በክርስቶስ በኲርነት ኹላችን እንነሣለን (፩ኛ ቆሮ፲፭፥፳-፳፪)

በዲ/ን ሰሎሞን አስረስ

ሚያዚያ 11 ቀን 2006 ዓ.ም. 

እግዚአብሔር ሰውን እንደ መላእክት ሕያው ስሙን ሊቀድስ ክብሩን እንዲወርስ እንጂ እንዲታመም እንዲሞት አድርጎ አልፈጠረውም ነበር፡፡ ሞት ግን ሰው በፈቃዱ ያመጣው እንጂ እግዚአብሔር ሰውን ሊሞት አልፈጠረውም ። ጥበበኛው ሰሎሞን ‹‹በሕይወታችሁ ስሕተት ለሞት አትቅኑ፤ በእጃችሁም ሥራ ጥፋትን አታምጡ፡፡ እግዚአብሔር ሞትን አልፈጠረምና፤ የሕያዋንም  ጥፋት ደስ አያሰኘውምና፡፡ ነዋሪ ይሆን ዘንድ ፍጥረቱን ፈጥሮአልና፡-የዓለም መፈጠርም ለድኀነት ነውና በእነርሱም ዘንድ የጥፋት መርዝ አልነበረምና ለሲኦልም በምድር ላይ ግዛት አልነበረውምና፡፡ ጽድቅ አትሞትምና፡፡ ክፉዎች ግን በእጃቸውና በቃላቸው ጠሩት፤ ባልንጀራም አስመሰሉት፡፡ በእርሱም ጠፋ፡፡›› እንዲል። (ጥበብ ፩፥፲፪-፲፯)::

ሰው በፈቃዱ ዕፀ በለስን በልቶ መሬት ነህና ወደ መሬት ትመለሳለህ የሚል ድምፅ ከሰማ ወዲህ የሚሞት ሆል፡፡ ይውም በአቤል ተጀምል፡፡ በዚህም አቤል በኲረ ምውታን ተብሎበታል፡፡ ከዚህ በላ የሚነሡ ሰዎች ሞተን ፈርሰን በስብሰን እንቀራለን ብለው ተስፋ እንዳይቆርጡ ኄኖክን በአካለ ሥጋ  ወደ ሰማይ በማሳረጉ ተስፋ ትንሣኤውን ሰጥቸዋል፡፡ (ዘፍ ፭፥፳፬ ፣ ዕብ ፲፩፥፭)::  ሞት እንዳለ በኤቤል ነግሮ አሳዘናቸው ትንሣኤ እንዳለ በኄኖክ ነግሮ ደስ አሰኛቸው ብለው ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን ተርጓመዉታል፡፡ይህንም እነ ቅዱስ ዳዊት ትንቢት የተናገሩለትን አበው በምሥጢር ያውቁት የነበረውን ተስፋ ትንሣኤ  ጌታ ሰው በኾነ ጊዜ በመዋዕለ ስብከቱ አስምሮታል‹‹በመቃብር ያሉቱ ሁሉ ድምፁን የሚሰሙበት ሰዓት ይመጣል፤ መልካምም ያደረጉ ለሕይወት ትንሣኤ ክፉም ያደረጉ ለፍርድ ትንሣኤ ይወጣሉና በዚህ አትደነቁ››:: (ዮሐ ፭፥፳፰)፡፡ ጌታችን በቃል ያስተማረንን ተስፋ ትንሣኤ መዓልት  ሌሊት በከርሠ መቃብር አድሮ ሙስና መቃብርን አጥፍቶ ሕማም ሞት የማይከተለው፣ ረሃብ ድካም የማይስማማው ኃያል ሕያው ኖ በመነሣቱ በገቢር አሳይል፡፡  በዚህም አቤል አስቀድሞ በመሞቱ በኩረ ምውታን እንደ ተባለ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም አስቀድሞ በመነሣቱ በኲረ ትንሣኤ ኾኗል፡፡  ክርስቶስ በሞቱ ሞትን  ደምስሶ በትንሣኤው  የኛን  ትንሣኤ ገልጦ፤ በስብሰን፣ ፈርሰን በመቃብር እንደማንቀር ዘላለማዊ ሕይወት እንዳለን በተግባር አሳየን ፡፡ ‹‹አሁን ግን ክርስቶስ ላንቀላፉት በኲራት ሆኖ ከሙታን ተነሥቷል፡፡ ሞት በሰው በኩል ስለመጣ፤- ትንሣኤ ሙታን በሰው በኩል ሁኗል፡፡ ሁሉ በአዳም እንደሚሞቱ እንዲሁ ሁሉ በክርስቶስ ሕያዋን ይሆናሉና፡፡ ነገር ግን እያንዳንዱ በራሱ ተራ ይሆናል፤ ክርስቶስም እንደ በኲራት ነው:: ›› እንዳለ ቅዱስ ጳውሎስ (፩ኛ ቆሮ፲፭፥፳-፳፫) ፡፡

በዓለ ትንሣኤ ከኃጢአት ወደ ጽድቅ ከሐሳር ወደ ክብር፤ ከሰይጣን አገዛዝ ወደ ዘላለማዊ ነፃነት ፤ ከአሮጌ ሕይወት ወደ አዲስ ሕይወት የተሻገርንበት ታላቅና በኲረ በዓላት ነው፡፡ ቤተክርስቲያናችን  በቅዳሴ ጊዜ   “ክርስቶስ ተንሥአ እሙታን ሞተ ወኬዶ ለሞት፤ ለእለ ውስተ መቃብር  ወኀበ ሕይወት ዘለዓለም ዕረፍት” .እያለች በልዩ ሁኔታ ታከብረዋለች፡፡ ፡፡ በተጨማሪም በመዘምራኑ አማካኝነት ትንሣኤህን ላመን ብርሃንህን ላክልን በማለት በጨለማ የነበራቹህ ሕዝቦች ኑ፤ የትንሣኤውን ብርሃን እዩ ፤ ብርሃኑን ወስዳቹሁ የብርሃኑ ተካፋይ ሁኑ እያለች ጧፍ እያበራች ታድላለች፡፡ ያቆናቱ ደግሞ ‹‹ወተንሥአ እግዚአብሔር ከመ ዘንቃህ እምነዋምወከመ ኃያል ወኅዳገ ወይን፤ ወቀተለ ጸሮ በድኀሬሁ::›› (ትርጉም- እግዚአብሔርም ከእንቅልፍ እንደሚነቃ ተነሣየወይን ስካር እንደተወው እንደ ኃያልም ሰው ጠላቶቹን በላቸው መታ፡፡ መዝ ፸፯፥፷፭::) ብላ ቅዱስ ዳዊት አስቀድሞ የዘመረውን  ትሰብከናለች::   መላእክቱም መልካቸው እንደ መብረቅ፣ ልብሳቸውም እንደ በረዶ ነጭ ለብሰው በትንሳኤው እለት በመቃብሩ ቦታ ተገኝተው ለእነ መግደላዊት ማርያም እንዳበሰሩ እኛም ክርስቲያኖች ነጭ ልብስ ለብሰን በታላቅ ደስታ እናከብረዋለን። (ማቴ ፳፰፥፫)፡፡

ክርስቶስ እንደሚሞት እንደሚነሣም አስቀድሞ በነቢያቱ አማካነት ትንቢት አናግሯል፤ ሱባዔም አስቆጥሯል በምሳሌ አስቀድሞ አሳል፡፡  ጌታችን እንደሚነሣ ጠላቶቹን እንደሚበትን፤መድኃኒትን  እንደሚያደርግ፤ ነፍን በሲኦል የሥጋውንም   በመቃብር እንደማይተው   አስቀድሞ በቅዱስ ዳዊት ተናግል፡፡ (መዝ ፲፩፥፭ ፣ ፲፭፥፲ ፣  መዝ ፷፯፥፩ ፣ መዝ ፸፯፥፷፭)::  ጌታ በመዋዕለ ስብከቱ ‹‹ዮናስ በዓሣ አንባሪ ሆድ ሦስት ቀንና ሦስት ሌሊት እንደ ነበረ፤ እንዲሁ የሰው ልጅ በምድር ልብ ሦስት ቀንና ሦስት ሌሊት ይኖራል፡፡ ብሎ በተናገረው መሠረት ሙስና መቃብርን አጥፍቶ  በ፫ኛው ቀን ተነሥቷል ። (ዮናስ ፪፥፩  ፲፪፥፵)፡፡

በዚህም መሠረት ክርስቶስ በሦስተኛው ቀን እንደተነሣ ወዲያውኑ መላእክት ለቅዱሳት አንስት አበሠሩ እርሱም ለወንዶችም ለሴቶችም ተገለጠአዩትምዳሰሱትም፡፡(ማቴ ፳፰፥፭ ፣ ማር፲፮፥፩-፰፣ ሉቃ ፳፬፥፴)፡፡ ከትንሣኤውም በላ ራሱ ክርስቶስ በብዙ ቦታ ይታይ የቀደመውንም ተአምራቱን ያሳይ ጀመር፤ ፍጹም ሰው ፍጹም አምላክ እንደሆነ  ትንሣኤውም ምንም ጉደለት እንደሌለበት ራሱ መሰከረ አስረዳ፡፡ የተጠራጠሩትን እንዲዳስሱትና እንዲረዱት አደረገ፤ ትንሣኤውም እውነት ስለሆነ ማንም እንዲጠራጠር ክፍት በር አልተወም፡፡(ሉቃ ፳፬፥፴፮-፵፣ዮሐ ፳፥፳፭፳፱)፡፡  ሃይማኖታቸው የጸና አንደበታቸው የቀና ፫፻፲፰ ሊቃውንትም ‹‹ሐመ ወሞተ ወተቀብረ ወተንሥአ እሙታን አመ ሣልስት ዕለት  በከመ ጽሑፍ ውስተ ቅዱሳት መጻሕፍት›› ሲሉ ተናግረዋል። (በደነገጉት ጸሎተ ሃይማኖት)፡፡ ቅዱስ ጳውሎስም በክርስቶስ ትንሣኤ ያለማመን ከንቱነትን ሲያስረዳ ‹‹…ክርስቶስ ከሙታን ካልተነሣ እንግዲያስ ትምህርታችን ከንቱ ነው፤ የእናንተም እምነታቹህ ከንቱ ነው…›› አረጋግጦልናል፡፡ (ኛቆሮ ፲፭፥፲፬)፡፡

አጠቃላይም ክርስቶስ ላንቀላፉት ሁሉ በኩር ሆኖ ተነሥቷል ፤ በዚህም ሁላችንም እንደምንነሳ አብነቱን በተግባር ጭምር አሳይቶናል፡፡ ፍጥረተ አዳም ሁሉ እንደሚነሱ በዳግማዊዉ አዳም ተረጋግጦልናል፡፡ የሰው ልጅ በድካም ይቀበራል በትንሣኤ ፤  መግነዝ ፍቱልኝ ፤ መቃብር ክፈቱልኝ ሳይል፤ ረዳት ሳይሻ ፤ ኃይል አግኝቶ  አካልን ገዝቶ በኃይል ይነሳል፡፡ ስለሆነም በምንነሣው ትንሣኤ  እና ከተነሣን በላ በሚኖረን ሕይወት መሠረት ትንሣኤው ለሰው ልጆች ሁለት ዓይነት ገጽታ አለው፡፡ የክብር ትንሣኤ አለ፤ እንዲሁም የሐሳር ትንሣኤ አለ፡፡ ለክብር ትንሣኤ የተመረጡትም ወቀሳ ሳይኖር ክብርን ለማግኘት ብቻ የሚነሡት ትንሣኤ ነው ፤ ሁለተኛው ደግሞ ለዘለዓለም ፍዳን ወቀሳን ተቀብሎ ለመሔድ የሚነሡት ትንሣኤ ነው፡፡ የሰው ልጅ በሕይወቱ ሳለ  ደግ ሠርቶ እንደሆን ክብር፤ ክፉ ሠርቶ እንደሆን ፍዳ ያገኛል፡፡  

በዚህ ዓለም ነፍሳችን በሥጋችን ተውጣ  ሥጋችንን መስላ  የሥጋችንን ፈቃድ በመከተል ትኖር እንደነበረ በለኛው ሕይወታችን ደግሞ ሥጋችን በነፍሳችን ተውጣ፤ ፈቃደ ሥጋችን ተለውጣ በፈቃደ ነፍሳችን ጸንታ ትኖራለች፡፡ ስለዚህም ቅዱስ ጳውሎስ ሲናገር ‹‹ይ የሚጠፋው የማይጠፋውን ይለብስ ዘንድ  አለውና፤ ይም የሚሞተው የማይሞተውን ይለብስ ዘንድ አለውና ፡፡ ይም የሚጠፋው የማይጠፋውን በለበሰ ጊዜ፤ይው የሚሞተው የማይሞተውን በለበሰ ጊዜ የዚያን ጊዜ ይፈጸማል፡፡ ‹‹ሞት በመሸነፍ ተዋጠ›› ተብሎ የተጻፈው ያንጊዜ ይፈጸማል፡፡›(ኛ ቆሮ ፲፭፥፶፫-፶፬)፡፡

 በመሆኑም የሰው ክብሩ ውርደቱም የሚታወቀው በዳግም ምጽአቱ በትንሣኤ ዘጉባኤ ብቻ ነው የአሁኑ ግን ጊዚያዊ ሕይወት  በመሆኑ ክብሩም ያልፋል ይጠፋል ፤ ውርደቱም ያልፋል ይረሳል፡፡ ከትንሣኤ ሙታን በላ ያለው ግን ካገኙ ማጣት ከገቡ መውጣት  ከተደሰቱ ማዘን ስለሌለ ሁልጊዜ በደስታ ተውጠው የሚኖሩባት  ዘላለማዊ ሕይወት የምትገለጠው በዚያን ጊዜ ነው፡፡ አምላካችን እግዚአብሔር ከትንሣኤው ረድኤት በረከት ያሣትፈን፤ ለክብር ትንሣኤ ያብቃን፡፡

የእግዚአብሔር ቸርነት የድንግል ማርያም አማላጅነት የቅዱሳኑ ተራዳኢነት አይለየን አሜን፡፡