Entries by Website Team

በዓለ ልደቱ ለእግዚእነ ወአምላክነ ወመድኃኒነ ኢየሱስ ክርስቶስ

በበኩረ ፍሥሐ ቀሲስ ኃይለኢየሱስ ተመስገን ታኅሣሥ 28 ቀን 2010 ዓ.ም. “እስመ ናሁ እዜንወክሙ ዓቢየ ዜና ዘይከውን ፍሥሐ ለክሙ ወለኩሉ ሕዝብ “ሉቃ ፪ ፥፲ ለወልደ እግዚአብሔር ሁለት ልደታት እንዳሉት እናምን ዘንድ ይገባናል። አንዱ ከዘመን ሁሉ አስቀድሞ ከእግዚአብሔር አብ የተወለደው ልደት ነው። ሁለተኛውም ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም በኋላ ዘመን የተወለደው ልደት ነው፡፡ሃይማኖተ አበው ዘባስልዮስ ምዕራፍ ፴፬ ቁጥር ፮ […]

በአውሮፓ የሕፃናት እና ታዳጊዎች ሥርዓተ ትምህርት ተመረቀ

በእንግሊዝ ንዑስ ማእከል ኅዳር 13 ቀን 2010 ዓ.ም. በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሰ/ት/ቤ/ማ/መ/ ማኅበረ ቅዱሳን አውሮፓ ማእከል የተተኪ ትውልድ ሥልጠና ክፍል አስተባባሪነት የተዘጋጀ ከኢትዮጵያ ውጪ የሚኖሩ ሕፃናት እና ታዳጊዎችን ለማስተማር የሚያግዝ ሥርዓተ ትምህርት በእንግሊዝ አገር በለንደን ከተማ በደብረ ገነት ቅድስት ሥላሴ ቤተ ክርስቲያን ኅዳር ፫ ቀን ፳፻፲ ዓ.ም ተመረቀ፡፡

በጀርመን ኑረንበርግ ዐውደ ርእይ እና የስብከተ ወንጌል መርሐግብር ተካሄደ

በጀርመን ንዑስ ማእከል ጥቅምት 20 ቀን 2010 ዓ.ም. በደቡባዊቷ የጀርመን ከተማ ኑረንበርግ ጥቅምት 11 እና 12፣ 2010 ዓ.ም “አብረን እንሥራ ለውጥ እናመጣለን” በሚል መሪ ቃል የዐውደ ርእይ እና የስብከተ ወንጌል መርሐግብር ተካሄደ። ይህንን በማኅበረ ቅዱሳን የአውሮፓ ማእከል  የጀርመን ንዑስ ማእከል ከኑረንበርግ ቅድስት ሥላሴ ቤተ ክርስቲያን ሰበካ ጉባኤ ጋር በመተባበር ያዘጋጀውን ፍኖተ ቤተከርስቲያን፣ ገዳማት እና የአብነት ትምህርት ቤቶች […]

“ወይንሳዕ መስቀለ ሞቱ ወይትልወኒ – የሞቱን መስቀል ተሸክሞ ይከተለኝ”

በዲ/ን ዶ/ር ቴዎድሮስ በለጠ መስከረም 16 ቀን 2010 ዓ.ም. ለስም አጠራሩ ክብር ይግባውና በቃል መነገሩ፣ በኅሊና መዘከሩ፣ በሰው ልብ መታሰቡ፣ በቅዱሳት መጻሕፍት መዘገቡ ከፍ ይበልና፣ ጌታችንንና አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እኛ ልጆቹ ፈቃዱን እያደረግን እንድንኖርና እርሱም ከመልካም ምግባራችንና ከበጎ ትሩፋታችን ብቻ የተነሳ ፍጹማን እንደማንሆን ያውቃልና፣ ከማያልቅ ልግስናው ከማይጓደል ምሕረቱ ዘመናትን እየመጸወተን ደስ የሚሰኝበትን ለእኛ እያደረገ […]

በኮፐንሀገን የደብረ ምሕረት ቅዱስ አማኑኤል ቤተ ክርስቲያን ዐቢይ የአዲስ ዓመት መንፈሳዊ ጉባኤ አካሄደ።

በዴንማርክ ግንኙነት ጣቢያ መስከረም 10 ቀን 2010 ዓ.ም. ባሳለፍነው ቅዳሜ መስከረም 6 እና እሑድ መስከረም 7 ቀን 2010 ዓ.ም. (September 16 and 17 /2017) በዴንማርክ ኮፐንሀገን የደብረ ምሕረት ቅዱስ አማኑኤል ደብር የአዲሱን ዓመት ክብረ በዓል ምክንያት በማድረግ ዐቢይ የርእሰ አውደ ዓመት ጉባኤ አድርጓል። የጉባኤውም መሠረታዊ ዓላማ በሥራ፣ በትምህርት እና በተለያዩ የኑሮ ሁኔታዎች ከአገር ርቀው ያሉ “ዝርዋን ምዕመናንን” […]

ሀገረ ስብከቱ ፬ኛ ዓመታዊ ጠቅላላ ጉባኤውን አካሄደ።

በጀርመን ንዑስ ማእከል መስከረም 3 ቀን 2010 ዓ.ም. በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በምሥራቅ፣ ምዕራብና ደቡብ አውሮፓ ሀገረ ስብከት ፬ኛ ዓመታዊ ጠቅላላ ጉባኤውን  ዓርብ ነሐሴ 26 እና ቅዳሜ ነሐሴ 27 ቀን 2009 ዓ/ም የሀገረ ስብከቱ መቀመጫ በሆነችው በጀርመኗ ሮሰልስሀይም ከተማ አካሄደ። በዚህ ዓመታዊ ጉባኤ የሀገረ ስብከቱ ልዩ ልዩ ሓላፊዎች፣ የአድባራት አስተዳዳሪዎችና የሰበካ ጉባኤ ተወካዮች የተገኙ ሲሆን […]

የስዊዘርላንድ ግንኙነት ጣቢያ አዉደ ርዕይ አካሄደ።

 በስዊዘርላንድ ግንኙነት ጣቢያ መስከረም 1 ቀን 2010 ዓ.ም. ነሐሴ ፳ እና ፳፩ ፳፻፱ በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤ/ማ/ መምሪያ ማኅበረ ቅዱሳን አዉሮፓ ማእከል የስዊዘርላንድ ግንኙነት ጣቢያ ከስዊዘርላንድ የሎዛን ደብረ ኃይል ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን ጋር በመተባበር በስዊዘርላንድ ሀገር ለሁለተኛ ጊዜ ልዩ የአብነት እና የገዳማት ቀን በሎዛን ከተማ አካሂዷል። የዕለቱ መሪ ቃል ”ኑ አብረን እንስራ፤ ለውጥም እናመጣለን” የሚል ነበር። መርሐ […]

በእንግሊዝ ሀገር የመጀመሪያው ሐዊረ-ሕይወት ተካሄደ

በዩናይትድ ኪንግደም ንዑስ ማእከል ነሐሴ 8 ቀን 2009 ዓ.ም. በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤ/ማ/ መምሪያ ማኅበረ ቅዱሳን አዉሮፓ ማእከል የዩናይትድ ኪንግደም ንዑስ ማእከል ያዘጋጀዉ የመጀመሪያ ዙር የሐዊረ-ሕይወት መርሐ ግብር ሐምሌ 29 ቀን 2009 ዓ.ም. በዩናይትድ ኪንግደም የግብጽ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ማእከል (ስቲቪኔጅ) ተካሄደ። በተለያዩ የእንግሊዝ ከተሞች የሚኖሩ ከ200 በላይ የሚሆኑ ምእመናን መነሻቸዉን ለንደን እና በርሚንግሃም ከተሞች ባደረጉ አራት አዉቶቡሶች […]

በማኅበረ ቅዱሳን የአውሮፓ ማዕከል 17ኛውን ጠቅላላ ጉባኤውን አካሄደ።

በአውሮፓ ማእከል ኅ/ኤ/ሚዲያ ክፍል ሐምሌ 8 ቀን 2009 ዓ.ም. በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደረጃ መምሪያ ማኅበረ ቅዱሳን የአውሮፓ ማእከል አስራ ሰባተኛውን ጠቅላላ ጉባኤ “ታገኙ ዘንድ ሩጡ “፩ቆሮ ፱÷፳፬  በሚል መሪ ቃል በጀርመን ክሮፍልባህ የግብፅ ቅዱስ እንጦስ ገዳም የአካባቢው አቢያተ ክርስቲያናት አስተዳዲሪዎች ፣ የሀገረ ስብከቱ ተወካይ፣ የማኅበሩ አባላት እና ተጋባዥ እንግዶች በተገኙበት ከዓርብ ሰኔ ፴ እስከ እሁድ […]

የጣሊያን ንዑስ ማእከል አውደ ርእይ አካሄደ

በጣሊያን ንዑስ ማእከል ሰኔ 25 ቀን 2009 ዓ.ም. ማኅበረ ቅዱሳን የጣሊያን ንዑስ ማእከል ግንቦት ፲፱ እና ፳ ፳፻፱ ዓ/ም ከሮም ደብረ ጽዮን ቅድስት ማርያም እና ቅዱስ ኡራኤል ቤተክርስቲያን ጋር በመተባበር “ አብረን እንስራ ለውጥም እናመጣለን!” በሚል መሪ ቃል ዐውደ ርእይ አካሄደ። ዐውደ ርእዩ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በሕገ ልቡና በሕገ ኦሪትና በሕገ ወንጌል ያደረገችው ጉዞ፣ የገዳማትና አብነት […]