Entries by Website Team

በጀርመን ሀምቡርግ ከተማ ዐውደ ርእይ ተካሄደ

በጀርመን ቀጣና ማእከል ሰኔ 3 ቀን 2007 ዓ.ም. በጀርመን ሀገር በሀምቡርግ ከተማ ግንቦት ፳፱ እና ፴ ፳፻፯ ዓ.ም. ”ለሁለንተናዊ የቤተክርስቲያን እድገት የድርሻችንን እንወጣ” በሚል መሪ ቃል የዐውደ ርእይ እና የስብከተ ወንጌል መርሐግብር ተካሄደ። ዐውደ ርእዩን በማኅበረ ቅዱሳን የአውሮፓ ማእከል ከሀምቡርግ ደብረ መድኃኒት ቅድስት ኪዳነ ምሕረት ቤተ ክርስቲያን ሰበካ ጉባኤ ጋር በመተባበር ያዘጋጀው ሲሆን መርሐግብሩን የከፈቱት […]

ማኅበሩ ስብከተ ወንጌል በአውሮፓ ሊያካሂድ ነው

ግንቦት 30 ቀን 2007 ዓ.ም. በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ሰ/ት/ቤቶች ማ/መምሪያ ማኅበረ ቅዱሳን የአውሮፓ ማዕከል ትምህርትና ሐዋርያዊ አገልግሎት ክፍል በየዓመቱ በምዕራባውያኑ የበጋ ወቅት የሚያካሂደውን የስብከተ ወንጌል አገልግሎት በቅርቡ እንደሚጀምር አስታወቀ።

በፓሪስ የደ/ም/ቅ/ማርያም ቤተክርስቲያን የምሥረታ በዓል ብጹዕ አቡነ ዮሴፍ በተገኙበት ተከበረ

በፈረንሳይ ግንኙነት ጣቢያ ግንቦት 27 ቀን 2007 ዓ.ም. በፈረንሳይ ሀገር የመጀመሪያ የሆነችው በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ የደ/ም/ቅ/ማርያም ቤ/ክ ፲ኛ ዓመት የምሥረታ ክብረ በዓል እና የንግሥ በዓል ከግንቦት ፳፩ እስከ ፳፫ ቀን ፳፻፯ ዓ.ም. በድምቀት ተከበረ። በመጀመሪያ ጥቂት ምእመናን በእመቤታችን በቅድስት ማርያም ሥም በጽዋ ማኀበር ተሰባስበው ለብዙ ዓመታት ከቆዩ በኋላ በ፲፱፻፺፯ ዓ.ም. ግንቦት ወር በወቅቱ የአውሮፓ ሀገረ ስብከት ሊቀ […]

በሀገረ ጀርመን በርሊን ከተማ የቅዱስ አማኑኤል ቤተ ክርስቲያን ቅዳሴ ቤት ተከበረ

ግንቦት 26 ቀን 2007 ዓ.ም. በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የደቡብ፣ምስራቅና ምዕራብ አውሮፓ ሀገረ ስብከት የበርሊን ቅዱስ አማኑኤል ቤተ ክርስቲያን የተገዛው ሕንፃ ቤተ ክርስቲያን ቅዳሴ ቤት ግንቦት 23 ቀን 2007 ዓ.ም ተከበረ፡፡

በጀርመን ሙኒክ ዐውደ ርእይ ተካሔደ

በጀርመን ቀጣና ማእክል ግንቦት 20 ቀን 2007 ዓ.ም. በማኅበረ ቅዱሳን የአውሮፓ ማእከል ግንቦት ፲፭ እና ፲፮ ፳፻፯ ዓ.ም. በጀርመን ሙኒክ ደብረ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን ”ለሁለንተናዊ የቤተክርስቲያን እድገት የድርሻችንን እንወጣ” በሚል ርዕስ የዐውደ ርእይ እና የስብከተ ወንጌል መርሐ ግብር አካሄደ::

፲፭ ኛው የአውሮፓ ማዕከል ጠቅላላ ጉባዔ ሊካሄድ ነው

ግንቦት 19 ቀን 2007 ዓ.ም. በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስትያን ሰ/ት/ቤቶች ማ/መምሪያ ማኅበረ ቅዱሳን የአውሮፓ ማዕከል ፲፭ኛ ጠቅላላ ጉባዔውን በጀርመን ሀገር ፍራንክፈርት ከተማ ሊያካሂድ ነው። ከሰኔ ፳፮ እስከ ፳፰ ቀን ፳፻፯ዓ.ም. በሚቆየው በዚህ ጉባዔ፦ የደቡብ ፣ የደቡብ ምሥራቅ እና የደቡብ ምዕራብ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ሙሴ እና የሀገረ ስብከቱ ዋና ጸሐፊ የሰሜን ምዕራብ […]

ዐውደ ርእይ እና የስብከተ ወንጌል መርሐ ግብር

ሚያዚያ 30 ቀን 2007 ዓ.ም. በኢ.ኦ.ተ.ቤ. ማኀበረ ቅዱሳን በአውሮፓ ማዕከል የጀርመን ቀጣና ማዕከል በሙኒክ ከተማ በደ/ብ/ቅ/ገብርኤል ቤተክርስቲያን ግንቦት 15 እና 16 ቀን 2007ዓ.ም (May 23 – 24/2015) የዐውደ ርእይ እና የስብከተ ወንጌል መርሐ ግብር አዘጋጅቷል። በዕለቱ የሚኖረውን ዝርዝር መርሐ ግብር ከማስታወቂያው ላይ ይመልከቱ። ቀ/ማዕከሉ በሙኒክ ከተማ እና አካባቢዋ ለሚገኙ ምዕመናን በተጠቀሰው ቀን እና ሰዓት ጊዜያቸውን […]

በአውሮፓ የወላጆች የውይይት መድረክ

ሚያዚያ 22 ቀን 2007 ዓ.ም. በአውሮፓ በአይነቱ ልዩ የሆነ የወላጆች የውይይት መድረክ «ሕጻናትን እና ታዳጊዎችን እንዴት ማሳደግ አለብን» በሚል ርዕስ ሚያዝያ 27 (May 5, 2015 GC) ቀን 2007ዓ.ም ከምሽቱ 20፡00 ሰዓት CET በፓልቶክ ይካሄዳል። እባክዎን ዝርዝር መርሃ ግብሩን ከማስታወቂያው ላይ ይመልከቱ።   ወስብሐት ለእግዚአብሔር።

ብፁዕ አቡነ ሙሴ የትንሣኤን በዓል አስከመልክቶ የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት አስተላለፉ

ሚያዚያ 04 ቀን 2007 ዓ.ም. የደቡብ፣ ደቡብ ምሥራቅ እና ደቡብ ምዕራብ አውሮፓ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ሙሴ የትንሣኤን በዓል አስከመልክቶ የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት አስተላልፈዋል። ብፁዕነታቸው ያስተላለፉትን መልእክት ከዚህ በታች ይመልከቱ። ወስብሐት ለእግዚአብሔር።  

በጀርመን ሀገር 2ኛው የሐዊረ ሕይወት ጉዞ ተካሄደ

በአውሮፓ ማዕከል መገናኛ ብዙኀን እና ቴክኖሎጂ አገልግሎት ክፍል መጋቢት 16 ቀን 2007 ዓ.ም. በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ማኀበረ ቅዱሳን በአውሮፓ ማዕከል የጀርመን ቀጣና ማዕከል አዘጋጅነት የሐዊረ ሕይወት (የሕይዎት ጉዞ) መርሐ ግብር ከመጋቢት 11 እስከ 13 /2007ዓ.ም በክሩፈልባክህ (Kroeffelbach) ከተማ በሚገኘው በቅዱስ እንጦንስ የግብፅ ገዳም (Sankt-Antonius Kloster) ለሁለተኛ ጊዜ ተካሄደ። በመርሐ ግብሩ ላይ ከተለያዩ የጀርመን […]