ዜና

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ አረፉ

አምስተኛው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ ዶ/ር አቡነ ጳውሎስ ፓትርያርክ፣ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳሳ ዘአክሱም፣ ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት፣ የዓለም አብያተ ክርስቲያናት ፕሬዚዳንት ነሐሴ 10 ቀን 2004 ዓ.ም. ከንጋቱ 11:00 ሰአት ከዚህ ዓለም በሞተ ሥጋ ተለይተዋል።

abune_paulose

እግዚአብሔር አምላክ የቅዱስነታቸውን ነፍስ በደጋግ አባቶች አቅፍ ውስጥ ያኑርልን፣ አሜን

አውሮፓ ማዕከል ፲፫ኛ ጠቅላላ ጉባኤውን አካሔደ

ሐምሌ ፲፩ ቀን  ፳፻፭ .ም.

በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክን ማኀበረ ቅዱሳን የአውሮፓ ማዕከል ፲፫ኛ ጠቅላላጉባኤውን ከሐምሌ ፭ እስከ ቀን ፳፻፭ ዓ.ም. በኖርዌይ ዋና ከተማ ኦስሎ አካሔደ። በጉባኤው ከተለያዩ የአውሮፓ አገራት የመጡ የማኀበሩ አባላት፣ ካህናትና የማኅበሩን አግልግሎት በተለያየ መንገድ የሚደግፉ ምእመናንተሳተፉ ሲሆን ከዋናዉ ማዕከል ደግሞ ሁለት ልዑካን ተገኝተዋል። 

Read more

ሀገረ ስብከቱ አብይ ጉባዔ አደረገ

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን በደቡብ፤ ደቡብ ምሥራቅና ምዕራብ አውሮፓ ሀገረ ስብከት በሮም ኢጣሊያ የሀገረ ስብከቱ አብይ ጉባዔ ተደረገ።

Read more