Entries by Website Team

በጀርመን የክሮንበርግ ቅዱስ ዑራኤል ቤተ ክርስቲያን ቅዳሴ ቤቱ ተከበረ።

በጀርመን ንዑስ ማእከል የካቲት 13 ቀን 2008 ዓ.ም. በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን በደቡብ፣ ምሥራቅ እና ምዕራብ አውሮፓ ሀገረ ስብከት የክሮንበርግ(ጀርመን) ቅዱስ ዑራኤል ቤተ ክርስቲያን በሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ በብፁዕ አቡነ ሙሴ የካቲት 6 ቀን 2008 ዓ.ም. ተባርኮ ቅዳሴ ቤቱ ተከብሯል። የቤተክርስቲያኑ መመሥረት በፍራንክፈርትና አካባቢው ከተወሰኑ ዓመታት ወዲህ በዓታ ለማርያም የፅዋ ማኅበርን በማቋቋም ተሰባሰበው ይገለገሉ […]

የገና በዓል በቅዱስ ላሊበላ

በቀሲስ መንግስቱ ጎበዜ ታህሳስ 27 ቀን 2008 ዓ.ም በቅድስት ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያናችን በድምቀት ከሚከበሩት የጌታችንና የመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ዓበይት በዓላት መካከል የገና (የልደት) በዓል አንዱ ነው።ይህ በዓል ሰማይና መሬት የታረቁባት፣ ሰው እና መላእክት በአንድነት የዘመሩበት ፣ ከሁሉም በላይ አምስት ሺህ አምስት መቶ ዘመን ሲጠበቅ የነበረው የአዳም ተስፋ የተፈፀመበት፣ አምላክ የአምላክ ልጅ በግሩም ተዋህዶ ከእመቤታችን ከቅድስት […]

ክፍት የሥራ ማስታወቂያ

በማኅበረ ቅዱሳን የአውሮፓ ማእከል ጽ/ቤት ታህሳስ 3 ቀን 2008 ዓ.ም በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምርያ ማኅበረ ቅዱሳን የአውሮፓ ማእከል እየሰጠ ያለውን አገልግሎት አጠናክሮ መስጠት ያስችለው ዘንድ በመደበኛነት የሚያገለግል የጽ/ቤት ረዳት ሆኖ እገዛ የሚሰጥ አገልጋይ ይፈልጋል፡፡

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የደቡብ ምሥራቅና ምዕራብ አውሮፓ ሀገረ ስብከት”የግብጽ እና የኢትዮጵያ ሲኖዶስ ተቋቋመ” ተብሎ እየተናፈሰ ስላለው አሉባልታ መግለጫ ሰጠ።

ሀገረስብከቱ በቅርቡ የተሳካ ዓመታዊ ስብሰባ፣ የትምህርተ ወንጌልና የዐውደ ጥናት ጉባኤ አካሂዷል። በጀርመን ንዑስ ማእከል መስከረም 11 ቀን 2008 ዓ.ም በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የደቡብ ምሥራቅና ምዕራብ አውሮፓ ሀገረ ስብከት ሰሞኑን “በጀርመን የሆክስተር ከተማ ነሐሴ 14 ቀን 2007 ዓ.ም የግብጽ እና የኢትዮጵያ ሲኖዶስ ተቋቋመ” ተብሎ እየተናፈሰ ነው ስላለው አሉባልታ መግለጫ አወጣ:: ሀገረ ስብከቱ መግለጫውን ያወጣው […]

ሀገረ ስብከቱ የመጀመሪያውን ልዩ የትምህርተ ወንጌል ጉባኤና ዐውደ ጥናት እንደሚያካሂድ አሳወቀ፡፡

በወርቁ ዘውዴ ነሐሴ 19 ቀን 2007 ዓ.ም. በኢ/ኦ/ተ/ቤተ ክርስቲያን የደቡብ፣ ምሥራቅና ምዕራብ አውሮፓ ሀገረ ስብከት ከነሐሴ ፴ እስከ ጷጉሜን ፩ ቀን ፳፻፯ ዓ.ም. የሀገረ ስብከቱ ጽ/ቤት በሚገኝበት በጀርመኗ ሮሰልሳይም ከተማ የትምህርተ ወንጌል ጉባኤ እና ዐውደ ጥናት ለማካሄድ ዝግጅቱን ማጠናቀቁን አሳወቀ፡፡ ሀገረ ስብከቱ በአዲስ መልኩ ተዋቅሮ የመንበረ ጵጵስና መቀመጫውን በጀርመን ካደረገበት ጊዜ አንስቶ አስተዳደራዊ መዋቅሩን በማጠናከር […]

ጾም በስደት ሀገር

በቀሲስ ለማ በሱፈቃድ ሐምሌ 30 ቀን 2007 ዓ.ም. በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሥርዓት መሠረት ሰባት አጽዋማት አሉ :: ከእነዚህም አንዱ ጾመ ፍልሰታ ነው:: ጾም ማለት በታወቀ ወራት ሳምንታት እና ዕለታት እስከ ጾሙ ፍጻሜ ድረስ ከተከለከሉ ጥሉላት ምግቦችና መጠጦች ወይም የእንስሳት ውጤቶች ሥጋ ወተትና ከመሳሰሉት መከልከል ሲሆን፣ ከዚያ ውጪ የሆኑ ምግቦች ለተወሰነ ሰዓት ብቻ መከልከል […]

በፓርማ አውደ ርእይ ተካሄደ

በጣሊያን ንዑስ ማእከል ሐምሌ 26 ቀን 2007 ዓ.ም. የፓርማ ቤዛ ብዙኃን ቅድስት ኪዳነ ምህረት ቤተክርስቲያን ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ ከማኅበረ ቅዱሳን የአውሮፓ ማእከል ጋር በመተባበር ያዘጋጀው አውደ ርእይ በጣሊያን ፓርማ ከተማ ተካሄደ።

በዴንማርክ ዐውደ ርእይ ተካሄደ

በዴንማርክ ግኑኝነት ጣቢያ ሐምሌ 10 ቀን 2007 ዓ.ም. በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ሰ/ት/ቤቶች ማ/መምሪያ ማኅበረ ቅዱሳን አውሮፓ ማዕከል የዴንማርክ ግንኙነት ጣቢያ ከዴንማርክ የደብረ ምሕረት ቅዱስ አማኑኤል ቤተክርስቲያን ሰበካ ጉባኤ ጋር በመተባበር በኮፐንሃገን ከተማ ዐውደ ርእይ አካሄደ። ዐውደ ርእዩ በመልአከ ምሕረት ቆሞስ አባ ዘሚካኤል ጸሎት እና የመግቢያ ንግግር እንዲሁም ለአውሮፓ ማዕከል ፲፭ኛ ጠቅላላ ጉባኤ ከዋናው ማዕከል ተወክለው በመጡት በአቶ […]

የአውሮፓ ማዕከል ፲፭ኛ ጠቅላላ ጉባኤውን በፍራንክፈርት ፥ ጀርመን አካሄደ

በብዙኀን መገናኛ እና ቴክኖሎጂ አገልግሎት ክፍል ሐምሌ 02 ቀን 2007 ዓ.ም. በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የሰንበት ት/ቤቶች ማደረጃ መምሪያ ማኅበረ ቅዱሳን የአውሮፓ ማዕከል አስራ አምስተኛ ጠቅላላ ጉባኤውን በጀርመን ሀገር በፍራንክፈርት ከተማ በምትገኘው በደብረ ፀሐይ ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን ከሰኔ ፳፮ እስከ ፳፰ ቀን ፳፻፯ ዓ.ም. አካሄደ።

ጉባኤያቱ እንደቀጠሉ ናቸው።

በብዙኀን መገናኛ እና ቴክኖሎጅ አገልግሎት ክፍል ሰኔ 23 ቀን 2007 ዓ.ም. በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ማኅበረ ቅዱሳን የአውሮፓ ማእከል በተለያዩ የአውሮፓ ሀገራት ካሉ አብያተ ክርስቲያናት ጋር በመተባበር «ለሁለንተናዊ የቤተክርስቲያን እድገት የድርሻችንን እንወጣ» በሚል መሪ ቃል እያካሄደ ያለው ጉባኤ እንደቀጠለ ነው። ከማዕከሉ ያገኘው መረጃ እንደሚያመለክተው በሰኔ ፮ ቀን ፳፻፯ ዓ.ም. ለመጀመሪያ ጊዜ በስዊዘርላድ […]