማቴ. 6፣4).

በዲ.ን ኃይሉ ተረፈ ኅዳር 26 ቀን 2005 ዓ.ም. ለስም አጠራሩ ክብር ምስጋና ይግባዉና ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በኅቡዕ በምንፈጽማቸዉ ሥራዎች ሁሉ እዉነተኞች ተጠቃሚዎች እንድንሆን ሥራዎቻችን ሁሉ በእርሱ ዘንድ ሚዛን የሚደፉና የሚታዩ እንዲሆኑ “በስውር የሚያይ አባትህም በግልጥ ይከፍልሃል”  (ማቴ. 6፣4) በማለት ይመክረናል፡፡ እግዚአብሔር ሰዎች ያላዩትን ሁሉ የሚያይ፣ በሰዎች ዘንድ ዋጋ ያልተሰጠዉን እርሱ ግን ዋጋ የሚሰጠዉ፣ ለሁሉም […]

የግቢ ጉባኤያት በእንግሊዝ ፡ ምዝገባ ጀምረናል!

«የግቢ ጉባኤ» ምንድን ነው? ማኅበረ ቅዱሳን ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ከሰጠችው ኃላፊነት አንዱ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ውስጥ መደበኛ ትምህርታቸውን በመማር ላይ የሚገኙ ኦርቶዶክሳውያን ወጣቶች የሚኖራቸውን የተጣበበ ጊዜ እና የአኗኗር ዘይቤያቸውን ያገናዘበ ልዩ መርሐ ግብር በማዘጋጀት መንፈሳዊ ትምህርት እንዲያገኙና በኋላ በሥራ ዓለም ሲሰማሩ በሃይማኖት ጸንተው፣ በምግባር ታንጸው በመገኘት በእውቀታቸው፣ በጉልበታቸውና በገንዘባቸው ቤተ ክርስቲያናቸውን እንዲያገለግሉ ማድረግ ነው። ይህንን […]

ቤተ ክርስቲያንን ጠብቋት

ጥቅምት 6 ቀን 2005 ዓ.ም. አባ ዘሚካኤል ቅድሚያ ለቤተ ክርስቲያን እንቁም! ምን እንደምትልም እንጠብቃት (እንስማት)! “ወይእዜኒ ዕቀቡ ርእሰክሙ ዘሎቱ ሤመክሙ መንፈስ ቅዱስ ጳጳሳተ ከመ ትርአዩ ቤተ ክርስቲያኑ ለክርስቶስ እንተ አጥረያ በደሙ፤ በገዛ ደሙ የዋጃትን የእግዚአብሔርን ቤተ ክርስቲያን ትጠብቋት ዘንድ መንፈስ ቅዱስ እናንተን ጳጳሳት አድርጎ ለሾመባት ለመንጋው ሁሉና ለራሳችሁ ተጠንቀቁ” (የሐዋ.20፥28)፡፡ ፓትርያርክ ለመሾም:- ሁሉም ድርሻው እስከምን […]

የዚህን ዓለም ጣዕም ናቁ

በዲን. ብርሃኑ ታደሰ ጥቅምት 03 ቀን 2005 ዓ.ም. በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ’ዓለም’ የሚለውን ቃል በተለያየ አገባብ እናገኘዋለን። ለምሳሌ፦ ፍጥረትን፥ ሰማይንና ምድርን የሚወክልበት ጊዜ አለ፦ “ዓለም ሳይፈጠር በፊት ቅዱሳንና ነውር የሌለን በፍቅር እንሆን ዘንድ በክርስቶስ መረጠን።”(ኤፌ 1፥4) “ምድርና ሞላዋ ለእግዚአብሔር ናት፥ ዓለምም በእርስዋም የሚኖሩ ሁሉ።” እንዲል። (መዝ 24፥1) በሌላም ስፍራ  “ከዚህም በኋላ ዓለም አያየኝም፤ እናንተ ግን ታዩኛላችሁ፤” (ዮሐ 14፥19) […]

ማኅበረ ቅዱሳን የቴሌቪዠን መርሐ ግብር ሊጀምር ነው

መስከረም 12 ቀን 2005 ዓ.ም. በዲ/ን ዮሴፍ ይኲኖ አምላክ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን፣ ማኅበረ ቅዱሳን ከጥቅምት 4 ቀን 2005 ዓ.ም ጀምሮ ዘወትር በየሳምንቱ እሑድ ጧት ከ3፡30 እስከ 4፡00 ሰዓት የሚቆይ መርሐ ግብር በኢትዮጵያ ብሮድ ካስቲንግ ሰርቪስ ቴሌቪዠን (EBS TV) ለመጀመር ሙሉ ዝግጅት ማጠናቀቁ ተገለጠ፡፡ በማኅበረ ቅዱሳን ኅትመትና ኤሌክትሮኒክስ ሚዲያ፥ የሬድዮና ቴሌቪዠን ፕሮግራም አስተባባሪ የሆኑት […]

ውጤታማ በመሆን ለውይይት ማመን

መስከረም 10 ቀን 2005 ዓ.ም. በዲ/ን ዶ/ር መርሻ አለኸኝ የአምስተኛው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ፓትርያርክ ሥርዓተ ቀብር ከተፈጸመ ቀናት ተቆጠሩ፡፡ ፓትርያርኩ ዐርፈው መንበረ ፕትርክናው ባዶ መኾኑ ከተረጋገጠበት ዕለት ጀምሮ መንበሩን ለመጠበቅና ለማሰጠበቅ ይበቃል ያለውን አካል የመሾም፤ የቤተ ክርስቲያኗን መንፈሳዊና ማኅበራዊ አገልግሎት የማስቀጠል ሓላፊነት የተጣለበት ቅዱስ ሲኖዶስ አምስት ዋና ዋና ተግባራትን ፈጽሟል፡፡ የመጀመሪያው ፓትርያርኩ ማረፋቸው እንደተሰማና […]