በጀርመን የክሮንበርግ ቅዱስ ዑራኤል ቤተ ክርስቲያን ቅዳሴ ቤቱ ተከበረ።

በጀርመን ንዑስ ማእከል

የካቲት 13 ቀን 2008 ዓ.ም.

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን በደቡብ፣ ምሥራቅ እና ምዕራብ አውሮፓ ሀገረ ስብከት የክሮንበርግ(ጀርመን) ቅዱስ ዑራኤል ቤተ ክርስቲያን በሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ በብፁዕ አቡነ ሙሴ የካቲት 6 ቀን 2008 ዓ.ም. ተባርኮ ቅዳሴ ቤቱ ተከብሯል። የቤተክርስቲያኑ መመሥረት በፍራንክፈርትና አካባቢው ከተወሰኑ ዓመታት ወዲህ በዓታ ለማርያም የፅዋ ማኅበርን በማቋቋም ተሰባሰበው ይገለገሉ በነበሩ ምዕመናን ጥረት የተጀመረ መንፈሳዊ እንቅስቃሴ ውጤት መሆኑ በዕለቱ ተገልጸል።

pic2

ይህ ለፍራንክፉርት ከተማ አቅራቢያ በምትገኘው በክሮንበርግ ከተማ የተተከለው ቅዱስ ዑራኤል ቤተ ክርስቲያን በጀርመን አገልግሎት በመስጠት ላይ የሚገኙ በኢ//// አብያተ ክርስቲያናት ቁጥር አሥራ ሦስት አድርሶታል።

በዓሉን አስመልክቶ ትምህርት እና ቡራኬ የሰጡት የሀገረ ስብከቱ ሊቀጳጳስ ብፁዕ አቡነ ሙሴ በቤተ ክርስቲያኑ መከፈት ምእመናኑን እንኳን ደስ ያላችሁ በማለት ለቤተክርስቲያኑ መመስረት አስተዋጽኦ ያደረጉትን ሁሉ ያመሰገኑ ሲሆን ወደፊት የሚጠበቅባቸው ኃለፊነት ትልቅ መሆኑን አስታውሰዋልበቤተ ክርስቲኑ መከፈት የነበሩ ውጣ ውረዶች መኖራቸውን በመግለጽ አስከመጨረሻው ድረስ የቤተ ክርስቲንን ውሳኔ አክብሮ መጓዝ በመቻላቸው ለምመናኑ ምስጋና አቅርበዋል።ለወደፊትም በመመካከር የቤተ ክርሰቲያኑን አገልግሎት አጠናክሮ መቀጠል ተገቢ መሆኑን አባታዊ መመሪያ አስተላልፈዋል

በዓሉን ምክንያት በማድረግ የሦሰት ቀን ጉባኤ ተዘጋጅቶ የነበረ ሲሆን ለተሳታፊ ምእመናን ሰፊ ትምህርት ተሰቷልሥርዓተ ቅዳሴው እንደተጠናቀቀ ቤተክርስቲያኑን እንዲያስተዳድ መልአከ ስብሐት ተክሌ ሲራክ (የካርልስሩሀ አቡነ ተክለሃይማኖት ቤተክርስቲያን አስተዳዳሪ) በብፁዕ አቡነ ሙሴ የተሾሙ ሲሆን እርሳቸውም የተሰጣቸውን ኃላፊነት ባግባቡ እንደሚወጡ በዮሐንስ ፲ ፥፩ ፡፲፮ ያለውን የወንጌል ክፍል በማንበብ ቃል ገብተዋልምእመናኑም ሹመታቸውን ሦስት ጊዜ ይደልዎ በማለት መቀበሉን የገለጸ ሲሆን ይህን የመሰለ ሹመት አሰጣጥ የቤተ ክርስቲኗ የቆየ ትውፊት መሆኑን በዕለቱ በሀገረ ስብከቱ ዋና ጸሐፊ በመጋቤ ምስጢር ኅሩይ ኤርሚያስ ለምዕመናን ሰፊ ማብራርያ ተስጥቷል

pic1

በበዓሉ ላይ በጀርመን ከተማ የሚገኙ የአድባራት አስተዳደሪዎችና አገልጋዮች፣የሰ/ት/ቤት አባላት፣ በዓሉን ምክንያት በማድረግ ከኢትዮጵያም የተጋበዙ መምህራን እንዲሁም ከመላው ጀርመን የመጡ በርካታ ምእመናን ተሳታፊዎች ነበሩ