የመምጣትህና የዓለሙ ፍፃሜ ምልክቱ ምንድን ነው? (ማቴ 24፡4)

መጋቢት 12 ቀን 2006 ዓ.ም. 

መ/ር ሰሎሞን መኩሪ 

በቅዱስ ወንጌል የመምጣትህና የዓለሙ ፍፃሜ ምልክቱ ምንድን ነው? (ማቴ 244) የጠየቁ የእጁን ተአምራት ተመልክተው የቃሉን ትምህርት ሰምተው ሁሉን ትተው ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከዋለበት የዋሉ ካደረበት ያደሩ ትምህርት ተአምራት ያልተከፈለባቸው ቅዱሳን አባቶቻችን ሐዋርያት ናቸው፡፡ ርሱም የተናገራቸውን ሰምተው ለብቻቸው ሲሆኑ በሚያድሩበት በደብረዘይት ተራራ ላይ ጌታ ሆይ ንገረን ይህ መቼ ይሆናል የመምጣትህና የዓለሙ ፍፃሜ ምልክቱ ምንድን ነው? ብለው ጠየቁት በዚህ ክፍለ ንባብ ሐዋርያት ሶስት ነገሮችን ጠይቀውታል፡፡

  1. ምልክት

  2. ጌታችን ዳግመኛ ለፍርድ መምጣቱን

  3. የአለም ፍጻሜ

  1. ምልክቱ ምንድን ነው?

ቅዱሳን አባቶቻችን ሐዋርያት የክርስቶስን ዳግም ተመልሶ መምጣትየዓለምን ጻሜ ለመረዳት ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን የጠየቁት ጥያቄየመምጣትህ ነገር ምልክቱ ምንድን ነው?” የሚል ነበር ጌታችንም ለቅዱሳን ሐዋርያት ሲመልስላቸው እንዲህ አለብዙዎች በስሜ እኔ ክርስቶስ ነኝ ብለው ይመጣሉ ብዙዎችንም ያስታሉይህ የመጀመሪያው ምልክት ነው ይህም ማለት ከሰው ልጆች ኃይማኖት ይጐድላል ከእውነተኛይቱ ሀይማኖት ብዙዎች ይናወጣሉ (ይክዳሉ) (ማቴ 244) ስለዚህም ተጠንቀቁ ብሏል፡፡ ተጠንቀቁ ማለ ከሀይማኖታችሁ አትውጡ (አትካዱ) ማለቱ ነው። ዛሬ እንደምንመለከተው ይህንን የትንቢት ቃል በህይወታቸው የሚፈጸባቸ ከቀናችውና ከፀናችው ኦርቶዶክሳዊት ተዋህዶ ሐይማኖታቸው ወጥተው በተለያየ ጥቅማጥቅም ተጠምደው ሀይማኖታቸውን የካዱ /መናፍቅ/ የሆኑ አሉ

ጌታችንም ቀጥሎ ለሐዋርያት እንዲህ አላቸውሕዝብ በሕዝብ ላይ መንግስትም በመንግስት ላይ ይነሣሉ በየሀገሩም ረሀብ ቸነፈር የምድር መናወጥ ይሆናል፡፡ ከዚህ አያይዞ ጌታችን እንዲህ አላቸው ብዙዎች ሐሰተኞች ነቢያት ይነሳሉ ብዙዎችንም ያስታሉ በአህዛብ ላይ ምስክር ሊሆን ይህ የመንግስት ወንጌል በዓለም ሁሉ ይሰበካል፡፡ ይህም ማለት በወንጌል የተነገረውን ነገረ ድህነት ያመነ የተጠመቀ ይድናል ሥጋየን የበላ ደሜን የጠጣ የዘለዓለም ህይወት አለው የሚለውን አልሰማንም እንዳይሉ ለፍርድ እንዲሆንባቸው ባላመኑትም ዘንድ ወንጌል እንደሚሰበክ ተናገረ ዛሬም ይህ ሊፈፀም አህዛብ እንኳ ሳይቀሩ ወንጌሉን እንመራመረው ብለው በቤታቸው አኑረውት ይገኛል፡፡ (ማቴ 2414)

ከዚያም ጌታችን ለሐዋርያት እንዲ አላቸውከዐመፅ ብዛት የተነሣ ፍቅር ከብዙዎች ዘንድ ትጠፋለች”። (ማቴ 2412) አመፅ ለእግዚአብሔር ሕግ አለመታዘዝ ነው። ከዚህ የተነሣ ፍቅረ እግዚአብሔር ትቀዘቅዛለች ማለትም ስለ ፍቅረ እግዚአብሔር ብሎ በእውነት ማገለግል፣ በቅድስና በመንፈሳዊነት መዘመር፣ መቀደስ፣ መስበክ፣ የተለያየ መንፈሳዊ አገልግሎት ማገልገል እየቀነሰ ይሄዳል፡፡ ሁለተኛም ፍቅረ ቢፅ (ወንድምን መውደድ) ይቀንሳል። ስለዚህ ሰውን ከመውደድ ይልቅ ገንዘብን ስልጣንን መውደድ ይቀድምና እርስ በእርስ መጠፋፋት ይሆናል፡፡ እነዚህን እና በምዕራፉ የተጠቀሱ ምልክዮችን በተመለከታችሁና በሰማችሁ ጊዜ በሀይማኖት እና በምግባር ፅኑ ብሎ አዘዛቸው።እስከ መጨረሻው የፀና እርሱ ይድናል” (ማቴ 2413) እንዳለ፡፡

  1. ጌታችን ዳግመኛ ይመጣል

ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከባህርይ አባቱአብ ከባህርይ ህይወቱ ከመንፈስ ቅዱስ ሳይለይ በተለየ አካሉ ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም ከሥዋጋ ሥጋ ከነፍሷ ነፍስ ነስቶ በህቱም ድንግልና ተፀንሶ በህቱም ድንግልና ተወለደ ዓለሙን ለማዳን መከራን በመቀበል በመልዕልተ መስቀል ተሰቀለ ሞተ ተቀበረ መቃብርን አጥፍቶ በስልጣኑተነሳ 40ኛው ቀን በክብር አረገ እንዲሁ እንዳረገ ዳግመኛ ተመልሶፍርድ ይመጣል (ማቴ 21 ማቴ 317 ማቴ 271 ሐዋ 19-12) ተመልሶ ሲመጣ በመጀመሪያ እንደመጣበት ባለአመጣጥ በትህትና መከራ ለመቀበልም አይደለም በክበበ ትስብእት (በለበሰው ሥጋ) በግርማ መለኮት ከባህ አባቱ ከአብ ከባህርይ ህይወቱ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር ቅዱሳን መላእክቱን አስከትሎ ለፍርድ ይመጣል ቅዱስ ዳዊት በመዝሙሩ (492-4) እንደተናገረከክብሩ ውብ ከጽዮን እግዚአብሔር በግልፅ ይመጣል አምላካችን ዝም አይልም እሳት በፊቱ ይነድዳል በዙሪያውም ብዙ ዐውሎ አለ በላይ ያለውን ሰማይ ምድርንም በሕዝቡ ለመፍረድ ይጠራል፡፡

በተጨማሪም ጌታችንም በቅዱስ ወንጌል ተመልሶ ለፍርድ የመምጣቱን ነገር በምሳሌ ሲያስረዳ እንዲህ ብሏል፡፡የሰው ልጅ (ክርስቶስ) በጌትነቱ ቅዱሳን መላእክትን ሁሉ አስከትሎ በሚመጣበት ጊዜ ያን ጊዜ በጌትነቱ ዙፋን ይቀመጣል፡፡ አህዛብ ሁሉ በፊት ይሰበሰባሉ እረኛም በጎችን ከፍየሎች እንደሚለይ እየራሳቸው ይለያቸዋል በጎችን በቀኙ ፍየሎችንም በግራው ያቆማቸዋል፡፡ (ማቴ 2531-33) ም የሰሩትን በቀኙ ከቅዱሳን አባቶቻችን ጋር በመንግስተ ሰማያት እንዲቀመጡ ያደርጋቸዋል። በአንጻሩ በፍየል የተመሰሉ ጥአን በግራ ያቆማቸዋል በሀይማኖት የሚሰራው በጐ ሥነምግባር ጐድሎባቸው በመገኘታቸው ለሰይጣንና ለሰራዊቱ ወደ ተዘጋጀ ወደ ዘለዓለም የጥፋት ቦታ ገሀነም እሳት ይጣላሉ፡፡ (ማቴ 2546) እንዲህ ያለውን ፍርድ ለመስጠት ተመልሶ ይመጣል ስለዚህ በክርስቶስ ክርስቲያን በወልድ ውሉደ እግዚአብሔር የተሰኘ 40 ቀን 80 ቀን ከአብራከ መንፈስ ቅዱስ ከማህፀነ ዮርዳኖስ በጥምቀት የተወለድን ክርስቲያኖች ሊፈርድልን እንዳይፈረድብን በሀይማኖታችን ፀንተን በጐ ሥነምግባር ይዘን ንስሐ ገብተን ሥጋ ወደሙ ተቀብለን ተዘጋጅተን ልንጠብቅ ያስፈልጋል፡፡

  1. የዓለሙን ማለፍ (ፍፃሜ)

አምላካችን ቅዱስ እግዚአብሔር ይህንን የሚታየውን ለም የማይታየውንም ዓለም እመኀበ አልቦ ሀበቦ ካለመኖር ወደ መኖር እንዲሁ አመጣው ሰማይን ያለ ባላ ምድርን ያለ ካስማ በውሃ ላይ አፀና፤ በውስጡ የሚኖሩ ፍጥረታቱንም በመግቦቱ በጠብቆቱ አልተለየውም ደግሞም በዕለተ ምፅአት እንዲሁ ይህንን ዓለም ወደ አለመኖር ያሳልፈዋል፡፡

ዓለም ፍጻሜ ሲያስረዳ ቅዱስ ዳዊትም እንዲህ ብሏልአቤቱ አንተ አስቀድመህ ምድርን መሠረትህ ሰማያትም የእጅህ ሥራ ናቸው፡፡ እነርሱ ይጠፋሉ አንተ ግን ትኖራልህ ሁሉ እንደ ልብስ ያረጃሉ እንደ መጐናፀፊያም ትለውጣቸዋለህ ይለወጡማል(መዝ 10125-26) ስለዚህ በዓለም ውስጥ ያለው እና ዓለሙ በሙሉ ያልፋል ይጠፋል ሌላ የማያልፍ ዓለም ይገለጣል ቅዱስ ጴጥሮስም በመልእክቱ (2ጴጥ 310) “ሰማያት የሚነዋወጡባትና የሚያልፍባት ቀድሞ የነበረው ፍጥረት ሁሉ በእሳት ነበልባል የሚቀልጥባት ምድርና በእርስዋ ላይ ያለው ፍጥረት ሁሉ የሚቃጠልባት የእግዚአብሔር ቀን ግን እንደ ሌባ ድንገት ትመጣለችብሏል፡፡ እንግዲህ ዓለሙም በዓለም ውስጥ ያለው ሥልጣኔው የሥጋ ፈቃዳት የአይን አምሮት ሁሉ የሚያልፍ የሚጠፋ የሚሻር ከሆነ በዚህ የሚያልፈው ዓለም እየኖርን ወደ ማያልፈው ዓለም መሸጋገሪያ የሚሆነን መንፈሳዊ ሥራ (የነፍስ ሥራ) ልንሰራ ያስፈልጋል፡፡

ጠቃላጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በደብረ ዘይት ለሐዋርያት የመምጣቱን ምልክት ከነገራቸው በኋላ እነርሱ ደግሞ የሚድኑበትን ማለትም ይማኖታቸውን እንዲያፀኑ ከመከራው የሚያመልጡበትን ነገር እንዲህ በማለ ነግቸዋል፡፡ያን ጊዜ በደጅ ያሉ ወደ ተራሮች ይሽሹ(ማቴ 2416) ይህ ምሳሌ ነው ትርጓሜውም ተራራ ከምድር ከፍ ያለ ቦታ ነው የውሃ ማጥለቅለቅ የእሳት አደጋ በሆነ ጊዜ ተራራ መሸሻ ነው፡፡ በተራራ የተመሰለች እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ናት (መዝ 472) ወደ እመቤታችን ይሽሹ ማለትም በእመቤታችን አማላጅነት ይታመኑ (ውዳሴ ማርያም ይድገሙ) ማለት ነው ከእመቤታችን ቀጥሎ በተራራ የተመሰሉ ቅዱሳን ናቸው (መዝ1201) ስለዚህ በቅዱሳን ቃልኪዳን ይታመኑ ማለት ነው፡፡

በሌላ ትርጓሜ ተራራ የተባለች ቅድስት ቤተክርስቲያን ናት (መዝ141) ስለዚህ ወደ ቤተክርስቲያን መሄድን እንዳናስታጉል በቤተክርስቲያን የሚፈተተውን ቅዱስ ሥጋውን የሚቀዳውን ክቡር ደሙን ንስሐ ገብተን እንድንቀበል በዚህም የጌታችንን መምጣት እንድንጠባበ አዘዘን እንደ ጌታችን ትዕዛዝ ተዘጋጅተን እንድንኖር የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም አማላጅንት የቅዱሳን ፀሎት የመላእክት ፈጣን ተራዳኢነት አይለየን፡፡ አሜን፡፡