ተዋሕዶ ለአንድሮይድ ተለቀቀ

tewahedoAndroid-calendarየካቲት 17 ቀን 2006

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን፣ ማኅበረ ቅዱሳን፣ የሰሜን አሜሪካ ማእከል ሚድያና ቴክኖሎጂ ክፍል «ተዋሕዶ» የተሰኘ የእጅ ስልክ እና የኪስ ኮምፒዩተር/ታብሌት/ ላይ የሚሰራ ፕሮግራም ለአይፎን እና አይፓድ /iPhone & iPad/ መልቀቁ የሚታወስ ነው። እነሆ አሁን ደግሞ ለአንድሮይድ/Android/ የእጅ ስልክ እና የኪስ ኮምፒዩተር ተጠቃሚዎች የሚሆን ሶፍትዌር/App/ አዘጋጅቶ አቅርቧል።

ይህ የስልክ ሶፍትዌር ለአይፎንም ሆነ አንድሮይድ ተጠቃሚዎች በያሉበት ኾነው

  • ልዩ ልዩ ትምህርቶችን እና መዝሙራትን፣
  • የቀን መቁጠሪያን፣
  • የዕለትና የበዓላት ምንባባትን /ግጻዌን/፣
  • በድምጽና በምስል የቀረቡ መንፈሳዊ ትረካዎችንና ጭውውቶችን፣
  • ልዩ ልዩ የጸሎት መጻሕፍትን
  • እንዲሁም በሰሜን አሜሪካ በልዩ ልዩ ግዛቶች ስለሚገኙ አብያተ ክርስቲያናት መረጃዎችን

በቀላሉ ማግኘት ያስችላቸዋል።

ይህንን አገልግሎት ለማግኘት የሚሹና አንድሮይድ የተሰኘውን ግብረ ቴክኖሎጂ የሚጠቀሙ የእጅ ስልክ ወይም የኪስ ኮምፒዩተር ያላቸው ሁሉ ሶፍትዌሩን /አፕሊኬሽኑን/ ከጉግል ፕለይ/Google Play/ ወስጥ ተዋሕዶ/Tewahedo/ የሚለውን ፈልጎ በመጫን መጠቀም ይችላሉ።

 

GooglePlay