በእንግሊዝ ሀገር የቨርችዋል ግቢ ጉባኤ ተማሪዎች ተመረቁ

ከዩኬ ንዑስ ማእከል 

ነሐሴ ፩ ቀን ፳፻፲፫ ዓ.ም

ተመራቂ የግቢ ጉባኤ ተማሪዎች (በከፊል) ከአባቶች ጋር

በማኅበረ ቅዱሳን አዉሮፓ ማእከል በዩናይትድ ኪንግደም ን/ማእከል አስተባባሪነት ላለፉት ሦስት ዓመታት ተከታታይ የቤተ ክርስቲያን ትምህርት ሲማሩ የነበሩ 11 የግቢ ጉባኤ ተማሪዎች ሐምሌ 24 ቀን 2013 ዓ/ም በአባቶች ቡራኬ ተመረቁ። በለንደን ደብረ ገነት ቅድስት ሥላሴ ቤተ ክርስቲያን አዳራሽ በተካሄደዉ በዚህ የተማሪዎች ምርቃት መርሐ ግብር ላይ ካህናት አባቶች፣ ተመራቂ ተማሪዎችና የተመራቂ ቤተሰቦች፣ ጥሪ የተደረገላቸዉ እንግዶች፣ የማኅበረ ቅዱሳን አባላት፣ ሌሎች የግቢ ጉባኤ እንዲሁም የሰ/ት/ቤት ተማሪዎች የተገኙ ሲሆን ሌሎች የአዉሮፓ ማእከል አባላት እና ታዳሚዎች መርሐ ግብሩን በዙም (Zoom) ተከታትለዋል። የአዉሮፓ ማእከል ሰብሳቢ ዲ/ን ፈንታ ጌቴ ለተመራቂዎች የ’እንኳን ደስ ያላችሁ’ መልእክት አስተላልፈዋል። በዚህም ተመራቂዎች ወደ ማኅበረ ቅዱሳን ተቀላቅለዉ የማኅበሩን አገልግሎት እንዲያግዙ ጥሪ አቅርበዋል።

ትምህርት በመልአከ ሰላም ቀሲስ አዲስ ሲሰጥ

በዚህ የምረቃ መርሐ ግብር ላይ፣ መልአከ ሰላም ቀሲስ አዲስ አበበ የለንደን ደብረ ገነት ቅድስት ሥላሴ ቤተ ክርስቲያን አገልጋይና የስብከተ ወንጌል ኃላፊ ትምህርት ሰጥተዋል። በተጨማሪም ተማራቂዎችና የፍሬ ሃይማኖት ሰ/ት/ቤት ተማሪዎች መዝሙር ያቀረቡ ሲሆን በግቢ ጉባኤ በመምህርነት ከሚያገለግሉት አባቶች መካከል መልአከ ሣህል ቀሲስ ዶ/ር ያብባል ሙሉዓለም እና ሊቀ ኅሩያን ቀሲስ ፍስሐ ለተመራቂዎች መልእክት አስተላልፈዋል።

 

ለተመራቂዎች የመስቀል ስጦታ በአባቶች ሲሰጥ

 

ለተመራቂዎች የመስቀል ስጦታ በአባቶች አማካኝነት ተበርክቷል። በን/ማእከሉ የተተኪ ትዉልድ እና ግቢ ጉባኤ ክፍል ተወካይ ለመርሐ ግብሩ ታዳሚዎች መልእክት ያስተላለፉ ሲሆን በዚህም ለግቢ ጉባኤዉ ስኬት አስተዋጽኦ ያደረጉትን መምህራንና ሌሎች አካላትን በሙሉ አመስግነዋል። ለምረቃ መርሐ ግብሩ የቤተ ክርስቲያኑን አዳራሽ ለፈቀደው የቤተ ክርስቲያኒቱ ሰበካ ጉባኤ ጽ/ቤት ምስጋናቸዉን አቅርበዋል።

የተተኪ ትዉልድ ንዑስ ክፍል ባለፈዉ ዓመት ዕድሜያቸዉ ሰባት ዓመት እና ከዚያ በላይ የሆኑ ከሦስት መቶ በላይ የሚደርሱ ህጻናትን፣ በየዕድሜያቸዉ ለይቶ የቤተ ክርስቲያንን ትምህርት በእንግሊዘኛ ቋንቋ ሲሰጥ መቆየቱን አስታዉሰዉ ትምህርቱን በተጠናከረ መልኩ ለማስቀጠል ምዝገባ እየተካሄደ መሆኑን ገልጸዋል። በግቢ ጉባኤ ንዑስ ክፍልም እንዲሁ አዳዲስ የአንደኛ ዓመት ተማሪዎችን ለመመዝገብ ዝግጅት ማጠናቀቁን ገልጸዉ ይህንን የምዝገባ መልእክት በማስተላለፍ ሁሉም አካላት እንዲተባበሩ ጠይቀዋል።

የ’ቨርችዋል’ ግቢ ጉባኤዉ በዩኬ በመጀመሩ ምክንያት የዘንድሮ ተመራቂዎች ሁሉም ከዩኬ ሲሆኑ፣ ከሁለት ዓመት በፊት ጀምሮ፣ ግቢ ጉባኤዉ በሌሎች የአዉሮፓ አገሮች ያሉ ተማሪዎችን ያካተተ በመሆኑ አሁን ላይ ወደ አዉሮፓ ግቢ ጉባኤነት ያደገ መሆኑን ገልጸዋል።

በኮሮና ቫይረስ (COVID 19) ሳቢያ በአውሮፓ የምትገኘውን ቤተ ክርስቲያን (ምእመናን) ሊያጋጥሙ የሚችሉ ተግዳሮቶች እና መፍትሔዎች

የመስቀሉ ነገር ለምናምን ለእኛ የእግዚአብሔር ኃይል ነው ። (1ኛ ቆሮ 1፥18)

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን።

እንኳን ለጌታችን ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የመስቀል በዓል በሰላም አደረሳችሁ።

በዲያቆን ዮሐንስ አያሌው

ቤተ ክርስቲያናችን በዓለ እግዚአብሔርን በማክበር ነገረ እግዚአብሔርን፤ በዓለ ቅዱሳንን በማክበር ነገረ ቅዱሳንን፤ በዓለ መስቀልን በማከበር ነገረ መስቀሉን ታስተምራለች። በበዓለ መስቀሉ እና በሌሎችም በመንፈሳዊ በዓላት አከባበሯ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በሰማይ ላይ ደምቃ እንደምታበራ ፀሐይ ናት። ፀሐይ በጨለማው ሰማይ ላይ ብርሃኗን በመፈንጠቅ የቀን ብርሃንና ውበት እንደምትሰጥ ቤተ ክርስቲያናችንም መንፈሳዊ ብርሃኑ በጠፋበት ዓለም የክርስትና ጸጋዋን እያጎናጸፈች ለጨለማው ዓለም ታበራለች። መንፈሳዊ በዓላትን ማክበር ወንጌልን መስበክ ነው። የቀደሙት ክርስቲያኖች ወንጌልን እንደልብ መስማት በማይችሉበት ዘመን በሰሙት ጥቂት ቃለ እግዚአብሔር ከአምላካቸው ጋር ይገናኙ የነበሩት በዓለ መስቀልንና በዓለ ቅዱሳንን በማክበርና መታሰቢያቸውን በማድረግ ነበር። 

ቅዱስ ጳውሎስ የመስቀሉ ነገር በሚጠፉ ሰዎች ዘንድ ስንፍና ነውና፣ ለምንድነው ለእኛ የእግዚአብሔር ኃይል ነው (1ኛ ቆሮ 1፥18) ብሏል። መስቀል በዘመነ ኦሪት ክፉ ይባሉ ከነበሩትና በሐዲስ ኪዳን አምላካችን የሕይወት መገኛ ካደረጋቸው ነገሮች አንዱ ነው። እግዚአብሔር ኢየሱስ ክርስቶስ በመስቀሉ ላይ ተሰቅሎ ከጨለማው ዓለም አውጥቶናል። በመሆኑም ዛሬ መስቀል የብርሃን እና የድል ምልክት ነው። በኃጢአቱ ምክንያት ከአምላኩ እርቆ የነበረውን አዳምን በዲያብሎስ ግዞት ከሚደርስበት መከራ ክብር ምስጋና ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመስቀል ላይ ራሱን መሥዋዕት አድርጎ አድኖታል (ሉቃ. 22፥52)። በዚህም “ፈደየ እዳነ በመስቀሉ” በመስቀሉ እዳችንን ከፈለ እያልን እናመሰግነዋለን። ብርሃነ ዓለም ቅዱስ ጳውሎስ “በመስቀሉ ጥልን አጠፋ”(ኤፌ. 2፤16) ብሎ እንዳስረዳን መስቀል ዛሬም ጥልንና ጥፋትን የሚያመጡ ወንበዴዎች ሰይጣናት የሚጠፉበት ነው። “ከባላጋራችን የተነሳ በእዛዝ የተጻፈውን የዳችንን ደብዳቤ ደመሰሰልን፣ ከመካከላችንም አራቀው፣ በመስቀሉም ቸነከረው” (ቆላ. 2፤14) እንደተባለ ዛሬም ወንበዴዎች አጋንንትን በኃይሉ ቸንክረን አስረን በሰላም እንድንኖር የሚያስችለን ታላቁ የሰላማችን አምባ መስቀል ነው። መስቀል ኃይል፣ ጸወን (አምባ፣ መጠጊያ፣ መሸሸጊያ፣ ማምለጫ) ነው።

መስቀል ዓለሙ የተቀደሰበት ዛሬም የሚቀደስበት የቅድስናና መንፈሳዊ ሀብታት መገኛ መኾኑን ኢትዮጵያዊው ሊቅ ቅዱስ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ ውዳሴ መስቀል በተሰኘ መጽሐፋቸው ሲመሰክሩ “አማንኬ ይደሉ ከመ ይስቅሉ ለወልደ እግዚአብሔር እስመ በመስቀሉ ይቄድሶ ለዓለም” በእውነት ኢየሱስ ክርስቶስ ዓለሙን ይቀድሰው ዘንድ በመስቀል ላይ መሰቀሉ የተገባ ነበር። ይኽም የተገባ የኾነው ኢየሱስ ክርስቶስ እንደ አዳም በድሎ፤ እንደ ቃየል ገድሎ፤ እንደ ይሁዳ አታሎ ሳይሆን በመስቀሉ ዓለሙን ኹሉ ይቀድሰው ዘንድ ነው።” በማለት ርኩሳን ይሰቀሉበት የነበረውን የጥፋት መሳሪያ ዓለምን የሚቀድስ መንፈሳዊ የውጊያ መሳሪያ እንዳደረገው ገልጸውልናል። ሌሎች ሊቃውንትም “ወለእመ ኢተሰቅለ እመ ኢድኅነ ባይሰቀልስ ኖሮ ባልዳንን ነበር፣ በማለት የሚያስተምሩን ይህንን እውነት ገልጦ ለማስረዳት ነው።

ለቅዱስ መስቀሉ በዓሉን እንድናከብር ብቻ ሳይኾን የጸጋ ስግደት እንድንሰግድለትም ታዝዘናል። ይህንንም ያዘዙን ቅዱስ ወንጌልን ያስተማሩ ሐዋርያት መኾናቸውን ቤተ ክርስቲያናችን ትመሰክራለች። መስተብቍዕ ዘመስቀል በተባለው የቤተ ክርስቲያናችን የጸሎት ክፍል የተገለጠውን ስንመለከት “አዘዙነ መምህራ ቅዱስ ወንጌል አምሳለ ፈጣሪ ልዑል ንስግድ ለመስቀል ወለማርያም ድንግል ለማርያምሰ ዘንሰግድ ላቲ እስመ ነሥአ ሥጋ እም ሥጋሃ እግዚአብሔር ፈጣሪሃ ወረከብነ መድኃኒተ እምኔሃ ለዕፀ መስቀልኒ እስመ አንጠብጠበ ደመ ቃል” – የቅዱስ ወንጌል አስተማሪዎች ቅዱሳን ሐዋርያት/መምህራን ለድንግል ማርያምና ለመስቀል እንድንሰግድ አዘዙን። ለድንግል ማርያም የምሰግድላት እግዚአብሔር ከሥጋዋ ሥጋን ከነፍስዋም ነፍስን ነስቶ ሰው ስለኾነና ሰው በመኾኑም ከእርሷ መድኃኒትን ስላገኘን ነው። ለመስቀል የምንሰግደውም አካላዊ ቃል እግዚአብሔር ወልድ አዳኝ ፈራጅ የኾነ ቅዱስ ደሙን ስላንጠበጠበበት ነው ተብሎ ተብራርቶ ተጽፎልን  እናገኘዋለን። (መስተብቍዕ ዘመስቀል)

መስቀል ከላይ እንዳየነው በብሉይ ኪዳን ወንበዴዎች የሚቀጡበት መቀጣጫ የነበረ ቢኾንም የሐዲስ ኪዳን ሕይወትነቱን ለመግለጥ በዘመነ ኦሪትም ብዙ መንፈሳዊ ተአምራት ይፈጸሙበት ነበር። ለምሳሌ፦ በራፌድ በረሃ ሙሴ ከአማሌቃውያን ጋር በተዋጋ ጊዜ እጁን በትምእርተ መስቀል አምሳል በመዘርጋት አማሌቃውያንን ድል ነስቷቸዋል።(ዘጸ 17813) ስለዚህም “መሰቀል ዘተገብረ በአምሳሊሁ ለእደ ሙሴ በገዳመ ራፌድ በእንተ ጸብአ አማሌቅ” – በአማሌቃውያን ጥል ምክንያት በገዳመ ራፌድ በሙሴ እጆች አምሳል የተዘረጋ ቅዱስ መስቀል ነው ተብሎለታል። ሊቀ ነቢያት ሙሴ የማራን ውኃም እንጨት በመስቀል አምሳል አመሳቅሎ በመጣል ከመራራነቱ ፈውሶታል።(ዘጸ 152325) ይኸም “መስቀል ዘአጥዐሞ ለማይ መሪር በገዳመ ሱር ሶበ ተወደየ ውስቴቱ በእደ ሙሴ” በነብዩ በሙሴ እጅ ተመሳቅሎ ወደ ውስጡ በተጣለ ጊዜ መራራውን የሱር ውኃ ያጣፈጠው መስቀል ነው ተብሎለታል።(ውዳሴ መስቀል) የሱርን (የማራን) ውኃ እንዳጣፈጠ ዛሬም መስቀሉ የብዙዎችን መራራ ሕይወት ወደ መንፈሳዊ ጥፍጥና ይለውጣል። ነብዩ ሙሴ የሠራው የነሃስ እባብና መስቀሉም ዕፀ መስቀል እባብ የተባለ የሰይጣንን ተንኮል የምናልፍበት ከንክሻውም የምንድንበት መሆኑን ማሳያ ነው። በአጠቃላይ መስቀል ለክርስቲያኖች  ሕይወታችን ነው። በተጨማሪም መስቀል፦

 • ክርስቶስ የሚያበራበት ተቅዋመ ወርቅ (የወርቅ መቅረዝ) ነው።

ኢየሱስ ክርስቶስ “እኔ የለም ብርሃን ነኝ”። በብርሃኔ ተመላለሱ ብሎናል። ፀሐይ የሚሽከረከረው በነፋሳት እንደኾነ መብራት የሚበራውም በመቅረዝ (ማብሪያ) ላይ ኾኖ ነው። ኢየሱስ ክርስቶስ የዓለም ብርሃን ሲኾን ብርሃኑ የተገለጠበት ማብሪያው ደግሞ መስቀሉ ነው። ይህን ይዞ ሊቁ ሲያደንቅ “ኢየሱስ ክርስቶስን ሊሰቅሉት ሥጋውን ከልብስ አራቆቱት ምክንያቱም ለመብራት የሚፈልገው ኹሉ እንዲያየው ከፍ ብሎ በተቀመጠ በመቅረዙ ላይ ኾኖ ማብራት እንጅ በልብስ ተሸፍኖ መቀመጥ አይገባውምና፤ ዳግመኛም ሊሰቅሉ በእንጨት ላይ አወጡት ለምን ካላችኹ መብራትን አብርተው በተራራ ላይ እንጅ ከእንቅብ በታች በምድር ላይ ሊያስቀምጡት አይገባም።”  “ተቅዋምሰ መስቀል ውቱ ወማኅቶትኒ አማኑኤል ውቱ ናንሦሱ እንከ በብርሃኑ ለወልደ እግዚአብሔር ወኩሎ ዘየአምን ኪያሁ ውስተ ብርሃን ይሐውር ወጽልመትኒ ኢይረክቦ ማብሪያ መቅረዙ መስቀል ነው፤ በቀራንዮ ተራራ ላይ በተተከለ የመስቀሉ መቅረዝ ላይ የሚያበራው ብርሃን ደግሞ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። ይህንን ተረድተን ኹላችንንም በብርሃኑ እንመላለስ በእርሱም እንመን። በእርሱ የሚያምን በብርሃን ይመላለሳል ጨለማም አይቀርበውም በማለት አስተምሮናል። (ውዳሴ መስቀል)

 • አስቀድሞ የሰውን ልጅ ለማዳን የተዘጋጀ ነው።

አባ ጊዮርጊስ ሔዋን “ሔዋን” ተብላ ስም የወጣላት በእመቤታችን በቅድስት ድንግል አማካኝነት እንደኾነ ኹሉ በመስቀሉ ያመነ ሕይወት እንዲሆነው ስላወቀ መስቀሉንም አስቀድሞ “ዕፀ ሕይወት” አለው በማለት መስቀሉ አስቀድሞ በአምላክ ዘንድ ተዘጋጅቶ እንደነበር ይመሰክራሉ። የተሰቀለው እርሱ አስቀድሞ ባዘጋጀው መስቀል እንደኾነ ሲገልጡም “አምጽኡ ዘዚአሁ ለዚአሁ፣ የራሱን ለራሱ አመጡለት” በማለት እያደነቁ ጽፈዋል።

 • ድኅነታችን የተጻፈበት ሕያው መጽሐፍ ነው።

የዕዳ ደብዳቤያችን አስቀድሞ በእብነ እርካብ ተጽፎ ነበር። መጽሐፍ ድኅነታችን ደግሞ በአምላካችን በደሙ ቀለምነት በመስቀል ላይ ተጽፏል። ለዚህ ነው ቅዱስ ጳውሎስ “የዕዳ ደብዳቤያችንን በመስቀሉ ጠርቆ አስሮ ከመንገዳችን አስወገደው”ብሎ የመሰከረው። ሌላኛው ሊቅም “በንጠብጣበ ደምከ ተጽሕፈ ምሕረትከ በሰሌዳ መስቀልከ፣ በመስቀልህ ሰሌዳ ላይ በደምህ ነጠብጣብነት  ምሕረትህ ተጻፈች” በማለት ይህንን እውነት አጽንተው አስተምረዋል።

 • የአምላካችን የፍቅሩ መግለጫ ነው።

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ለሰው ልጆች እንደ ክርስቶስ መስቀል ያለ የእግዚአብሔርን ፍቅር የሚያስረዳ (የሚገልጥ) ነገር የለም በማለት እንዳስረዳን፤ መስቀል የፍቅሩ መገለጫ ነው።( Commentary on 2nd Timothy) ቅዱስ ዮሐንስም “በወንጌሉ በእርሱ የሚያምን ኹሉ እንዲድን እንጅ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን ቤዛ አድርጎ እስከ መስጠት ድረስ እንዲሁ ዓለሙን ወዶታል” በማለት የመሰከረለትን የእግዚአብሔር ፍቅር (ዮሐ. 316) ያለ መስቀሉ መረዳት አይቻልም። እስከ መስቀል ድረስ የታመነ ሆነ የተባለውን መረዳት የሚቻለው ነገረ መስቀሉ ሲገባን ብቻ ነው። ነገረ መስቀሉን ሳንረዳ ወደ እምነት ልንመጣ አንችልም። የመስቀልህ ጥላ ፈያታዊ ዘየማንን አንተን ወደ ማመን መለሰው እንዳለ ሊቁ ዛሬም ወደ ንስሐና ወደ ተግባራዊ ክርስትና የሚያደርሰን ትልቁ ሀብታችን በመስቀሉ ላይ የሚያበራው የክርስቶስ ብርሃን በልቡናችን ውስጥ ሲያበራ ነው።   

 • የሥጦታዎች ኹሉ መገኛ ነው።

ሕይወት፤ ድኅነት፤ ትንሣኤ፤ ምልጃ፤ እርቅ፤ ተስፋ፤ ተድላ ገነት በመስቀሉ የተገኙ ናቸው። እመቤታችንና ሐዋርያት ሁሉም የተሰጡን ከመስቀል ስር ነው። ከመስቀሉ ስር ካለቅስን አብሮን የሚያለቅስ አናጣም። ሌላው መስቀሉ ኃጢአታችንን በመግለጥ ወደ ንስሐ ያደርሰናል። ከመስቀሉ ስንርቅ ግን የአምላካችን ውለታውን እንረሳዋለን።

 • የዳግም ምጽአት ምልክታችን ነው።

ክርስቶስ በፍጻሜ ዘመን በኅልቀተ ዓለም የሚመጣው ምልክት እያሳየ ነው። ይህንንም ቅዱሳት መጽሐፍት ሲመሰክሩልን “ክርስቶስ ይመጽ በደመና ሰማይ ምስለ ኃይል ወመላእክቲሁ ምስሌሁ ወመስቀሉ ቅድሜሁ አሜሃ እለ ወግዑከ ይበክዩ፤ ወእለሰ ይነስዑ ማኅተመ ስምከ ይከውን ሎሙ ሰላመ ወሣህለ እግዚአብሔር ኢየሱስ ክርስቶስ ከኃይሉ ጋር መስቀሉ በፊቱ እያበራ በክበበ ትስብእት በይባቤ መላእክት ይመጣል፤ ያንጊዜም የወጉት ያለቅሳሉ፤ የስሙን ማኅተም የያዙ ግን ሰላምና የእግዚአብሔር ምሕረት ይደረግላቸዋል በማለት ያስተምራሉ። (ራዕ 17 ዘካ 121) አምላካችን እኛንም ለቀኝ ቁመት፣ ከእግዚአብሔር የሚሰጠውን ሰላምና ምሕረትም ለመቀበል የበቃን የሚያደርገን ምልክት መስቀል ነው።

በመሆኑም መስቀል በቤተ ክርስቲያን እንዲሁም በአባቶቻችን በካህናት እጅ ተይዞ ስናየው ክብሩና ኃይሉ እንደምናየው በሰውና በቦታ ብቻ የተወሰነ አይደለም። ምስጢሩና ሀብቱ ጥልቅና ብዙ ነው። ስለኾነም ድርሳን ተደርሶለታል፤ መልክእ፤ መስተበቍዕ፤ ውዳሴ፤ ሰላምና አርኬ ተጋጅቶለታል።(መጽሐፈ ጤፉት) በእነዚህ ድርሳናትም ሊቃውንቱ ደሙ የፈሰሰበት ክቡር መስቀልን ልብን ደስ የሚያሰኝ የሕይወት የወይን ወንዝ (ፈለገ ወይን)፤ መንፈሳዊ ጣዕምን የሚያሰጥ የማር ወንዝ (ፈለገ ማዕር)፤ ሕይወት የሚገኝበት፣ ነፍስን የሚያጠራና የሚያሰማምራት የመንፈሳዊ ዘይት ወንዝ (ፈለገ ቅብዕ)፤ በመንፈሳዊ ሕይወታችን ሕጻናት የኾን ሁሉ አባታችንን ወደ መምስል የሚያሳድገን በጸጋና በቅድስና የምንልቅበት የወተት ወንዝ (ፈለገ ሐሊብ)፣ እያሉ በሚያሰጠው ሀብትና ጸጋ ዓይነት እያመሰገኑ እንድናመሰግን አዝዘውናል።

በአጠቃላይ ቅዱስ ጳውሎስ “ነገር ግን ዓለም ለእኔ የተሰቀለበት እኔም ለዓለም ከተሰቀልኹበት ከኢየሱስ ክርስቶስ መስቀል ሌላ ትምክህት ከእኔ ይራቅ” እንዳለው፤ ትምክህታችን መስቀሉና በመስቀሉ ላይ የተገለጠው ፍቅር ኹኖ ዛሬም የቅዱስ መስቀልን መታሰቢያ ምክንያት በማድረግ ቃለ እግዚአብሔር በመስማት፤ ቅዳሴ በማስቀደስ፤ ዝክር በመዘከር መንፈሳዊ በረከት የምንቀበል ብዙዎቻችን ነን፤ ከዚህም በላይ የበረከት፤ የቃል ኪዳን፤ የማንነት ከዚህ አልፎም የሕልውናችን ምንጮች የሆኑ መንፈሳዊ በዓላታችንን በደማቅ ኹኔታ ማክበራችንን የበለጠ አጠንክረን ልንቀጥልበት የሚገባ ነው። የውጭው ጥቁር የባህል ደመና እንዳይወድቅባቸው፤ ከትውፊታዊ ይዘታቸውም ሳይቀነሱ እንዲከበሩ መጣርም ከምንፈጽማቸው ከእያንዳንዳችን የሚጠበቅ መንፈሳዊ ግዴታ ነው። ለዚህም ይረዳን ዘንድ እርስ በእርሳችን እንድንፋቀር፤ አምላካችንን፤ አገልግሎታችንን፤ ቤተ ክርስቲያናችንንና ሀገራችንን እንድንወድ የልዑል አምላካችን ቅዱስ ፈቃዱ ይኹንልን። አሜን!

 ወስብሐት ለእግዚአብሔር ወለወላዲቱ ድንግል ወለመስቀሉ ክቡር ለዓለም ዓለም አሜን።

Celebration of the Feast of the Cross

In the Name of the Father and the Son and the Holy Spirit, One God. Amen.

Celebration of the Feast of the Cross

Mahibere Kidusan members Celebrating Meskel in “Meskel Square”

The Ethiopian Orthodox Tewahido Church is the treasure of the grace of God and riches of apostolic Traditions. The church is the kingdom of God on the earth and serves as a ladder to let believers ascend to the heaven for eternal life. The celebrations of holy festivals are spiritual practices Christians partake in to become ready for the Kingdom of God. The Ethiopian Orthodox Tewahido Church celebrates feasts not only to commemorate their historical events, but to participate in the rituals as the body of Christ to be blessed by the salvation of God revealed on the Cross. The purpose of this short article is to brief readers about the historical background of the feast of the Cross, the significance of the mystical celebration of the event and the power of the Cross in our spiritual life.

Celebration of the Feast of the Holy Cross

Our Lord Jesus Christ, to Whom be praise and glory, saved the world by presenting His own pure body a sacrifice on the mystical temple (the Holy Cross) for the salvation and ransom of all humanity. He made us free from every curse reigned over us, being made a curse for human being as Saint Paul puts: “Christ redeemed us from the curse of the Law, being made a curse for us: for it is written, cursed is everyone that hangs on a tree (Gal. 3: 13). The Cross of Christ is hope, life, symbol and seal of salvation for those who believe in the Crucified God. On the contrary, it was the symbol of shame and curse for Jews. Therefore, when the Jews saw the miracle the Holy Cross did, in healing sick, blind, deaf, paralytic and so forth, they became nervous and wanted to conceal these wonders. Finally, they decided to bury the Cross by taking it away from Golgotha. Then, they decreed and ordered people to cast dirty things on the Life-giving Wood of the Cross for more than two hundred years.   

The Holy Cross was left buried till the Holy Spirit inspired the blessed Queen Eleni (Helena) to search for it. The queen was a very devout Christian and brought up her son, Constantine, whose father was a gentile King. Constantine was brought up being coached under his father’s supervision, moving from place to place with the king. Upon the death of his father, Constantine took over the throne and the scepter of his father. The devout lady, Eleni (Helena), wanted to search for the glorious and Life-giving Wood of the Cross and told her son that she would go to Jerusalem. This took place twenty years after the enthronement of Constantine. When the king heard this news from his mother, he became very happy and sent her to the holy land with lots of money and soldiers.  

Church Scholars on “Meskel Square”

When the queen arrived in Jerusalem, she visited the holy places, worshiped God and was blessed. Then, she started to search for the Cross. But no one was there to inform her whereabouts of the cross. Finally, she was informed by someone that there was an elderly man, named Kirakos, who could tell her where there cross had been buried. The elderly man was not willing to inform her about the Cross. The Church Tradition tells us that the queen used her own wisdom to oblige the man to tell her about the buried secrete. She gave him food full of salt and prevented him to drink water unless he tells her where the cross had been concealed. Then, he told her that the Cross had been buried under one of three big hills out there. Thus, the old man told her to burn a pile of wood or Demera by adding to it very fragrant incense called Sandrose. The queen did what the old man told her. The smoke of the burning wood and the incense rose to heaven and miraculously bowed down pointing towards the hill where the Life-giving Cross had been buried. Being led by the miracle she observed from the smoke, the queen ordered the people to start digging the mountain on September 26 (Meskerem 16). Thus, our apostolic Tewahido Church celebrates this holy feast to commemorate this mystical event which took place on this date.  

Empress Eleni (Helena) discovered the Holy Cross of our Lord on Megabit 10 (March 19) after much toil. When she found the Cross, three crosses appeared (Our Lord’s Cross and the thieves’ crosses crucified with Him) and the queen could not identify the True Cross. Then she ordered to bring a dead body and put on the crosses one after the other. The two crosses did not reveal any sign. However, when the body was put on the Life-giving Wood of the Cross, it immediately restored to life. Then the queen became very happy and sang with the people around her. That is why we sing today during the celebration of the feast of the Cross. The queen became very happy and built lots of churches in the holy land and consecrated them on September 27 (Meskerem 17) inviting popes from the dioceses of Alexandria, Rome, Constantinople and Ephesus.

We have to make clear two things about the celebration of the feast of the Cross on September 27 (Meskerem 17). We celebrate the feast of the Cross on September 26 to commemorate the Demera of the queen as mentioned before. On this date the smoke proceeded from the Demera and indicated where the Cross had been buried and the queen ordered people to start digging the hill right away. We again celebrate the feast on September 27 to commemorate the appearance of the Cross on March 19 (Megabit 10). The date the True Cross appeared (March 19) falls in the Great Lent and it is not suitable to celebrate such a significant holiday with great observance during the fasting days. Thus, our early church fathers decided to celebrate the feast of discovering the True Cross on September 27 following Demera, coupled with the consecration of the churches the queen built in Jerusalem.

The Festival of the Cross Today

Sunday school student Celebrating Meskel in “Meskel Square”

In Ethiopia the feast of the cross is one of the colorfully celebrated holidays. The fact that the celebration of the feast comes near the beginning of the year gives it especial ritual grace. In our country during this season, the valleys and the hills are decorated with diversified and colorful flowers which let our spirits soar up in spiritual contemplation and admiration of the beauty of the creation of God. The splendor of this nature at the beginning of the year mystically symbolizes the renewal of mankind through the grace of salvation given to us through the redemptive work consummated on the Cross. That is why we hold the cross and colorfully celebrate the feast, commemorating the love of God revealed through His sufferings. Ethiopians celebrate this festival communally, coming together from different nations, cultural backgrounds and linguistic diversities with one accord and love. This depicts the fact that our church has been established on a unified foundation laid by the work of Christ on His Cross (Eph. 2: 16). 

We celebrate this holiday lighting or burning chibo, our traditional torch, for different reasons. Firstly, we burn chibo to commemorate the appearance of the Wood of the Life-giving Cross indicated by the smoke proceeded from the burning Demera of Queen Eleni. Secondly, when the Queen Eleni saw the true Cross of our Lord of Glory, light proceeded from it. So we enjoy and contemplate this spiritual miracle by burning chibo. Thirdly, Ethiopians give thanks to God Who transfers them from the darkness of the Kiremt (Summer) to the bright Metsew (Autumn) season in September. This holiday is colorfully celebrated in southern part of the country and has deep spiritual meditations. This is reminiscent of the words of our Lord: “pray you that your flight be not in the winter, neither on the Sabbath day” (Mat. 24: 20). But the whole symbol and mystery we try to depict through Demera or chibo is to give thanks to God that we were transferred from the darkness of ignorance to spiritual light or knowledge, from reciting the shadow or letters to the body or spirit of salvation, from the darkness of Hell to Paradise and from the shadow of death to brightness of eternal life through the work accomplished on the Cross. That is why we sing with Saint Yared “The Cross is light for the whole world and foundation for the Church”.

When we see the Wood of the Cross, we spiritually ascend to the Hill of Golgotha with our Saver where He was crucified. This reality leads us to deep contemplation of the work God did on the Cross to redeem us. The crucified God on the Cross indicates four directions. His head and feet indicate the heaven and the earth. That is He reconciled those in the heaven and on the earth with His precious blood gushed on the Cross. Another, the head and the feet of our Lord on the Cross also show that the Cross is the ladder of our salvation through which we ascend to heaven for eternal life.  Similarly, His two hands indicate the right and the left corner of the world. The two hands reveal that He reconciled the Israelites and the gentiles through the work of His Cross (Eph 2: 16). Moreover, whenever we see the wood of the cross, we always mystically feel that we are in the bosom of our Redeemer like chicken of a hen which get shield under their mother’s feather (John 12: 32). That is why deacons hold the cross taller than their heads so that everybody sees and contemplates the mystery of this salvation. In the same manner, we put the cross on the top of the gates of the compounds and the domes of churches. Our believers always look up to these crosses during their prayer to contemplate the whole mysteries of the cross which transcend our knowledge and expressions through words. Thus, for us the Cross is our spiritual instructor which preaches us the love of God and the symbol and the seal of our salvation.  

Image result for celebrating meskel

Making the Sign of the Cross

When we make the sign of the cross, we confess our belief in the Holy Trinity and express that our salvation was consummated through the Mystery of Incarnation. The followers of the Ethiopian Orthodox Tewahido Church make the sign of the cross when they start and complete prayer, start and complete eating food, rebuke evil spirits and perform other spiritual practices. When the believers do these all, they say “In the name of the Father and the Son and the Holy Spirit, one God. Amen”. By doing so, they confess their belief in the Holy Trinity. They join their three fingers together and make the sign of the cross to show that they believe in One God. When we make the sign of the cross, we say in the Name of the father (while touching our forehead) and of the Son (while touching our chest) and of the Holy Spirit (while touching first our left shoulder and then our right shoulder). Here, besides confessing our belief in the Holy Trinity, we also express that we were saved and restored to our original state by the redemptive work of our Lord Jesus Christ, the Incarnate Logos. We always remember that God descended from the heaven to the earth and transferred humanity from left to right, from darkness to light, from Hell to Paradise and from death to eternal life.

When we make the sign of the cross, we also confess that we belong to Christ Who saved us being crucified and express that we partake in his sufferings. We follow the order of our Lord: “And he who does not take his cross and follow after Me is not worthy of Me” (Matt. 10:38) and “If anyone desires to come after Me, let him deny himself, and take up his cross, and follow Me” (Matt.16: 24; Mark.8: 34). The Church followed her Lord right from his birth in the person of Salome, Joseph and Virgin Mary during his persecution (Mat. 2:13). When he was led to Golgotha, the Church carried His Cross in the person of Simon the Cyrene (Mat. 27:32) and accompanied her Lord up to Bethany  when He ascended (Luke 24: 50). The church physically holds the Cross of her Lord teaching the mystery of our salvation accomplished on the Cross and intellectually contemplates the depth of His love revealed through His suffering on the Life-giving Wood.

The mysteries of the Cross are evident in our daily life and are vividly depicted in spiritual and ritual practices. The culture of Ethiopian Christians is predominantly religious. Our cloth, jewelry and buildings reveal the sign of the cross.  That is, the sign of the cross is part of our life. Whenever we go to church and pray at our homes, we clothe in sign of the cross. People also engrave the sign of the cross on their foreheads and on different parts of their body to express their love for the crucified God. Furthermore, some believe that they have to confess their belief making tattoos of the cross on their bodies, even when it may cost them their precious lives because they could be easily targeted.

 The Adoration of the Cross in Ethiopian Orthodox Tewahido Church

The Ethiopian Orthodox Tewahido Church venerates the Cross of our Lord Jesus Christ with due attention and high spiritual observance. This is because the church is a treasure of apostolic Traditions and full of riches of the grace of salivation of our Saver. As the bride of Christ, the Church lives sacramental life derived from the mystery of salvation performed on the Cross.

The bride of Christ believes that there is no salvation outside the church and no power without the Holy Cross. She is content with the words of Saint Paul: “For the message of the cross is foolishness to those who are perishing, but to us who are being saved it is the power of God” (1Cor.1: 18). Our holy Church always confesses that she has been betrothed to her Bridegroom (Christ) with the precious dowry (His blood) given to her on the Cross. The Church sings and meditates this mystery with Saint Paul: “But God forbid that I should glory except in the cross of our Lord Jesus Christ, by which the world has been crucified to me, and I to the world” (Gal.6: 14). Our priests use the cross when they exorcise devils and rebuke evil spirits because they believe that the Cross is their power. The evil spirits also tremble when a cross is put on the forehead of an individual suffering from the spirits.

The church knows and preaches the wonders God gave to his holy apostles. For example, we read a verse from Acts of the Apostles that “Insomuch that they brought forth the sick into the streets, and laid them on beds and couches, that at the least the shadow of Peter passing by might overshadow some of them” (Act. 5: 15). Following this practice, the Holy Bible tells us that “There came also a multitude out of the cities round about unto Jerusalem, bringing sick folks, and them which were vexed with unclean spirits: and they were healed everyone (Act. 5: 16). The same was true with the wonder doing cloth of Apostle Paul. We read: “And God wrought special miracles by the hands of Paul. So that from his body were brought unto the sick handkerchiefs or aprons, and the diseases departed from them, and the evil spirits went out of them (Act.19:11-12). Thus, if the shadow and cloth of the saintly apostles could do these miracles, how much does the Life-giving Wood of the Cross of our Lord do more miracles? It is this belief that encourages our apostolic church employ the Cross as her power in every walks of her life.

The Church uses the cross in all holy sacraments for consecration and blessing. For instance, the spiritual rebirth (baptism) cannot be performed without using the cross. The baptismal font is blessed with the holy cross to convert the water to the Life-giving Water gushed from the side of Christ on His Cross. The clergymen are also consecrated with the cross when they are selected for some spiritual office. The vestment or robe they wear is also blessed with the cross when they serve in liturgy. Generally speaking, no church sacrament is blessed and become effective without being sanctified with the cross. That is why we say that the Ethiopian Orthodox Tewahido Church daily practices the sacrament entrusted to her through the graceful redemptive work of Christ. The church also teaches her followers to live sacramental life to prepare for the eternal life to come. The source of all the mysteries in the New Testament is the glorious Cross of our Lord and Saver Jesus Christ.

To sum up, our ancient and apostolic church observes or solemnizes the festival of the Cross commemorating its historical background and holds it as her power and seal of salvation. The Historical commemoration of the Cross reveals that the Holy Cross continues as the center of our spiritual contemplation to the end of the ages. The spiritual celebration of the feast, on the other hand, shows that we always cling to the Cross because it is the source of our life. The Cross is the symbol and seal of our salvation and the “armour of God that we may be able to stand against the wiles of the devil” (Eph. 6:11).

Glory be to God Who is glorified in His Life-giving Cross. Amen.

Mahibere Kidusan Education and Apostolic Mission Coordination

Email Adress : –apostolic.mission@eotcmk.org

‹‹ዮም መስቀል ተሰብሐ፤ ዓለም ተጸውአ፤ ወሰብእ ግዕዘ፡፡›› ቅዱስ ያሬድ

‹‹ዮም መስቀል ተሰብሐ፤ ዓለም ተጸውአ፤ ወሰብእ ግዕዘ፡፡ ዛሬ መስ ከበረ፤ ዓለም ለድኅነት ተጠራ፤ ሰውም ነጻ ወጣ፡፡›› ቅዱስ ያሬድ

‹‹መስቀል›› የሚለውን ቃል አለቃ ኪዳነ ወልድ በመዝገበ ቃላታቸው በቁሙ፤ መስቀያ፤ መሰቀያ፤ ለሞት የሚያበቃ መከራ በማለት ተርጉመውታል፡፡ (ገጽ.፰፻፹፫)

መንፈሳዊና ምሥጢራዊ የመስቀልን ትርጉም በሰፊው ያብራሩት ደግሞ ኢትዮጵያዊው ቄርሎስ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ ናቸው፡፡

በውዳሴ መስቀል ድርሰታቸው ከሰጡት ማብራሪያ ጥቂቱን እንደሚከተለው አቅርበነዋል፡፡

መስቀል፡   – ዕፀ ሕይወት ነው

 • ዕፀ መድኃኒት ነው፡፡
 • ዕፀ ትንቢት ነው፡፡
 • ዕፀ ዕረፍት ነው፡፡
 • ሰይጣንን የሚያጠፋ ምሳር ነው፡፡
 • የአጋንንትን ራሶች የሚቆርጥ ሰይፍ ነው፡፡
 • የቅድስናና የንጽሕና ማኅተም ነው፡፡
 • ለሚጋደሉ የድል አክሊል፣ ወደ በጉ ሰርግ ለተጠሩትም የሰርግ ልብሳቸው ነው፡፡……

አጠቃቀም

      ኦርቶዶክሳዊት ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ያለ መስቀል የምትሠራው ምንም ዓይነት ሥራ የለም፡፡ ከቅዱስ ፓትርያርኳ ጀምሮ እስከ ምእመናን ድረስ ያሉት ሁሉ ለአምልኮተ እግዚአብሔር ሲፋጠኑ መስቀልን በዋነኛነት ይጠቀማሉ፡፡ ጸሎታቸውን ሲጀምሩ ካህናት በመስቀል ምእመናን በጣታቸው አመሳቅለው በማማተብ ስመ ሥላሴን ይጠራሉ፡፡ ቤተ ክርስቲያናችን ምሥጢራተ ቤተ ክርስቲያንን ስትፈጽም መስቀል ዋነኛ መንፈሳዊ መሣሪያዋ ነው፡፡ የቤተ ክርስቲያን ሊቃውንት የመስቀልን ሁለገብ አገልግሎት እንደሚከተለው ገልጸውታል፡፡

‹‹በተግባራችን ሁሉ፣ በምንገባበትና በምንወጣበት ጊዜ፣ ልብሶቻችንን ከመልበሳችን በፊት፣ ከመታጠባችን በፊት፣ በቀንና በማታ ወደ ምግብ ገበታ በምንቀርብበት ጊዜ፣ ማታ መብራታችንን በምናበራበት ጊዜ፣ መጽሐፍ ቅዱስን ለማንበብ በምንጀምርበትና በምንፈጽምበት ጊዜ፣ በዕለታዊ ሕይወታችን መደበኛ ሥራችንን በምንጀምርበት ጊዜ በትምእርተ መስቀል ግንባራችንን እናማትባለን፡፡››

በግልጽ እንደሚታየው ድኅነተ ዓለም የተፈጸመበትን ቅዱስ መስቀል ቤተ ክርስቲያናችን በጉልላቷ ላይ በማድረግ ተሸክማው ትኖራለች፡፡ ካህናትና ምእመናንም ከቅፅረ ቤተ ክርስቲያን ሲደርሱ በዐይነ ሥጋ መስቀሉን በዐይነ ነፍስ ደግሞ የተሰቀለውን (ክርስቶስን) እያዩ ለተሰቀለው አምላክ የባሕርይ፣ ለተሰቀለበት መስቀል ደግሞ የአክብሮት ስግደት ይሰግዳሉ፡፡ ‹‹እግሮቹ በሚቆሙበት ስፍራ እንሰግዳለን፡፡›› (መዝ.፻፴፩፥፯) እንደተባለ፤ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ መላ አካሉ ላረፈበት፣ እጆቹና እግሮቹ ለተቸነከሩበትና በቅዱስ ደሙ መፍሰስ ለተቀደሰ መስቀሉ እንሰግዳለን፡፡

ታሪካዊ የአጠቃቀም ጉዞውም የሚከተለውን ይመስላል፡፡

 • በሁለተኛው ምእት ዓመት የሶረያ ቤተ ክርስቲያን በምሥራቅ አቅጣጫ በግድግዳው ላይ መስቀልን ማኖር (ማንጠልጠል) ጀምራለች፡፡

በአራተኛው ምእት ዓመት ክርስትናው በተሰበከበት ዓለም ሁሉ በአብያተ ክርስቲያናት ሕንፃዎች በውስጥና በውጭ መስቀልን ማኖር፣ ማንጠልጠልና መቅረጽ በስፋት መተግበር ጀመረ፡፡ ለዚህም ምክንያቱ ታላቁ ቈስጠንጢኖስ ከመክስምያኖስ ጋር በተዋጋ ጊዜ ‹‹በዝ ትእምርተ መስቀል ትመውዕ ፀረከ፡፡ ጠላትህን በዚህ  የመስቀል ምልክት ታሸንፋለህ፡፡›› ከሚል ጽሑፍ ጋር በጸፍጸፈ ሰማይ የመስቀል ምልክት መታየት ነው፡፡ ቈስጠንጢኖስ እንዳየው አድርጎ በፈረሱና በበቅሎው ኮርቻ፣ ልጓም፣ ግላስና በዕቃዎቻቸው ሁሉ፤ በጦር መሣሪያዎቻቸውና በጦር ልብሶቻቸው እንዲሁም በሰንደቅ ዓላማት ላይ የመስቀልን ምልክት በማስቀረጹ ድል አድራጊ መሆን ችሏል፡፡ ከዚህ ጊዜ ጀምሮ በአብያተ ክርስቲያናት በስፋት መጠቀም ተጀመረ፡፡ ከዚህም አልፎ እስካሁንም ድረስ እንደሚታየው ፊንላንድ፣ ጆረጂያ፣ አይስላንድ፣ ኖርዌይ፣ ስዊዘርላንድ፣ ስዊድን፣ ግሪክና የመሳሰሉት አገራት በባንዲራቸው ላይ የመስቀል ምልክት መጠቀምን ከቈስጠንጢኖስ ወርሰዋል፡፡

      ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ፡- ‹‹እርሱም (ክርስቶስ) የአካሉ ማለት የቤተ ክርስቲያን ራስ ነው፡፡›› (ቈላስይስ ፩፥፲፰) በማለት እንዳስተማረው ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ይህንኑ በተግባር በሚያሳይ መልኩ ከላይ እንደገለጽነው በራስዋ (በጉልላቱ) ላይ መስቀሉን ተሸክማ የክርስቶስ አካልነቷን ታረጋግጣለች፡፡ ልጆቿም በአንገታቸው በማንጠልጠል፣ የክርስቶስ አካል (የቤተ ክርስቲያን) ሕዋሳት መሆናቸውን ያሳያሉ፡፡ በዚህም መስቀሉን ባዩ ቁጥር በላዩ የተሰቀለውን፣ የድኅነታቸው ራስና ፈጻሚ የሆነውን መድኃኔ ዓለምን እያሰቡ በዐይነ ኅሊና ቀራንዮ ይጓዛሉ፡፡

የመስቀሉ አከባበር ታሪካዊ ዳራ

      መስቀል የከበረው፣ ዓለም ለድኅነት የተጠራውና የሰው ልጅ ነጻ የወጣው በክርስቶስ ሲሆን በተለይም በቀራንዮ አደባባይ በተሰቀለ ጊዜ ይህ ሁሉ ተፈጽሟል፡፡ ‹‹ወይቤ ተፈጸመ ኵሉ፡፡ ሁሉ ተፈጸመ አለ፡፡›› (ዮሐ.፲፱፥፴) እንዲል፡፡ በመስቀል ላይ በሆነው ሞቱ ነቢያት የተነበዩት ትንቢት፣ የመሰሉት ምሳሌ፣ የቆጠሩትም ሱባኤ ተፈጽሟልና፡፡ በሌላ አገላጽ ሁሉም ስለሰው ልጅ ድኅነት ነበርና የሰው ልጅ ድኅነት በመስቀል ላይ ተፈጸመ፤ ታወጀ፤ ተረጋገጠ፡፡ በደሙ ቀድሶ ያከበረውን ቅዱስ መስቀል በዚህ መልክ የማክበራችን ምክንያትስ ምንድነው? ቀጥለን እናየዋለን፡፡

      መድኃኒታቸውን ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ክደው የሰቀሉ አይሁድ በደሙ የከበረ መስቀልም ሕይወት፣ መድኃኒት መሆኑን ባዩ ጊዜ በሰይጣናዊ ቅንዓት ነደዱ፡፡ ‹‹እሱን (ክርስቶስን) ተገላገልን ስንል መስቀሉ ደግሞ ተአምራት ያደርግ ጀመር!›› ብለው በመቆጣት በቆሻሻ ማጠራቀሚያ ጉድጓድ ጣሉት፡፡ እስከ ፸ ዓመተ ምሕረት ድረስ የጣሉት ቆሻሻ በመስቀሉ ላይ እንደኮረብታ ተከመረ፡፡ በ፸ ዓ.ም ኢየሩሳሌም በጠፋች ጊዜ የተረፉት አይሁድ በመሰደዳቸው ተረስቶና ተቀብሮ ከ፫፻ ዓመታት በላይ ያለበት ሳይታወቅ ቀረ፡፡

      መስቀሉ የእግዚአብሔር ኃይል መሆኑን የተረዳች (፩ቆሮ.፩፥፲፰)ንግሥት እሌኒ በ፫፻፳፮ ዓ.ም መስቀሉን ፍለጋ ወደ ቅድስት ሀገር ኢየሩሳሌም ገሰገሰች፡፡ በዚያም ከአይሁድ መምህራን መካከል የተቆጠረ ኪርያኮስ የተባለ ሽማገሌ አገኘች፡፡ ከብዙ ውጣ ውረድ በኋላ መስቀሉ የተቀበረበትን አካባቢ አሳይቷታል፡፡ ክፉዎች ወገኖቹ ከጉድጓድ ቀብረው የቆሻሻ መጣያ እንዳዳረጉት ነገራት፡፡ ንግሥት እሌኒም መስከረም ፲፮ ቀን እንጨት አስደምራ ከለኮሰችው (ካቀጣጠለችው) በኋላ ከፍህሙ ላይ በርካታ ዕጣን አደረገችበት፡፡ የዕጣኑም ጢስ ወደ ላይ ወጥቶ ከመንበረ ጸባኦት ደርሶ ተመልሶ በፈቃደ እግዚአብሐር መስቀሉ ከተቀበረበት መካከለኛው ኮረብታ ዐረፈ (ሰገደ)፡፡ በዚህ ድንቅ ተአምር መካነ መስሉን ተረድታ መስከረም ፲፯ ቀን ሠሪዊቷንና ሕዝቡን ይዛ ማስቆፈር ጀመረች፡፡

      ለረጅም ዓመታት በመስቀሉ ላይ የተጣለው ቆሻሻ ታላቅ ተራራ ሁኖ ስለነበር ያንን የቆሻሻ ክምር በጥንቃቄ ካስወገዱ በኋላ ሦስት መስቀሎችን አገኙ፡፡ እነዚህም የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ የሆነው ቅዱስ መስቀልና የሁለቱ ወንበዴዎች የተሰቀሉባቸው መስቀሎች ናቸው፡፡ መስቀሉ የተገኘው ከብዙ ድካምና ጥረት በኋላ መጋቢት ፲ ቀን ሲሆን ዕውራንን አብርቷል ሐንካሣንን አርትቷል ሙታንን አንሥቷል የጌታችን መስቀልም ባደረገው ድንቅ ተአምራት በተለይም ሙት በማስነሳቱ ተለይቶ ሊታወቅ ችሏል፡፡

      የተባረከችው ንግሥት እሌኒ ባየቻቸው አምላካዊ ተአምራት እጅግ በመደሰቷ መስቀሉን አቅፋ እግዚአብሔርን አመሰገነችው፡፡ ሕዝቡም ሁሉ በቅዱስ መስቀሉ መገኘት ከፍተኛ ሐሴትና ደስታ አደረጉ፡፡ እየዳሰሱትም ኪሪያላይሶን እያሉ ዘመሩ፡፡ በመሸም ጊዜ ቅድስት እሌኒ ከኢየሩሳሌሙ ኤጲስ ቆጶስ ከአባ መቃርዮስ፣ ከሠራዊቶቿና ከሕዝቡ ጋር የችቦ መብራት ይዘው በሰልፍ ሆነው እየዘመሩ ቅዱስ መስቀሉን በክብር አኖሩት፡፡

      ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ከመጀመሪያ ጀምሮ መስቀሉን የተሸከመችውና የምታከብረው ቢሆንም በተለይም ከዚህ ጊዜ ጀምሮ በልዩ ሁኔታ ማክበርን ጀመረች፡፡ ለመስቀል መስገድ፣ መስቀልን መሳም፣ በመስቀል ሕዝብን መባረክ፣ መስቀል መያዝ፣ በልብስና በአካል ላይ የመስቀል ምልክት መቅረጽ እየተስፋፋ መጣ፡፡ በማያምኑ ዘንድ እንደ ሞኝነት የሚቆጠረው (፩ቆሮ.፩፥፲፰) የመስቀሉ ነገር ኃይለ እግዚአብሔር መሆኑ ይበልጥ ጎልቶ የተሰበከውና ክብሩ የገነነው ከዚህ ወዲህ ነው፡፡

      በዓለ መስቀል መስከረም ፲፯ ቀን የመከበሩ ምክንያት ከላይ እንደገለጽነው በዚህ ቀን ንግሥት እሌኒ ግብር እግብታ ቁፋሮ ያስጀመረችበት ቀን ሲሆን በዋናነት ግን በዚሁ ቀን በዓመቱ ንግሥት እሌኒ በ፫፻፳፯ ዓ.ም በጎልጎታ ቤተ ክርስቲያን አሠርታ መስቀሉን ያስገባችበትና ቅዳሴ ቤቱን ያከበረችበት ቀን ስለሆነ ነው፡፡ በዚሁም ላይ መጋቢት ፲ ቀንም በዓሉን ማስብ (ማክበር) አልተወችም፡፡

      ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ታላቁን የመስቀል በዓል በየዓመቱ በአደባባይ (በመስቀል አደበባባይ) በድምቀት ታከብራለች፡፡ በዕለቱ ማለትም በበዓለ መስቀል ዋዜማ የቅድስት እሌኒን የመስቀል ፍለጋ ጉዞ ለማስታወስ ደመራ ደምራ ለበዓሉ የተዘጋጀውን ስብሐተ እግዚአብሔር ታደርሳለች፡፡ በጸሎቱም ፍጻሜ በ፬ቱም መዓዝን አባቶች ዞረው ከባረኩት በኋላ ይለኰሳል፤ (ይቀጣጠላል)፡፡ ሕዝቡም ችቦውን እያቀጣጠለ ታሪኩንና በዋናነት በመስቀሉ ኃይል የተገለጠው ብርሃን ያበሥራል፡፡ ቅድስት ቤተ ክርስቲያንም ለቅዱስ መስቀሉ የሰጠችውን ልዩ ትኩረት ለመግለጽ ከመስከረም ፲፯ እስከ መስከረም ፳፬ ድረስ ያሉትን ቀናት ዘመነ መስቀል ብላ ሰይማዋለች፡፡ በነዚህም ቀናት ነገረ መስቀሉ ይሰበካል፤ ስብሐተ መስቀልም ይደርሳል፡፡

መስቀልና ነገረ ድኅነት

      በነገረ ድኅነት አስተምህሮ መስቀል ዋናው ማጠንጠኛ ነው፡፡ የተነገረው ትንቢት፣ የተቆጠረው ሱባኤና የተመሰለው ምሳሌ የተፈጸመው በመስቀል ላይ ነው፡፡ (ዮሐ.፲፱፥፴) ኢየሱስ ክርስቶስን እወዳለሁ የሚል ሁሉ እውነተኛዋን የአደራ እናቱን ያገኘውም በመስቀል ላይ ነው፡፡ (ዮሐ.፲፱፥፳፭‐፳፯) በሰው ልጆች ላይ ለ፶፻፭፻ ዓመታት ሠልጥኖ የኖረው ሞት የተወገደው በመስቀል ላይ በሆነው በክርስቶስ ሞት ነው፡፡ ጠላት ዲያብሎስ በአዳምና በሔዋን ላይ ያኖረውን (የሰወረውን) የዕዳ ደብዳቤ የደመሰሰው በመስቀሉ ነው፡፡ ‹‹በእኛ ላይ የነበረውን የሚቃወመንንም በትእዛዛት የተጻፈውን የዕዳ ጽሕፈት ደመሰሰው፤ እርሱንም በመስቀል አርቆ ከመንገድ አስወግዶታል፡፡›› (ቈላ.፪፥፲፬‐፲፮) እንዲል፡፡

      ስለ ነገረ ድኅነት ስንነጋገር ስለመስቀሉ መናገር የግድ ነው፡፡ የመዳናችን ጉዳይ (ምስጢር) ያለ መስቀሉ አልተፈጸመምና፡፡ ሊቃውንቱ ይህን በዝማሬያቸው ‹‹ለአዳም ዘአግብኦ ውስተ ገነት፣ ወለፈያታዊ ኅረዮ በቅጽበት፣ ዝንቱ ውእቱ መስቀል፡፡ አዳምን ወደ ነገት ያስገባው፤ ወንበዴውንም በፍጥነት የጠራው ይህ መስቀል ነው፡፡›› በማለት በመስቀል የተፈጸመውን ድኅነት አመስጥረውታል፡፡ ሊቀ ሐዋርያት ቅዱስ ጴጥሮስ በመስቀል ላይ የሆነውን የሰው ልጅ ድኅነት እንዲህ በማለት ነው የገለጸው፡፡ ‹‹ከኀጢአታችን ያወጣን ዘንድ በጽድቁም ያድነን ዘንድ እርሱ ስለኀጢአታችን በሥጋው በእንጨት ላይ ተሰቀለ፤ በግርፋቱም ቊስል ቊስላችሁን ተፈወሳችሁ፡፡›› (፩ጴጥ. ፪፥፳፬) ይህንኑ አስመለክቶ ቅዱስ ጳውሎስም፡- ‹‹ከእንግዲህስ ወዲያ ለኃጢአት እንዳንገዛ የኃጢአት ሥጋ ይሻር ዘንድ አሮጌው ሰዋችን ከእርሱ ጋር እንደተሰቀለ እናውቃለን፤ የሞተስ ከኃጢአቱ ጸድቋልና፡፡›› በማለት በሞት ጥላ ይኖር የነበረ የሰው ልጅ በመስቀሉ ነጻ መውጣቱን ገልጾልናል፡፡

መስቀል የሰላም ዋስተና

      በኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አስተምህሮ መሠረት ክርስቶስ በመስቀሉ ፯ቱን መስተጻርራን (ተቀዋዋሚዎች) አስታርቋል፡፡ እነዚህም ሰውና እግዚአብሔር፣ ሰውና ቅዱሳን መላእክት፣ ሕዝብና አሕዛብ፣ እንዲሁም ነፍስና ሥጋ ናቸው፡፡ በነዚህ በጥንድ በጥንዶቹ መካከል የጥል ግድግዳ ቆሞ ለአምስት ሺህ አምስት መቶ (5500) ዘመናት ሰላም ጠፍቶ በጠላትነት ነበር የኖሩት፡፡ እነዚህን በማስታረቅ እውነተኛውን ሰላም የሰጣቸውና አንድ ያደረጋቸው ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሲሆን የጥሉን ግድግዳ ያፈረሰውም በመስቀሉ ነው፡፡ ‹‹እርሱ ሰላማችን ነውና፤ ሁለቱን ያዋሐደ በአዋጅ የተነገሩትንም የትእዛዛትን ሕግ ሽሮ በመካከል ያለውን የጥል ግድግዳን በሥጋው ያፈረሰ፤ ይህም ከሁለታቸው አንድን አዲስን ሰው በራሱ ይፈጥር ዘንድ፣ ሰላምንም ያደርግ ዘንድ፣ ጥልንም በመስቀሉ ገድሎ በእርሱ ሁለታቸውን በአንድ አካል ከእግዚአብሐር ጋር ያስታርቅ ዘንድ ነው፡፡ መጥቶም ርቃችሁ ለነበራችሁ ለእናንተ ሰላምን፣ ቀርበው ለነበሩትም ሰላምን የምስራች ብሎ ሰበከ፡፡›› (ቈላስ.፩፥፳) በማለት የገለጸልን ይህንን ሲያረጋግጥልን ነው፡፡ ከላይ እንደተገለጸው ሕዝብ እና አሕዛብ (የተገዘሩና ያልተገዘሩ) በመባባል አንዱ አንዱን እየነቀፈ የሚያሳድድበት ዘመን ያበቃው በመስቀሉ ነው፡፡ ይህ በመስቀሉ የተገኘው ሰላምና አንድነት ነው፡፡ የመጀመሪያው የሁለትነታቸው ስም ሕዝብ (የተገዘሩ)፣ አሕዛብ (ያልተገዘሩ) የሚለው ስም ጠፍቶ በክርስቶስ ያገኘነው አንድ ስም ክርስቲያን መጠሪያችን ሆነ፡፡ ይህ ስም ሰላማችን የተረጋገጠበትና አንድንታችን የታወጀበት፣ ምድራውያኑንና ሰማያውያኑን እንኳን ሳይቀር በአንድ ምስጋና (ቅዳሴ) ያስተባበረ ሆነ፡፡

ማጠቃለያ

ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መስቀሉ ሁሉን ወደ እሱ ያቀረበበትና አንድ ያደረገበት መሆኑን በገለጸበት አንቀጽ እንዲህ ብሏል፡፡ ‹‹እኔም ከምድር ከፍ ከፍ ካልሁ ሁሉን ወደ እኔ እስባለሁ፡፡›› (ዮሐ.፲፪፥፴፪) ምንም ዓይነት ምድራዊና ሥጋዊ መስፈርቶች ሳያግዱት ሁሉም ሰው በመስቀሉ ተስቦ ቀርቧል፡፡ ከምድር ብቅ፥ ከሰማይ ዝቅ ብሎ መሰቀሉ ሰማያውያንና ምድራውያኑን አንድ ማድረጉን ማሳያ ነው፡፡ የመስቀሉን አራት ጐኖች፥ የክርስቶስም አራቱን አቅጣጫዎች ያጣቀሰ ስቅለቱ የሰው ልጆችን ሁሉ (በአራቱ ማዕዘናት ያሉትን) አንድ ማድረጉን የሚገልጽ ናቸው፡፡ ሁሉን ትተን እንድንከተለው ያዘዘን መስቀሉን ተሸክመን ነው፡፡ (ማር.፰፥፴፬)

ማኅበረ ቅዱሳን ትምህርትና ሐዋርያዊ አገልግሎት ማስተባበሪያ

ኢ-ሜይል አድራሻ፡-

የዘመናት ለውጥ ለክርስቲያኖች የደወል ድምፅ ነው።

ጌታቸው በቀለ

ዘመን

ዘመን የሚለው ቃል አንድ ዓመትን ያመለክታል። በብዙ ሲሆን ዘመናት ይባላል። ይህም ከአንድ ዓመት በላይ የሆነ ጊዜን ለማሳየት ነው። በዘመን ውስጥ ዕለታት እና ወራት አሉ። አንድ ዓመት ማለት መሬት አንድ ጊዜ በፀሐይ ዙሪያ ለመዞር የሚፈጅባት ጊዜ ነው፡፡ ይህም 365 ከ1/4 (ሦስት መቶ ስድሳ አምስት ቀን ከሩብ) ዕለታት ይፈጃል፡፡ አሁን ባለንበት የዓለማችን ግንዛቤ ምድር በራሷ ዛቢያ እየተሽከረከረች በፀሐይ ዙሪያም ትዞራለች፡፡ ምድር በፀሐይ ዙሪያ የምትዞረው ወደ ጎን 23 ተኩል ዲግሪ ያህል አጋድላ ነው፡፡ የቀን እና የሌሊት ርዝመት መለያየትም የሚከሰተው በዚህ ማጋደል ምክንያት ነው ተብሎ ይታሰባል፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ ደግሞ «ቀንና ሌሊትን ይለዩ ዘንድ፣ ለዕለታት፣ ለዘመናትና፣ ለዓመታት ምልክት ይሆኑ ዘንድ» /ዘፍ.1. 14- 15/ ይላል።ይህም የቀንና የሌሊት መፈራረቅ የዕለታትና፣ የወራት፣ የዘመናትም መገኛ መስፈሪያዎች መሆናቸውን ያመለክታል።

አንድ ዕለት ማለት አንድ ቀንን (መዐልት) /የብርሃን ክፍለ ጊዜን/ እና አንድ ሌሊትን /የጨለማ ክፍለ ጊዜን/ ያካተተ፣ ፀሐይ ከወጣች በኋላ ተመልሳ እስከምትወጣ ድረስ ያለውን ጊዜ የያዘ ነው፡፡ እንደ ዓለም ጠበብት አገላለጽ አንድ ዕለት ማለት ምድር በራሷ ዛቢያ አንድ ጊዜ የምትሽከረከርበት ነው፡፡ ወር ወይንም ወርኅ ማለት በግእዝ ጨረቃ ማለት ነው፡፡ ሙሉ ጨረቃ ከወጣች በኋላ ድጋሜ ሙሉ ሆና እስከምትወጣ ድረስ ያለው ጊዜ አንድ ወርኅ ይባላል፡፡ ይህም ጨረቃ፣ መሬትን አንድ ጊዜ ዙራ ለመጨረስ የሚፈጅባት ጊዜ ነው፡፡ አንድ ወር ሃያ ዘጠኝ ተኩል ዕለታት ነው፡፡

የዘመን መለወጫ ዕለት ስያሜዎች

1.    ዱስ ዮሐንስ

የኢትዮጵያ የዘመን መለወጫ ዕለት ስሙ ቅዱስ ዮሐንስ ይባላል። ቅዱስ ዮሐንስ የሚባልበትም ሁለት ምክንያት አለው። አንዱ፤ መጥምቁ ዮሐንስ በሄሮድስ አንቲጳስ ጊዜ ከጳጉሜን ፩ ቀን ጀምሮ ታስሮ ሰንብቶ በመስከረም ፩ ቀን ሞቱ ስለተወሰነበትና በመስከረም ፪ ቀን አንገቱ በሰይፍ ተቆርጦ በሰማዕትነት ስላረፈ ነው። በተጨማሪም ቅዱስ ዮሐንስ ለኦሪትና ለወንጌል መገናኛ መምህር ነበርና ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን በዚህ ዕለት ላለፈው ዘመን መሸኛ፥ ለሚመጣው ዘመን መቀበያ እንዲሆን ብለው በመስከረም ፩ ቀን በዓሉ እንዲከበር ስላደረጉ በሱ ስም ቅዱስ ዮሐንስ እየተባለ ይጠራል። ሁለተኛው ምክንያት በአቆጣጠርም ተራ ወደ ኋላ ተመልሶ ቢቆጠር ዓለም የተፈጠረበት ዘመን ከአራቱ ወንጌላውያን አንዱ በሆነው በዘመነ ዮሐንስ የሚገጥም ሆኖ ስለሚገኝ ቅዱስ ዮሐንስ ተብሎ ይጠራል።

2.    እንቍጣጣሽ

ከጥፋት ውኃ በኋላ የነበሩ ኖኅና ልጆቹ ሰማዩ በደመና በመክበዱ ምክንያት “ማየ አይኅ እንደገና ይመጣ ይሆን?” እያሉ ሲደነግጡ ከርመው በመስከረም ወር መጀመሪያ ላይ ሙሉ የፀሓይ ብርሃን ተመለከቱ። ምድር በአበባ አሸብርቃ የተገለጠችበትና በዚህም የእግዚአብሔርን ቸርነት፥ የቃል ኪዳኑን መጽናትም የተረዱበት ጊዜ ነው። ይህንንም ዕለት ቀድሞ ከአባቶቻቸው እንደ ወረሱት ጥንተ ብርሃን፥ ጥንተ ዓመት፥ ጥንተ ዕለት ብለው በዓል አድርገው አክብረውታል። ሲያከብሩትም እንግጫ ነቅለው፣ አበባ ጐንጕነው መጀመሪያ መሥዋዕት ይሠዉበት ከነበረው ቦታ ሄደው ለእግዚአብሔር አምኃ አቅርበዋል። ከዚያ በኋላ እርስ በራሳቸው የአበባ ስጦታ በመለዋወጥ አክብረውታል። ሲያከብሩትም ዕንቍጣጣሽ በሚል ቃል የመልካም ሞኞታቸውን ይገላለጡበት ነበር።

የታሪክ ጸሐፊዎች ‘ዕንቍጣጣሽ’ የሚለውን ቃል በልዩ ልዩ መልክ ተርጕመውት እናያለን። አንዳንዶች ንጉሡ ሰሎሞን ለሳባ ንግሥት የዕንቍ ቀለበት ሰጥቷት ነበርና ‹ዕንቍ ለጣትሽ› ማለት ነው ብለው ጽፈዋል። ሌሎች ደግሞ ‘እንቍጣጣሽ’ ማለት ‹ተንቈጠቈጠ፥ አንቈጠቈጠ› ከሚለው ቃል ተወስዶ ምድር በአበባ አጌጠች፥ ሰማይም በከዋክብት አሸበረቀ እንደ ማለት ሰማይን በከዋክብት ያስጌጠ አምላክ ምድርንም በአበቦች አጎናጸፋት ለማለት የተሰጠ ቃል ነው ይላሉ።

3.    መስከረም

ኖኅ በመርከብ ውስጥ በነበረ ጊዜ በዕብራውያን አቆጣጠር ስድስተኛ በሆነው በመስከረም ወር መጀመሪያ ላይ መርከቢቱ አራራት ከሚባለው ተራራ ላይ ዐርፋለች። በግእዝ ቋንቋ መርከብ ‹መስቀር› ይባላል። ከዘመን ብዛት በኋላ «ቀ» ወደ «ከ» ተለውጦ ‘መስከረም’ ተባለ እንጂ መስቀርም ምድር አገኘች፥ መርከብም ምድር ነካች ለማለት የተሰጠ የነካችበት ወሩ ስያሜ ነው።

4.    ርእሰ ዐውደ ዓመት

ርእሰ ዐውደ ዓመት የምንለው ‹ዐውድ› ማለት በግእዙ ቋንቋ ‹ዙሪያ፥ ክብ› የሆነ ነገር ማለት ነው። የዓመት ጠቅላላ መሠረታውያን ቀኖች የሚባሉት ሦስት መቶ ስድሳ አራት ቀኖች ናቸው። እነዚህም በኀምሳ ሁለት ሱባዔ ተከፍለው ለእያንዳንዱ ቀን በዓመት ውስጥ ለሰባቱ ዕለታት ኀምሳ ሁለት፣ ኀምሳ ሁለት ቀን ይደርሳቸዋል። ከነዚህ ቀኖች የተሳሳበ የሴኮንድ፥ የደቂቃ፥ የሰዓት ዕላፊ ተጠራቅሞ ሦስት መቶ ስድሳ ዐምስተኛዋን የዘመን ማገጣጠሚያ ቀን ያስገኛል። ይህቺ ቀን እንግዲህ ‹ዙሪያ፥ ክብ፣ መግጠሚያ› ናት ማለት ነው። በዚህች ቀን አማካይነት ወደ ዐዲሱ ዘመን መጀመሪያ እንተላለፋለን። ይህቺ ቀን ዕለተ ዐዕዋዲት፥ ዕለተ ምርያ፣ የመዘዋወሪያ ቀን፣ ወይም የመጨረሻ ቀን ተብላ ትጠራለች።

የዘመን መቀየር ክርስቲያኖችን የደወል ድምፅ ያህል ሊያነቃ ይገባል

ዘመን ሲቀየር ክርስቲያኖች ሊያስቡት የሚገባ ነገር አለ። እርሱም፦ ያለፈውን ዘመን እንዴት እንዳሳለፉት እና መጪውን እንዴት ሊያሳልፉ እንዳቀዱ ነው። ምክንያቱም የዘመን መቀየር በራሱ የእግዚአብሔር የደውል ድምፅ ነው። እግዚአብሔር ዓመቱን በወቅት ለይቶ አየሩን በፍቃዱ እያቀያየረ ያኖረናል። አንድም የእግዚአብሔር ሕልውና በፍጥረቱ ይገለጣልና በሠራው ሥራ እየተደመምን እንድናመሰግነው ሲሆን፣ በሌላ በኩል ዘመናችንን እያየን፣ ወደ ራሳችን እየተመለከትን ለንስሐ ሕይወት እንድንበቃ የተሰጠን ረቂቅ ደወል ነው። ቅዱስ ጴጥሮስየአሕዛብን ፈቃድ ያደረጋችሁበት በመዳራትና በሥጋ ምኞትም፣ በስካርም፣ በዘፈንም፣ ያለ ልክም በመጠጣት ነውርም ባለበት በጣዖት ማምለክ የተመላለሳችሁበት ያለፈው ዘመን ይበቃል’’ (1ኛ ጴጥ. 4፣3) እንዳለ፣ ያለፈው ዘመን የመንፈሳዊ ሕይወት አካሄድ እግዚአብሔርን ያስደሰተ ነው? ወይንስ ለሥጋችን ድሎት ብቻ የኖርንበት? ሌሎችን ወደ መንፈሳዊ ሕይወት ለመምጣት የጣርንበት ወይንስ ለሌሎች መሰናክል የሆንበት? ነውን እያልን የራሳችንን ያለፈ ዘመን አካሄድ የምንመረምርበት የደወል ድምፅ ነው።

በአጠቃላይ የዘመን መቀየር ክርስቲያኖችን የደወል ድምፅ ያህል ሲያነቃ ባለፈው ሕይወት ላይ ብቻ መሠረት ያደረገ ሊሆን አይገባም። ይልቁንም ደወሉ መጪውን ዘመን እንዴት ለመኖር እንዳሰብን ሊጠይቀን ይገባልል። ስላለፈው፣ ከመንፈሳዊ ሕይወት ለራቀ አኗኗራችን የምንጠየቀው በተሰጠን አዲስ ዘመን ማስተካከል ካልቻልን ነው። መጪው ዘመን በእጃችን ያለ፣ እግዚአብሔር እንደፈቃዱ የሰጠን፣ ዋጋ ያልከፈልንበት ስጦታ ነው። ይህም ከራሳችን አልፈን ሌሎችን ለመመለስ እንድንተጋ የተሰጠን የእግዚአብሔር ችሮታ ነው። በዮሐንስ ራዕይ 22፥15 ላይ እንደተፃፈው “አስማተኞች ሴሰኛዎችም ነፍሰ ገዳዮችም ጣዖትንም የሚያመልኩ፣ ውሸትንም የሚወዱና የሚያደርጉ ሁሉ በውጭ አሉ።” እንዳንባል ባለፈው ዘመን የነበሩንን፣ ከእግዚአብሔር ያጣሉንን የኃጢአት ተግባራት ሁሉ ልናስወግድበት እና የንስሓ ጊዜ አድርገን አዲሱን ዘመን ልንጠቀምበት ይገባናል።

የዘመኑ መለወጥ ደወል ሲሆን ደወሉን ሰምቶ ከክፉ መንገድ የሚመለስ በረከትን ያገኛል። በዘመኑ መቀየር ውስጥ የደወል ድምፁን እንዳልሰማ የሚያልፍ ደግሞ ከበረከት ይልቅ መርገምን ይቀበላል፤ ከጽድቅ ይልቅ ኲነኔ ይጠብቀዋል። በማቴዎስ ወንጌል 7፥24 ላይ ጌታችን እና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ “ስለዚህ ይህን ቃሌን ሰምቶ የሚያደርገው ሁሉ ቤቱን በዓለት ላይ የሠራ ልባም ሰውን ይመስላል። ዝናብም ወረደ ጎርፍም መጣ፣ ነፋስም ነፈሰ፣ ያንንም ቤት ገፋው፣ በዓለት ላይም ስለተመሠረተ አልወደቀም። ይህንን ቃሌን ሰምቶ የማያደርገው ሰው ሁሉ ቤቱን በአሸዋ ላይ የሠራ ሰነፍ ሰውን ይመስላል። ዝናብም ወረደ፣ ጎርፍም መጣ፣ ነፋስም ነፈሰ ያንም ቤት መታው፥ ወደቀም፥ አወዳደቁም ታላቅ ሆነ።’’ ብሎ እንዳስተማረን። ስለዚህ ሁላችንም በዘመን መቀየር ውስጥ ያለውን የእግዚአብሔር የደወል ድምፅ አስተውለን የበለጠ ቤተ ክርስቲያናችንን ለማገልገል የምንተጋበት፣ እና ለሰማያዊት ኢየሩሳሌም የበቃን የሚያደርገንን ሥራ የምናከናወንበት ዘመን ያድርግልን።  

ወስብሐት ለእግዚአብሔር።

ዐውደ ርእይ እና የስብከተ ወንጌል መርሐ ግብር

ሚያዚያ 30 ቀን 2007 ዓ.ም.

በኢ.ኦ.ተ.ቤ. ማኀበረ ቅዱሳን በአውሮፓ ማዕከል የጀርመን ቀጣና ማዕከል በሙኒክ ከተማ በደ/ብ/ቅ/ገብርኤል ቤተክርስቲያን ግንቦት 15 እና 16 ቀን 2007ዓ.ም (May 23 – 24/2015) የዐውደ ርእይ እና የስብከተ ወንጌል መርሐ ግብር አዘጋጅቷል። በዕለቱ የሚኖረውን ዝርዝር መርሐ ግብር ከማስታወቂያው ላይ ይመልከቱ።

alt

ቀ/ማዕከሉ በሙኒክ ከተማ እና አካባቢዋ ለሚገኙ ምዕመናን በተጠቀሰው ቀን እና ሰዓት ጊዜያቸውን አመቻችተው ይህን መርሐ ግብር እንዲሳተፉ በእግዚአብሔር ስም ጥሪ አስተላልፏል።

ወስብለእግዚአብሔር!

በአውሮፓ የወላጆች የውይይት መድረክ

ሚያዚያ 22 ቀን 2007 ዓ.ም.

በአውሮፓ በአይነቱ ልዩ የሆነ የወላጆች የውይይት መድረክ «ሕጻናትን እና ታዳጊዎችን እንዴት ማሳደግ አለብን» በሚል ርዕስ ሚያዝያ 27 (May 5, 2015 GC) ቀን 2007ዓ.ም ከምሽቱ 20፡00 ሰዓት CET በፓልቶክ ይካሄዳል። እባክዎን ዝርዝር መርሃ ግብሩን ከማስታወቂያው ላይ ይመልከቱ።

 

ወስብሐት ለእግዚአብሔር።

«ትንቢት ይቀድሞ ለነገር ፤ ተግባርን (ድርጊት) ትንቢት ይቀድመዋል»

በዘመናት ውስጥ ለእግዚአብሔር ምስክር ሆነው ሕይወታቸውን ከሰጡ ሰዎች መካከል ሠለስቱ ደቂቅ በዚህ ዘመን በተለይ ለወጣት ክርስቲያን ልጆች አርአያ ሆነው ይጠቀሳሉ። እግዚአብሔርም እራሳቸውን መሥዋዕት አድርገው ስለእርሱ በመስጠት የምናመልከው አምላካችን ከሚነድደው ከእሳቱ እቶን ያድነን ዘንድ ይችላል ፤ ከእጅህም ያድነናል። ”(ዳን 316) በማለት እንደተናገሩት ትንቢት ፣ በቅጽበት መልአኩ ቅዱስ ገብርኤልን ልኮ ተአምራቱን ገልጾላቸዋል። በእውነትም ይህ ታሪክ በተለይ በሃገራችን በታላቅ በዓል ታጅቦ መከበሩ እግዚአብሔርን በእውነት ላመኑ ፣ በሥሙም ለታመኑ ፣ ወደፊትም አምነው ለሚታመኑ ሁሉ ትልቅ ምስክር ነው ።

የቅዱስ ገብርኤል በዓል ታሪካዊ አመጣጥ

Read more

ልዩ የፓልቶክ ውይይት

gedamatdiscussionad