Entries by Website Team

የሰሜን ምዕራብ አውሮፓ ሀገረ ስብከት ሁለት የወረዳ ቤተ ክህነት ጽሕፈት ቤቶችን አዋቀረ።

በአውሮፓ ማእከል ኅ/ኤ/ሚ ክፍል የካቲት 2 ቀን 2009 ዓ.ም በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰሜን ምዕራብ አውሮፓ ሀገረ ስብከት የወረዳ ቤተክህነት ጽሕፈት  ቤቶችን  አዋቀረ። ሀገረ ስብከቱ የመላው አውሮፓ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ እና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል ብፁዕ አቡነ ሙሴ መቀመጫ በሆነችው በጀርመን ሀገረ በምትገኘው የሮሰልስሃይም ከተማ ጥር 19 እና  20 ቀን 2009 ዓ.ም ጉባኤውን  አካሂዷል። […]

ጥር​ ​፳፩​ ​የእመቤታችን​ ​በዓለ​ ​ዕረፍት (​አስተርእዮ​ ​ማርያም)

በቀሲስ ኃይለኢየሱስ ተመስገን ጥር 20 ቀን 2009 ዓ.ም ” አስተርእዮ ማርያም “ አስተርእዮ ማለት መታየት፣ መገለጥ ማለት ነው። ቃሉ አስተርአየ ታየ፣ ተገለጠ ከሚለው የግዕዝ ግሥ የተገኘ ነው። ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በገባው ቃል ኪዳን መሠረት በሥጋ የተገለጠበት(የታየበት) ፣ አንድነት ሦስትነቱም የተገለጠበት ወቅት በመሆኑ ከልደት በዓል እስከ ጥር መጨረሻ በሙሉ ዘመነ አስተርእዮ በመባል ይታወቃል። የእመቤታችን በዓለ ዕረፍት በዘመነ […]

ሠለስቱ ደቂቅ በትውልድ መካከል

በአባ ዘሚካኤል ደሬሳ ታኅሣሥ 18 ቀን 2009 ዓ.ም ትውልድ ያልፋል ትውልድ ይመጣል። ያልፈው ትውልድ እንደ እምነቱ እና እንደስሥራው ወይ ገነት ወይ ሲዖል ይኖራል። አዲሱ ትውልድ እንዲሁ የዚህን ዓለም ኑሮ ጊዜው ባመቻቸለት ሁኔታ ለሚቀጥለው ዘላለማዊ ሕይወት ወይ ለመንግስተ ሰማያት ወይ ለገኃነመ እሳት እራሱን ያዘጋጃል። ነገር ግን በትውልድ መካከል ሁልጊዜም እግዚአብሔር እንደትውልዱ የእምነት ፍላጎትና ጽናት መጠን ራሱን ይገልጻል። […]

ጽጌ አስተርአየ በውስተ ምድርነ ጊዜ ገሚድ በጽሐ

በ ዲ/ን አረጋ ጌታነህ ጥቅምት 25 ቀን 2009 ዓ.ም “ጽጌ አስተርአየ በውስተ ምድርነ ጊዜ ገሚድ በጽሐ  ፤ አበባ በምድራችን ታየ  የመከርም ጊዜ ደረሰ”  መኃ ፪፥፪ በቤተ ክርስቲያናችን የዘመን አቆጣጠር መሠረት አሁን ያለንበት ወቅት ዘመነ መፀው ይባላል። አንዳንዶች በስሕተት ፀደይ ሲሉት ይሰማሉ። ዓመቱን ለዐራት የሚካፈሉት ወቅቶች በሐዲስ ኪዳን በዐራቱ ወንጌላውያን የሚመሰሉ ሲሆኑ ሁልጊዜም በ፳፮ ይጀምራሉ በ ፳፭ ደግሞ የሚፈጽሙ […]

የመስቀል (ደመራ) በዓል በፊንላንድ ርዕሰ መዲና በሄልሲንኪ ለመጀመሪያ ጊዜ በአደባባይ በድምቀት ተከበረ።

በአውሮፓ ማእከል ኅ/ኤ/ሚ ክፍል መስከረም 26 ቀን 2009 ዓ.ም በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በሰሜን ምዕራብ አውሮፓ ሀገረ ስብከት የሄልሲንኪ ደብረ አሚን አቡነ ተክለ ሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን አዘጋጅነት በተካሄደው የደመራ በዓል ላይ የደብሩ አገልጋይ ካህናት ዲያቆናት፣ የሰንበት ትምህርት ቤት መዘምራን እና ምዕመናን ተገኝተዋል።  በተጨማሪም የሄልሲንኪ ደብረ ሰላም መድኃኔዓለም የኤርትራ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ካህናት እና ምእመናን፣ […]

‹‹መስቀል ለእለ ነአምን መድኅን›› ቅዱስ ያሬድ

በመጋቢ ሀዲስ ምስጢረ ስላሴ ማናዬ መስከረም 16 ቀን 2009 ዓ.ም. ‹‹መስቀል ለእለ ነአምን መድኅን – መስቀል ለምናምን መድኃኒት ነው››። ስለነገረ መስቀሉ ከተናገሩ ሊቃውንት የኢትዮጵያው ሊቅ ቅዱስ ያሬድ ትልቅ ድርሻ አለው። በአምስቱም ድርሰቶቹ በሰፊው ስለ መስቀል ዘምሯል፣ ተናግሯል፣ አመስጥሯል። ከላይ ያነሳነውን ኃይለ ቃል የተናገረውም እርሱ ነው። ምክንያቱም የቅዱስ ያሬድ ድርሰቶች ስለ ነገረ ድኅነነት ያጠነጥናሉ። እግዚአብሔር በነገረ […]

የደብረ መዊ ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያ ቅዳሴ ቤቱ ተከበረ

በአውሮፓ ማእከል ኅ/ኤ/ሚ ክፍል መስከረም 9 ቀን 2009 ዓ.ም በስዊድን ሉንድ ከተማ የደብረ መዊ ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያ በብፁዕ አቡነ ሙሴ የደ/ም/ም እና የሰሜን ምዕራብ አውሮፓ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ነሐሴ 29 ቀን 2008 ዓ.ም. ታቦተ ህጉ ተባርኮ ቅዳሴ ቤቱ ተከብሯል።

«መኑ ውእቱ ብእሲ ዘይፈቅድ ሐይወ ወያፈቅር ይርአይ መዋዕለ  ሠናያተ »

በመምህር ፍቃዱ ሣህሌ ጳጕሜ 5 ቀን 2008 ዓ.ም. ሕይወትን የሚፈቅድ ሰው ማን ነው ? በጎ ዘመንንም ለማየት የሚወድድ ማን ነው ? መዝሙረኛው ቅዱስ ዳዊት እንደ ሰውነቱ በርካታ ጥያቄዎችን ጠይቋል። እንደ መንፈስ ቅዱስ ማደሪያነቱ በመንፈስ ቅዱስ ተቃኝቶ ለጥያቄዎችም መልስ ሰጥቷል። ከላይ የተቀምጠው ጥያቃዊ  ኃይለ ቃልም በተመሳሳይ ሁኔታ ያቀረበው ጥያቄ ሲሆን ለሁላችንም ጥቅም  ይሆን ዘንድ መንፈስ ቅዱስ እርሱ […]

በጀርመን በርሊን ዐውደ ርእይ እና ስብከተ ወንጌል መርሐግብር ተካሄደ

በጀርመን ንኡስ ማእከል ጳጕሜ 3 ቀን 2008 ዓ.ም. በጀርመን ርእሰ ከተማ በበርሊን ነሐሴ ፯ እና ፰፣ ፳፻፰ ዓ.ም “ለሁለንተናዊ የቤተክርስቲያን እድገት የድርሻችንን እንወጣ” በሚል መሪ ቃል የዐውደ ርእይ እና የስብከተ ወንጌል መርሐግብር ተካሄደ። ይህንን በማኅበረ ቅዱሳን የአውሮፓ ማእከል ከበርሊን ደብረ ገነት ቅዱስ አማኑኤል ቤተ ክርስቲያን ሰበካ ጉባኤ ጋር በመተባበር ያዘጋጁትን መርሐግብር የከፈቱት የደብሩ አስተዳዳሪ መልአከ ገነት ቆሞስ […]

የአውሮፓ ማእከል ፲፮ኛ ጠቅላላ ጉባኤ ተካሔደ

በአውሮፓ ማእከል ኅትመትና ኤሌክትሮኒክስ ሚዲያ ክፍል ሐምሌ 15 ቀን 2008 ዓ.ም. በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ማኅበረ ቅዱሳን የአውሮፓ ማእከል ፲፮ኛ ጠቅላላ ጉባኤ ከሐምሌ ፩-፫ ቀን ፳፻፰ ዓ.ም በስዊድን አገር ስቶክሆልም ከተማ ተካሔደ። በጠቅላላ ጉባኤው በተለያዩ የአውሮፓ አገሮች የሚኖሩ ከሰባ በላይ የማእከሉ አባላት፤ የዋናው ማእከልና የሰሜን አሜሪካ ማእከል ተወካዮች፤ እንደዚሁም ጥሪ […]