Entries by Website Team

የዐቢይ ጾም ሳምንታት (ለሕፃናት) : – ክፍል ሦስት

በልደት አስፋው መጋቢት ፳፪ ቀን ፳፻፲፫ዓ.ም እንደምን ሰነበታችሁ ልጆች? ባለፈው ዝግጅታችን ከመጀመሪያው እሑድ እስከ ሦስተኛው እሑድ (ከዘወረደ ጀምሮ እስከ ምኵራብ) ድረስ የሚገኙትን የዐቢይ ጾም ሳምንታት የሚመለከት ትምህርት አቅርበንላችሁ ነበር፡፡ ዛሬ ደግሞ አራተኛውን የዐቢይ ጾም ሳምንት (መጻጕዕን) የሚመለከት ትምህርት ይዘንላችሁ ቀርበናል፡፡ መልካም ንባብ! ፬. መጻጕዕ ልጆች! አራተኛው የዐቢይ ጾም ሳምንት ‹‹መጻጕዕ›› ይባላል፡፡ መጻጕዕ ማለት በሽተኛ ማለት […]

የዐቢይ ጾም ሳምንታት (ለሕፃናት) – ክፍል ሁለት

በልደት አስፋው መጋቢት ፲፰ ቀን ፳፻፲፫ ዓ.ም እንደምን ሰነበታችሁ ልጆች? ደኅና ናችሁ? እግዚአብሔር ይመስገን!፡፡ ልጆች! በልዩ ልዩ ምክንያት አልችል ብለን ዘግይተናል፡፡ በቅድሚያ በገባነው ቃል መሠረት ወቅቱን ጠብቀን ትምህርቱን ባለማቅረባችን እናንተን ይቅርታ እንጠይቃለን፡፡ ልጆች! የካቲት ፲፩ ቀን ፳፻፱ ዓ.ም ባቀረብንላችሁ ትምህርት ከሰባቱ አጽዋማት መካከል ዐቢይ ጾም አንዱ እንደኾነ፣ ዐቢይ ጾም ማለት ታላቅ ጾም ማለት እንደኾነ፣ ጾሙ ጌታችን አምላካችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ […]

ዐቢይ ጾም ለሕጻናት

በልደት አስፋው                                                        መጋቢት ፩ ቀን ፳፻፲፫  ዓ.ም እንደምን ሰነበታችሁ ልጆች? ባለፈው ሳምንት ስለ ነቢዩ ዮናስ እና ስለ ነነዌ ሰዎች የጻፍንላችሁን ታሪክ አነበባችሁት? ጎበዞች፡፡ ከታሪኩ ውስጥ ያልገባችሁ ትምህርት ካለ ከቤተ ክርስቲያን መምህራን በመጠየቅ መረዳት ትችላላችሁ፡፡ በዛሬው ዝግጅታችን ደግሞ ስለ ዐቢይ ጾም አጭር ትምህርት ይዘንላችሁ ቀርበናል፤ ልጆች! ‹‹ዐቢይ ጾም›› ማለት ታላቅ ጾም ማለት ነው፡፡ ዐቢይ ጾም በቤተ […]

የጥምቀት በዓል በዮርዳኖስ ወንዝ

ጥር 11 ቀን 2013 ዓ.ም. ከወልደ ኢየሱስ /ቤካ ፋንታ/ ልጆችዬ እንኳን ለጥምቀት በዓል በሰላም አደረሳችሁ! ዛሬ ስለ ታላቁ በዓል ስለ ጥምቀት ብዙ የምነግራችሁ ነገር አለኝ፡ ፡ በደንብ ተከታተሉኝ እሺ፡፡ በገዳም ውስጥ ለሠላሳ ዓመት ለብቻው ሆኖ እግዚአብሔርን እያመሰገነ የሚኖር የእግዚአብሔር አገልጋይ ነበር፡፡ ስሙም ቅዱስ ዮሐንስ ይባላል፡፡ ልጆችዬ የቅዱስ ዮሐንስ ልብስ ምንድር መሰላችሁ የግመል ቆዳ ነበረ፣ የሚበላው […]

የሕፃኑ የኢየሱስ ልደት

ታኅሣሥ 26 ቀን 2005 ዓ.ም. ከወልደ ኢየሱስ /ቤካ ፋንታ/ “እነሆ ድንግል ትፀንሳለች ልጅም ትወልዳለች ስሙንም አማኑኤል ትለዋለች” ማቴ.1፥23ልጆችዬ እንደምን ሰነበታችሁ? ዛሬ ስለ ታላቁ ሕፃን ልደት የምነግራችሁ ነገር አለና በማስተዋል ተከታተሉኝ እሺ፡፡ ጎበዞች! የዛሬ ሁለት ሺ ዓመት ገደማ ነው፡፡ በኢየሩሳሌም ሀገር ንጉሡ ሄሮድስ ሕዝቡን ሁሉ ቤተልሄም ወደምትባል ከተማ ጠራቸው፡፡ እመቤታችንም በዚያ ጊዜ የአሥራ አምስት/15/ ዓመት ልጅ […]

ወላጆች ልጆቻችንን በመንፈሳዊ መንገድ እንዴት እናስተምር?

ዲያቆን ዮሴፍ ከተማ ወላጆች ለወለድናቸው ልጆች ትልቅ አምላካዊ አደራ አለብን፡፡እግዚአብሔርም ልጅን ያህል ትልቅና የደስታ ምንጭ የሆነ ስጦታ ሲሰጠን ደግሞ ከትልቅ ኃላፊነት ጋር ነው፡፡ ከኃላፊነታችን ትልቁ ለልጅ፡- ሃይማኖትን፤ ምግባርና ትሩፋትን በማስተማር ለእግዚአብሔር መንግሥት እንዲበቃ አድርጎ በፈሪሀ እግዚአብሔር ማሳደግ ነው፡፡ «ልጅን በሚሄድበት መንገድ ምራው፤ በሸመገለም ጊዜ ከእርሱ ፈቀቅ አይልም» እንዲል ምሳ. ፳፪፥፮፡፡ በዘመናችን መንፈሳዊ እሴቶች ተሸርሽረው በአብዛኞቹ […]

መስቀል (ለሕፃናት)

መስከረም 15 ፣ 2013 ብንያም ፍቅረ ማርያም ምንጭ ማኅበረ ቅዱሳን ዋናው ማዕከል። እንደምን ሰነበታችሁ ልጆች? እግዚአብሔር ይመስገን፡፡ እንኳን ከዘመነ ዮሐንስ ወደ ዘመነ ማቴዎስ በሰላም አሸጋገራችሁ፡፡ ትምህርት ቤት ተከፍቶ በአዲስ ደብተር፣ በአዲስ እስክርቢቶ፣ በአዲስ ልብስ … ስትማሩ ምን ተሰማችሁ? በጣም ያስደስታል አይደል? ይህ ሁሉ የሆነው እግዚአብሔር አዲስ ዘመን አዲስ ዓመት ስለሰጠን ነው፡፡ መስከረም 17 የሚከበረው የመስቀል በዓልም […]

ሕጻናትን ማስተማር እንዴት እና ለምን?

ለሕጻናት መምህራን የተዘጋጀ ስልጠና :https://us02web.zoom.us/j/86806058604 ከጀርመንና አካባቢው ሀገረ ስብከት የሕፃናትና የወጣቶች ክፍል ጉዳዩ:- የህጻናት አስተማሪዎች ስልጠና Zoom-Meeting መቼ: 1.Aug.2020 08:30 PM Paris ወደ መርሐ ግብሩ ክፍል ውስጥ ለመግባት Join Zoom-Meeting ይህን መስፈንጠሪያ (Link) ይጠቀሙ https://us02web.zoom.us/j/86806058604 ወይም የሚቀጥለውን ID በመስጠት ወደ መርሐ ግብሩ መግባት ይቻላል:: Meeting-ID: 868 0605 8604 One tap to join Audio: ምናልባት በዙም […]

ጰራቅሊጦስ (ለሕፃናት)

ከሰኔ 14 ቀን 2005 ዓ.ም. በድጋሚ የተለጠፋ በቤካ ፋንታ እግዚአብሔር የሠራት ቀን ይህች ናት/ መዝ 118፥24/ ይህች ታላቅ ዕለት  ከቅድስት ሥላሴ አንዱ አካል የሆነው እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ለቅዱሳን ሐዋርያት፣ ለቅዱሳን አርድእትና ለቅዱሳት ሴቶች የተገለጠባት ዕለት ናት፡፡    እነዚህ ሁሉ በጸሎት ተግተው በሚጸልዩበት ወራት መንፈስ ቅዱስ  በተከፋፈሉ የእሳት ልሳን አምሳል የወረደበት ቅዱስ ቀን ነው፡፡ አስቀድሞ ጌታችን አምላካችን […]