Entries by Website Team

በኖርዌይ ንዑስ ማእከል የመጀመሪያው ሐዊረ ሕይወት ተካሄደ

በኖርዌይ ንዑስ ማእከል ሰኔ 20 ቀን 2009 ዓ.ም. በማኅበረ ቅዱሳን አውሮፓ ማእከል፣ የኖርዌይ ንዑስ ማእከል ከክርስቲያንሳንድ ቅድስት ማርያም ቤተክርስቲያን ጋር በመተባበር በሀገረ ኖርዌይ የመጀመሪያውን የሐዊረ ሕይወት መርሐ ግብር በክርስቲያንሳንድ ከተማ መጋቢት ፳፫ እና ፳፬  ቀን ፳፻፱ ዓ.ም አካሔደ። በሐዊረ ሕይወቱ ላይ ከክርስቲያንሳንድ ከተማ እና በአቅራቢያው ከሚገኙ ሌሎች ከተሞች የተሰባሰቡ ቁጥራቸው ከ40 እስከ 50 የሚደርሱ ምእመናን ተሳትፈዋል።

የጀርመን ንዑስ ማእከል አራተኛውን የሐዊረ ሕይወት አካሄደ

በጀርመን ንዑስ ማእከል ሰኔ 20 ቀን 2009 ዓ.ም. የጀርመን ንኡስ ማእከል ከመጋቢት ፲፯ እስከ መጋቢት ፲፱ ቀን ፳፻፱ ዓ.ም አራተኛውን የሐዊረ ሕይወት መርሐ ግብር በጀርመን የግብፅ አቡነ እንጦንስ ገዳም አካሄደ፡፡ በዚህ ሐዊረ ሕይወት ከጀርመን እና ከሌሎች አውሮፓ ሀገራት የተውጣጡ ካህናት፣ ዲያቆናት እና ምዕመናን የተሳተፉ ሲሆን በጠቅላላ የተጓዦች ብዛት 250 ነበር።  የጕዞ መነሻውን መጋቢት ፲፯ ከቀኑ 11 ሰዓት ከፍራንክፈርት […]

የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ ክርስቲያን መዝሙራት ከየት ወዴት በሚል ለሦስተኛ ጊዜ የተዘጋጀ የግንዛቤ ማስጨበጫ መርሐግብር በእንግሊዝ ለንደን ከተማ ተካሄደ።

በእንግሊዝ ንዑስ ማእከል ሰኔ 16 ቀን 2009 ዓ.ም. በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ ክርስቲያን ስም የሚወጡ መዝሙራት ቁጥር እየተበራከቱ ቢሄዱም በተለይ በቅርብ ጊዜ የወጡ አንዳንድ መዝሙራት ግን ከያሬዳዊ ዜማ ይልቅ ለዓለማዊ ዘፈን ያደሉ መሆናቸዉን ተከትሎ ማኅበረ ቅዱሳን ባካሄደዉ ጥናት እየታዩ ያሉትን ችግሮችና የመፍትሔ ሐሳቦችን በመረጃ በማስደገፍ አቅርቦ ነበር። የዚህ ጥናት ዉጤት በተለያዩ የሀገር ዉስጥና የዉጭ ሀገራት ጉባኤያት ላይ የቀረቡ ሲሆን በማኅበረ […]

ጰራቅሊጦስ

በቀሲስ ኃይለኢየሱስ ተመስገን ግንቦት 26 ቀን 2009 ዓ.ም. በቅዳሴ ጸሎት ካህናት ከሚጸልዩት ጸሎት ውስጥ “ወቡሩክ መንፈስ ቅዱስ ጰራቅሊጦስ መጽንዒ ወመንጽሔ ኩልነ” የሚል እናገኛለን ሁላችንን የሚያነጻ፣ የሚያጸና መንፈስ ቅዱስም ቡሩክ ነው ማለት ነው። በዚህ ጸሎት ላይ ጰራቅሊጦስ የሚለው ቃል ከሦስቱ አካላት አንዱ ለኾነው ለእግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ መጠሪያ እንደሆነና የሚያነጻ፣ የሚያጸና መሆኑን ይገልጣል።

ቀርቦሙ እግዚእ ኢየሱስ ወሖረ ምስሌሆሙ (ጉዞ ከእግዚአብሔር ጋር) ሉቃስ 24÷13­-45

በቀሲስ ኃይለኢየሱስ ተመስገን ሚያዚያ 21 ቀን 2009 ዓ.ም. ክርስቶስ ተንሥአ እሙታን ……………. በዓቢይ ኃይል ወሥልጣን አሰሮ ለሰይጣን …………………………..አግአዞ ለአዳም ሰላም ……………………………………… እም ይእዜሰ ኮነ…………………………………………..ፍሥሐ ወሰላም “ክርስቶስ በታላቅ ኃይልና ሥልጣን ከሙታን ተለይቶ ተነሣ ፤ ዲያብሎስን አሰረው አዳምን ነጻ አወጣው ፤ ሰላም ከዛሬ ጀምሮ ሰላም ሆነ” 13.ወይእተ ዕለተ እንዘ የሐውሩ ክልኤቱ እምውስቴቶሙ ሀገረ እንተ ርኅቅት እምኢየሩሳሌም መጠነ ስሳ ምዕራፍ […]

ሆሣዕና

በኤርምያስ ልዑለቃል መጋቢት 30 ቀን 2009 ዓ.ም. ሆሣዕና ቃሉ የዕብራይስጥ ሲሆን ትርጉሙም አሁን አድን ማለት ነው። በቅድስት ቤተ ክርስቲያን ሥርዓት መሠረት የታላቁ ዓቢይ ጾም ስምንተኛ እሑድ የሆሣዕና በዓል በድምቀት የሚከበርበት ዕለት ነው። በዚህ ዕለት ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በታላቅ ትህትና በአህያ ጀርባ ተቀምጦ ወደ ኢየሩሳሌም ያደረገውን ጉዞ የሚዘክር ቃለ እግዚአብሔር በስፋት ይደርሳል። በአራቱም ወንጌላውያን በቅዱስ ማቴዎስ፣ ማርቆስ፣ ሉቃስ […]

በሆላንድ ሐዊረ ሕይወት ተካሔደ።

በሆላንድ ንዑስ ማእከል መጋቢት 26 ቀን 2009 ዓ.ም በማኅበረ ቅዱሳን አውሮፓ ማእከል የሆላንድ ንዑስ ማዕከል የመጀመሪያውን ሐዊረ ሕይወት በሆላንድ ሊቨልደ ግዛት በሚገኘው የግብፅ ኮፕት ቅዱስ ቴዎድሮስ ኦርቶዶክስ ገዳም መጋቢት ፱ ፳፻፱ ዓ.ም. አካሔደ። ሐዊረ ሕይወቱ በአባቶች ጸሎት የተከፈተ ሲሆን በመቀጠልም የመጀመሪያ የሆነው የነገረ ክርስቶስ ትምህርት በመጋቤ ምስጢር ኅሩይ ኤርምያስ ተሰጥቷል። ከሰአት በኋላ ከተሳታፊዎች ለተነሱ መንፈሳዊ […]

በቩርዝቡርግ ቅዱስ ማርቆስ ቤተ ክርስቲያን ዐውደ ርእይ ተካሔደ።

በጀርመን ንዑስ ማእከል መጋቢት 26 ቀን 2009 ዓ.ም በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ የሰ/ት/ቤ/ማ/መምርያ ማኅበረ ቅዱሳን አውሮፓ ማእከል የጀርመን ንዑስ ማእከል እና የቩርዝቡርግ ቅዱስ ማርቆስ ሰበካ ጉባዔ በመተባበር ከየካቲት ፳፭ እስከ የካቲት ፳፮ ቀን ፳፻፱ ዓ.ም ዐውደ ርእይ እና የስብከተ ወንጌል መርሐ ግብር አካሄዱ። ዐውደ ርእዩ የቩርዝቡርግ ቅዱስ ማርቆስ ቤተ ክርስቲያን አገልጋይ በሆኑት በቀሲስ ገብረማርያም እና የአውሮፓ ማእከል ሰብሳቢ […]

ምኵራብ

በዲያቆን አለባቸው በላይ የካቲት 25 ቀን 2009 ዓ.ም   ቅዱስ ወንጌል እንደሚነግረን በምኵራብ ያገለግሉ ዘንድ የተሾሙ ካሕናተ አይሁድ እና የጥቅም ተጋሪዎቻቸው ኃላፊነታችውን ረስተው፣ዓላማችውን ዘንግተው ቅዱስ የሆነውን የእግዚአብሔርን ቤት መንፈሳዊ ገበያነቱ ቀርቶ የሥጋ ገበያ፤ ቅጽረ ምኵራብን የወንበዴዎች መናኻሪያ (ማቴ 21:13፤ ሉቃ19:46) አድርገውት ነበር። በዚህ ምክንያት በቤቱ ተገኝቶ ጸሎት ማድረስ፤ መባእ ማቅረብ፤ ከፈጣሪ ጋር መገናኘት የማይቻልበት ሁኔታ ተፈጥሮ […]

ቅድስት

በዲያቆን መስፍን ኃይሌ የካቲት 18 ቀን 2009 ዓ.ም የቤተክርስትያናችንን መዝሙር ንባቡን ከዜማው አስማምቶ አጠናክሮ ያስተላለፈልን ኢትዮጵያዊው ሊቅ ቅዱስ ያሬድ በጾመ ድጓው በዓቢይ ጾም ለሚገኙትን እሑዶች ሁሉ የተለየ መዝሙር ስለሠራላቸው እያንዳንዱ እሑድ በመዝሙሩ ስም ይጠራል ። በዚህም መሰረት የዚህ ታላቅ ጾም ሁለተኛው እሑድ ቅድስት ተብሎ ተሰይሟል። ቅድስት የሚለው ቃል ግሱ“ቀደሰ” ሲሆን ለየ አከበረ መረጠ የሚል ትርጉም […]