Entries by Website Team

ሐዊረ ሕይወት በሀገረ ጀርመን ተካሄደ

በጀርመን ቀጣና ማእከል ግንቦት 15 ቀን፣ 2006 ዓ.ም. በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ማኅበረ ቅዱሳን አውሮፓ ማእከል የጀርመን ቀጣና ማእከል በአውሮፓ የመጀመሪያውን የሐዊረ ሕይወት መርሐ ግብር ከግንቦት 8-10, 2006 በክሩፈልባክህ (Kroeffelbach) በሚገኘው የኮፕቲክ ቅዱስ እንጦንስ ገዳም (Sankt-Antonius Kloster) በደማቅ ሁኔታ አካሄደ። በዚህ ከ80 በላይ ምእመናን  በተሳተፉበት መርሐ ግብር ላይ ሰፊ ትምህርት የተሰጠ ሲሆን በተለይ ነገረ ድኅነት […]

በክርስቶስ በኲርነት ኹላችን እንነሣለን (፩ኛ ቆሮ፲፭፥፳-፳፪)

በዲ/ን ሰሎሞን አስረስ ሚያዚያ 11 ቀን 2006 ዓ.ም.  እግዚአብሔር ሰውን እንደ መላእክት ሕያው ኾኖ ስሙን ሊቀድስ ክብሩን እንዲወርስ እንጂ እንዲታመም እንዲሞት አድርጎ አልፈጠረውም ነበር፡፡ ሞት ግን ሰው በፈቃዱ ያመጣው እንጂ እግዚአብሔር ሰውን ሊሞት አልፈጠረውም ። ጥበበኛው ሰሎሞን ‹‹በሕይወታችሁ ስሕተት ለሞት አትቅኑ፤ በእጃችሁም ሥራ ጥፋትን አታምጡ፡፡ እግዚአብሔር ሞትን አልፈጠረምና፤ የሕያዋንም  ጥፋት ደስ አያሰኘውምና፡፡ ነዋሪ ይሆን ዘንድ ፍጥረቱን […]

የመምጣትህና የዓለሙ ፍፃሜ ምልክቱ ምንድን ነው? (ማቴ 24፡4)

መጋቢት 12 ቀን 2006 ዓ.ም.  መ/ር ሰሎሞን መኩሪያ  በቅዱስ ወንጌል የመምጣትህና የዓለሙ ፍፃሜ ምልክቱ ምንድን ነው? (ማቴ 24፡4) ብለው የጠየቁት የእጁን ተአምራት ተመልክተው፣ የቃሉን ትምህርት ሰምተው፣ ሁሉን ትተው ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከዋለበት የዋሉ፣ ካደረበት ያደሩ፣ ትምህርት ተአምራት ያልተከፈለባቸው፣ ቅዱሳን አባቶቻችን ሐዋርያት ናቸው፡፡ እነርሱም የተናገራቸውን ሰምተው ለብቻቸው ሲሆኑ በሚያድሩበት በደብረዘይት ተራራ ላይ ጌታ ሆይ ንገረን […]

ተዋሕዶ ለአንድሮይድ ተለቀቀ

የካቲት 17 ቀን 2006 በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን፣ ማኅበረ ቅዱሳን፣ የሰሜን አሜሪካ ማእከል ሚድያና ቴክኖሎጂ ክፍል «ተዋሕዶ» የተሰኘ የእጅ ስልክ እና የኪስ ኮምፒዩተር/ታብሌት/ ላይ የሚሰራ ፕሮግራም ለአይፎን እና አይፓድ /iPhone & iPad/ መልቀቁ የሚታወስ ነው። እነሆ አሁን ደግሞ ለአንድሮይድ/Android/ የእጅ ስልክ እና የኪስ ኮምፒዩተር ተጠቃሚዎች የሚሆን ሶፍትዌር/App/ አዘጋጅቶ አቅርቧል።

ዓቢይ ጾም

የካቲት 15 ቀን 2006 ዓ.ም. በአባ ዘሚካኤል ደሬሳ  እንኳን ለጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የጾመውን ጾም ለመጾም አደረሳችሁ!!! ጌታችን መድኋኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከተጠመቀ በኋላ ከዲያብሎስ ይፈተን ዘንድ ወደ ገዳመ ቆሮንቶስ ሄደ። አርባ ቀንና አርባ ሌሊትም ጾመ። ከዛም ፈታኝ ዲያብሎስ ቀርቦ በስስት፣ በትእቢትና በፍቅረ ነዋይ ፈተነው። ጌታችንም ፈተናዎቹን በጥበበ አምላክነቱ ድል በማድረግ ድልን ለአዳምና ለእኛ ለልጆቹ ሰጠን (ማቴ. 4፡ 1 – […]

የለንደን ደ/ጽዮን ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን እንደገና ተከፍታ አገልግሎት መስጠት ጀመረች

ታኅሣሥ 25 ቀን 2006 ዓ.ም.  ከUK ቀጠና ማዕከል  የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ካህናትን እና ምእመናንን ባሳዘነ ሁኔታ ከዘጠኝ ወራት በላይ ተዘግታ የቆየችው የለንደን ርእሰ አድባራት ደብረ ጽዮን ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን እሁድ ታኅሣስ ፳ ቀን ፳፻፮ ዓ.ም. የሰሜን ምዕራብ አውሮፓ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብጹዕ አቡነ እንጦንስ በተገኙበት በይፋ እንደገና ተከፍታ አገልግሎት መስጠት ጀመረች።

እስክመጣ ድረስ ያላችሁን ጠብቁ (ራእ ፪፡፳፭)

በዲ/ን ሰሎሞን መኩሪያ  ጥቅምት 29 ቀን 2006 ዓ.ም.  ይህንን ኃይለ ቃል የተናገረው ቅዱስ እግዚአብሔር በሐዋርያዉና ወንጌላዊው ቅዱስ ዮሐንስ አማካኝነት ነው። ቅዱስ ዮሐንስ ከዓሣ አጥማጅነት ከተጠራበት ጊዜ አንስቶ ጌታችንን እስከ እግረ መስቀል ድረስ ተከተሎታል፤ በዚያም የጌታችንን መከራ እየተመለከተ ቢያዝንና ቢያለቅስ ይጽናና ዘንድ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምን እንሆ እናትህ በማለት የእናትነት ቃል ኪዳን ተቀብሏል። እርሷንም ወደ ቤቱ […]

አቤልና ቃየል (ለልጆች) (ዘፍ.4፣1-15)

  በአውሮፓ ማዕከል ትም/ እና ሐዋሪያዊ አገልግሎት ክፍል ጥቅምት 19 ቀን 2006 ዓ.ም.  አዳም እና ሔዋን በመጀመሪያ ቃየልን እና አቤልን ወለዱ። አቤልም በግ ጠባቂ ነበረ፤ ቃየልም ምድርን የሚያርስ ነበረ። ሁለቱም ካላቸው ነገር ለእግዚአብሔር ስጦታ ወይም መሥዋዕት አቀረቡ። ቃየል ክፉ ልብ ነበረውና እግዚአብሔር አይበላው ብሎ ከአመረተው እህል ጥሩዉን ሳይሆን መጥፎዉ የማይረባውን መናኛውን እህል ለእግዚአብሔር መሥዋዕት አቀረበ። አቤል […]

ልዩ መርሐ ግብር በእንግሊዝ አገር፣ ሊድስ ከተማ

  መስከረም  18 ቀን 2006 ዓ.ም. በሰሜን ምዕራብ አውሮፓ ሀገረ ስብከት የሊድስ ደብረ ስብሐት መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን እና በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ማኅበረ ቅዱሳን ትብብር ገቢው ለአብነት ት/ቤቶች መርጃ የሚውል ልዩ መርሐ ግብር ሊዘጋጅ ነው። ”በእንተ ስማ ለማርያም” በሚል መሪ ቃል የተሰየመው ይህ መርሐ ግብር ቅዳሜ መስከረም ፳፭ ቀን ፳፻፮ ዓ.ም (5 Oct 2013) […]

ወወሃብኮሙ ትእምርት ለእለ ይፈርሁከ፣ለሚፈሩህ ምልክትን ሰጠሃቸው (መዝ 59፡4)

በመምህር ሰሎሞን መኩሪያ መስከረም  16 ቀን 2006 ዓ.ም. ይህንን የተናገረ ልበ አምላክ ቅዱስ ዳዊት ነው፡፡ ልበ አምላክ ቅዱስ ዳዊት ከተሰጡት 7ት ሃብታት አንዱ ሃብተ ትንቢት  ነው። በዚተሰጠው ሃብተ ትንቢት  የራቀው ቀርቦለታል፣ የቀረበው ተከናውኖለታል፣የረቀቀው ጐልቶለታል። ስለዚህም ከእርሱ በፊት የተደረገውን፣ በእርሱ ዘመን የሆነውን፣ ከእርሱም በኋላ እስከ እለተ ምፅአት የሚደረገውን ሁሉ ልዑል እግዚአብሔር ገልፆለት ብዙ ነገር ተንብይዋል። ከትንቢቶቹም […]