Entries by Website Team

የአውሮፓ ማዕከል ሥራ አስፈጻሚ የገጽ ለገጽ ስብሰባውን አካሄደ።

መጋቢት 10 ቀን 2007 ዓ.ም. በኢ.ኦ.ተ.ቤ.ክ. ማኅበረ ቅዱሳን የአውሮፓ ማዕከል ሥራ አስፈጻሚ ጉባኤ የ፳፻፯ ዓ.ም. የመጀመሪያውን የገጽ ለገጽ ስብሰባ በዴንማርክ ሀገር በኮፐንሀገን ከተማ በቅዱስ ማርቆስ የግብጽ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ከመጋቢት ፬-፮ ቀን ፳፻፯ ዓ.ም. አካሄደ። የሥራ አስፈጻሚ አባላቱ አርብ መጋቢት ፬ ቀን ፳፻፯ ዓ.ም. ኮፐንሀገን ከተማ የተገኙ ሲሆን፣ ምሽቱን ከዴንማርክ ግንኙነት ጣቢያ አባላት ጋር የጋራ […]

ደብረ ዘይት

በአባ ዘሚካኤል ደሬሳ መጋቢት 4 ቀን 2007 ዓ.ም. ደብረዘይት የዓቢይ ጾም እኩሌታ ነው ። በእለቱም ስለ ዳግም ምጽአት ይነገራል። ስለ ምጽአት ነቢዩ ዘካርያስ «በዚያን ቀን እግሮቹ በኢየሩሳሌም ትይዩ በምሥራቅ በኩል ባለው በደብረ ዘይት ላይ ይቆማሉ… አምላኬ እግዚአብሔር ከቅዱሳኑ ጋር ይመጣል …አንድ ቀን ይሆናል…. በዚያም ቀን የሕይወት ውኃ ከኢየሩሳሌም ይወጣል፤ እኩሌታው ወደ ምሥራቁ ባሕር እኩሌታውም ወደ […]

ሀገረ ስብከቱ የመጀመርያውን ሥልጠና ሰጠ

በጀርመን ቀጣና ማዕከል መጋቢት 4 ቀን 2007 ዓ.ም. በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የደቡብ፣ ደቡብ ምሥራቅና ደቡብ ምዕራብ አውሮፓ ሀገረ ስብከት በአይነቱ ልዩ የሆነ እና የሰበካ ጉባዔ አባላትን አቅም ለማሳደግ የታለመ ሥልጠና በሀገረ ጀርመን በፍራንክፈርት ዙርያ የሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ መቀመጫ በሆነው በሩሰልስሀይም ከተማ የካቲት ፳፰ ቀን ፳፻፯ዓ.ም ሰጠ:: የሥልጠና መርሐግብሩን በጸሎትና በቡራኬ የከፈቱት ብፁዕ አቡኑ […]

የልጆች አስተዳደግ በውጭው ዓለም*

በላቸው ጨከነ (ዶ/ር) የካቲት 9 ቀን 2007 ዓ.ም. ልጆች ”ብዙ ተባዙ” በሚለው አምላካዊ ቃል መሠረት ከእግዚአብሔር የሚገኘ በረከቶች ናቸው። ቅዱስ ዳዊት “ልጆች የእግዚአብሔር ስጦታዎች ናችው”(መዝ ፻፳፮፥፫) እንዳለ። ቅዱሳን ፣ ጻድቃን፣ ጳጳሳት ፣ ካህናት፣ ነገሥታት እና መሣፍንት የሚገኙት ከዚሁ አምላካዊ በረከት ነው። በአለንበት ዘመን የአኗኗር ዘይቤ መቀየር ፣ የኑሮ ጫና እና የዓለም መቀራረብ የልጆችን አስተዳደግ ለሁሉም […]

ጾመ ነነዌ

ኤርምያስ ልዑለቃል (ዶ/ር) ጥር 26 ቀን 2007 ዓ.ም.  “የነነዌ ሰዎች በፍርድ ቀን ከዚህ ትውልድ ጋር ተነስተው ይፈርዳሉ ፤ በዮናስ ስብከት ንስሐ ገብተዋልና፡፡” (ማቴ ፲፪፥፵፩) ይህንን የተናገረው ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው፡፡ ጌታችን ለዚህ ትምህርቱ መነሻ ያደረገው የጻፎችን እና የፈሪሳውያንን ጥያቄ ነው፡፡ “መምህር ሆይ ከአንተ ምልክት ልናይ እንወዳለን” ቢሉት “ክፉና አመንዝራ ትውልድ ምልክት ይሻል ፤ ከነቢዩም […]

ጥምቀት እና በዓለ ጥምቀት

በዲ.ን ዶ.ር አለማየሁ ኢሳይያስ ጥር 8 ቀን 2007 ዓ.ም. ጥምቀት ጥምቀት የሚለው ቃል አጥመቀ (አጠመቀ ወይም ነከረ) ከሚለው የግእዝ ሥርወ ቃል የተገኘ ሲሆን ትርጉሙም መጠመቅ ፣ መነከር ፣ መደፈቅ ፣ ውኃ ውስጥ ብቅ ጥልቅ ማለት ነው ። ጥምቀት ከሌሎቹ ምሥጢራተ ቤተክርስቲያን በመጀመሪያ ላይ የሚፈጸም ምሥጢር ሲሆን ያለ ጥምቀት ከሌሎቹ ምሥጢራተ ቤተክርስቲያን መሳተፍ አይቻልም ። (ዮሐ. […]

የጥምቀት በዓል በለንደን እና በሊቨርፑል ከተሞች በአንድነት ይከበራል

በዩኬ ቀጠና ማዕከል ጥር 5 ቀን 2007 ዓ.ም. የ፪፻፯ ዓ.ም የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ የጥምቀት በዓል በታላቋ ብሪታኒያ በለንደን እና በሊቨርፑል ከተሞች በህብረት ይከበራል። በዓሉ በሰሜን ምዕራብ አውሮፓ ሀገረ ስብከት አዘጋጅነት ጥር ፲ እና ፲፩ ቀን ፪፻፯ ዓ.ም በለንደን ደብረ ጽዮን ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን እንዲሁም ጥር ፲፭ እና ፲፮ ቀን ፪፻፯ ዓ.ም በሰሜን ምዕራብ […]

ብፁዕ አቡነ እንጦንስ የልደትን በዓል አስከመልክቶ የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት አስተላለፉ

ታህሣስ 28 ቀን 2007 ዓ.ም. የሰሜን ምዕራብ አውሮፓ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ እንጦንስ የልደትን በዓል አስከመልክቶ የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት አስተላልፈዋል። ብፁዕነታቸው ያስተላለፉትን መልእክት ከዚህ በታች ይመልከቱ። ወስብሐት ለእግዚአብሔር።

ልዩ ከሆነች ድንግል ማርያም ይህ የአምላክ መወለድ ምን ይደንቅ

ዲ.ን ብሩክ አሸናፊ ቀን ታህሣስ 27 ቀን 2007 ዓ.ም. «ኦ ዝ መንክር ልደተ አምላክ እማርያም እምቅድስት ድንግል፤ ልዩ ከሆነች ድንግል ማርያም ይህ የአምላክ መወለድ ምን ይደንቅ» ውዳሴ ማርያም ዘሐሙስ ይህ ቃል በ፫፻፮ ዓ.ም ገደማ በሜሶጶጣሚያ ውስጥ በምትገኘው በንጽቢን ተወልዶ፣ የጸጋህን ማዕበል ግታልኝ እስኪል ድረስ ጸጋ እግዚአብሔር በዝቶለት እጅግ ብዙ ድርሳናትን የደረሰው፣ በጉባኤ ኒቅያ መምህሩ ከነበረው […]

ሐዊረ ሕይወት (የሕይወት ጉዞ) በሀገረ ጀርመን

ታህሣስ 26 ቀን 2007 ዓ.ም. በኢ.ኦ.ተ.ቤ.ክ.ሰ.ማ.መ.ማኅበረ ቅዱሳን የጀርመን ቀጠና ማዕከል ሁለተኛውን የሐዊረ ሕይዎት ጉዞ ከመጋቢት 11 – 13 ቀን 2007 ዓ.ም. ወደ ጀርመን ሀገር የሚገኘው ግብጽ ቅዱስ እንጦንስ ገዳም እንደሚያካሂድ አስታወቀ። በዚህ መርሐ ግብር ላይ በሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን ትምህርተ ወንጌል እንዲሁም ከምዕመናን ለሚነሱ ጥያቄዎች መልስ ይሰጥበታል። በጉዞው ላይ ከተለያዩ የአውሮፓ ሀገራት የሚመጡ ምዕመና እንደሚሳተፉ ይጠበቃል። […]