Entries by Website Team

በአውሮፓ ተወልደው ላደጉ የአብነት ተማሪዎች ሢመተ ዲቁና ተሰጠ

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በስዊድንና ስካንዴኒቪያን ሀገረ ስብከት የኦስሎ መካነ ቅዱሳን ቅዱስ ገብርኤል ወአቡነ ተክለሃይማኖት ቤተክርስቲያን በአውሮፓ ተወልደው ላደጉ ሰባት የአብነት ተማሪዎች ዲቁና ተሰጠ።  ለ 4 ዓመታት የአብነት ትምህርታቸውን ሲከተታሉ ለነበሩት ሰባት አዳጊ የአብነት ተማሪዎች ኅዳር 28 ቀን 2012 ዓ.ም. በሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ በብጹዕ አቡነ ኤልያስ ማዕርገ ዲቁና ተሰጥቷል፡፡  የኢጣሊያና አካባቢው ሀገረ ስብከት […]

በፍራንክፈርት ከተማ ዐውደ ርእይ ተካሄደ

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ማኅበረ ቅዱሳን በአውሮፓ ማእከል የጀርመን ንኡስ ማእከል አዘጋጅነት “ኦርቶዶክሳዊት ተዋህዶ ቤተክርስቲያንን አስተምህሮዋን እንጠንቅቅ፤ ድርሻችንን እንወቅ” በሚል መሪ ቃል ኅዳር 28 ቀን 2012 ዓ.ም. በፍራንክፈርት ምስካየ ኅዙናን መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን ዐውደ ርእይ ተካሄደ:: ዐውደ ርእዩን የጀርመን እና አካባቢው ሀገረ ስብከት ሥራ አስኪያጅና የደብሩ አስተዳዳሪ መልአከ መዊዕ ልሳነ […]

በቅድስት ቤተ ክርስቲያን እየደረሰ ያለውን ጥቃት በመቃወም በተለያዩ የአውሮፓ አገራት ሰላማዊ ሰልፍ ተደረገ፡፡

መንግሥት የዜጎችን ደኅንነት የማስጠበቅ ግዴታ ያለበት በመሆኑ በአገር ቤት በምትገኘው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን እና በልጆቿ ላይ እየደረሰ ያለውን ጥቃት የኢትዮጵያ መንግሥት እንዲያስቆም፣ አብያተ ክርስቲያነቱን ያቃጠሉ በልጆቿ ላይም ግፍን ያደረጉ ሰዎችን ለፍርድ እንዲያቀርብ ለመጠየቅ በአውሮፓ በሚገኙ ሦስቱ አህጉረ ስብከት (የስዊድንና የስካንዴኒቪያን ሀገረ ስብከት ፣ ጀርመንና አካባቢው ሀገረ ስብከት እና የጣልያንና አካባቢው ሀገረ ስብከት) አስተባባሪነት […]

ሁለቱ እንስሶች

በአስናቀች ታመነ ምንጭ: ስምዐ ጽድቅ ጋዜጣ ከሰኔ 16 – 30/ 2011 ዓ.ም. ዕትም ሰላም ልጆች እንደምን አላችሁ? ደኅና ናችሁ ለዚህ ቀን ያደረሰን እግዚአብሔር ይመስገን! አሜን! ልጆች ዛሬ ከሌላው ቀናት የተለየ ታሪክ ይዘንላችሁ ቀርበናል። ጽሑፉን ከማንበባችሁ በፊት አስቀድማችሁ እስቲ ገምቱ ስለምን ይመስላችኋል፧ ስለቅዱሳን ሰዎች ካላችሁ እንደዛ አይደለም። ስለምን እንደሆነ ልንገራችሁ ስለ እንስሳት ነው። ስለየትኞቹ እንስሳት ካላችሁኝ […]

የመስቀሉ ነገር ለምናምን ለእኛ የእግዚአብሔር ኃይል ነው ። (1ኛ ቆሮ 1፥18)

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን። እንኳን ለጌታችን ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የመስቀል በዓል በሰላም አደረሳችሁ። በዲያቆን ዮሐንስ አያሌው ቤተ ክርስቲያናችን በዓለ እግዚአብሔርን በማክበር ነገረ እግዚአብሔርን፤ በዓለ ቅዱሳንን በማክበር ነገረ ቅዱሳንን፤ በዓለ መስቀልን በማከበር ነገረ መስቀሉን ታስተምራለች። በበዓለ መስቀሉ እና በሌሎችም በመንፈሳዊ በዓላት አከባበሯ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በሰማይ ላይ ደምቃ እንደምታበራ ፀሐይ […]

Celebration of the Feast of the Cross

In the Name of the Father and the Son and the Holy Spirit, One God. Amen. Celebration of the Feast of the Cross The Ethiopian Orthodox Tewahido Church is the treasure of the grace of God and riches of apostolic Traditions. The church is the kingdom of God on the earth and serves as a […]

‹‹ዮም መስቀል ተሰብሐ፤ ዓለም ተጸውአ፤ ወሰብእ ግዕዘ፡፡›› ቅዱስ ያሬድ

‹‹ዮም መስቀል ተሰብሐ፤ ዓለም ተጸውአ፤ ወሰብእ ግዕዘ፡፡ – ዛሬ መስቀል ከበረ፤ ዓለም ለድኅነት ተጠራ፤ ሰውም ነጻ ወጣ፡፡›› ቅዱስ ያሬድ ‹‹መስቀል›› የሚለውን ቃል አለቃ ኪዳነ ወልድ በመዝገበ ቃላታቸው በቁሙ፤ መስቀያ፤ መሰቀያ፤ ለሞት የሚያበቃ መከራ በማለት ተርጉመውታል፡፡ (ገጽ.፰፻፹፫) መንፈሳዊና ምሥጢራዊ የመስቀልን ትርጉም በሰፊው ያብራሩት ደግሞ ኢትዮጵያዊው ቄርሎስ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ ናቸው፡፡ በውዳሴ መስቀል ድርሰታቸው ከሰጡት ማብራሪያ ጥቂቱን […]

፮ተኛው ሐዊረ ህይወት በጀርመን ሀገር ሆክስተር ከተማ ተካሄደ።

ሚያዚያ 17 ቀን 2011 ዓ.ም በጀርመን ንዑስ ማዕከል በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ/ሰ/ት/ቤ/ማ/መ/ ማኅበረ ቅዱሳን አውሮፓ ማዕከል የጀርመን ንዑስ ማዕከል ያዘጋጀው፥ ፮ተኛው ሐዊረ ህይወት በጀርመን -ከሃኖቨር  ከተማ 90 ኪሜ ርቀት ላይ በምትገኘው ሆክስተር ከተማ በሚገኘው የግብጽ ኦርቶዶክስ ቅድስት ማርያም እና ቅዱስ ማውሪስ ገዳም ከሚያዚያ ፬ እስከ ፮ ድረስ በተሳካ ሁኔታ ተካሄደ። ዓርብ ማምሻውን አባቶች ካህናት በተገኙበት በጸሎት ተከፍቶ፥ ሊቀ […]

የሆላንድ ንዑስ ማዕከል ዓውደ ርዕይ አካሄደ

ሚያዚያ 07 ቀን 2011 ዓ.ም በሆላንድ ንዑስ ማዕከል በሆላንድ አምስፎርት ከተማ “ኦርቶዶክሳዊት ተዋህዶ ቤተክርስቲያንን አስተምሮዋን እንጠንቅቅ፣ ድርሻችንን እንወቅ” በሚል ርዕስ ዓውደ ርዕይ ተካሄደ፡፡በሐመረ ኖህ ቅድስት ማርያም ቤተክርስቲያን ውስጥ ቅዳሜ ፳፩ / ፪ሺ፲፩ ዓም የተደረገው ይህ ዐውደ ርእይ ቀድሞ ከተካሄደው አውደ ርእይ ከረጅም ጊዜ በኋላ ቆይቶ የተካሄደ መሆኑን የቆዩ የንዑስ ማዕከሉ አባላት ይናገራሉ። በአራት ክፍል የተዘጋጀው […]

የጀርመን ንዑስ ማዕከል ሦስተኛውን ዐውደ ርዕይ በሙኒክ ከተማ አካሄደ።

ሚያዚያ 02 ቀን 2011 ዓ.ም በጀርመን ንዑስ ማዕከል “ቤተ ክርስቲያናችንን እንወቅ አስተምህሮዋን እንጠንቅቅ” በሚል መሪ ቃል፥ የተዘጋጀው ዐውደ ርእይ በተለያዩ የዓለማችን ክፍሎች ለሚገኙ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን በማኅበሩ ንዑሳን ማዕከላት አስተባባሪነት እየቀረበ የሚገኝ ሲኾን፥ ዋና ዓላማውም ቤተክርስቲያንን ለምዕመናን በማስተዋወቅ አስተምህሮዋንና ኹሉን ዓቀፍ ህልውናዋን ለማስቀጠል የበኩሉን አስተዋጽዖ ለማድረግ ነው። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አስተምህሮና ማንነት፤ ሐዋርያዊ […]