ሥነ-ፍጥረት/ለልጆች

ነሐሴ 14 ቀን 2005 ዓ.ም. 

ልጆች እግዚአብሔር አምልካችን ሰማይ እና ምድርን እንዲሁም በውስጣቸው የሚኖሩትን ፍጥረታትን መቼ እንደፈጠራቸው ታውቃላችሁ? በዚህ ጽሁፍ ስለ ሥነ-ፍጥረት ትማራላችሁ።

እግዚአብሔር ፍጥረታትን ካለመኖር ወደመኖር ያመጣ የሁሉ ፈጣሪ ነው። እግዚአብሔርም በሳምንት ውስጥ ካሉ ሰባት ቀናት (ዕለታት) በመጀመሪያዎቹ ስድስት ቀናት የተለያዩ ፍጥረታትን ፈጠረ።

     kids1

 በየዕለቱም የፈጠራቸው ፍጥረታት ልዩ ልዩ ናቸው። 

በመጀመሪየው ቀን እሁድ ስምንት ፍጥረታትን ፈጠረ እነዚህም ሰማይ፣ መሬት፣ ውኃ፣ ነፋስ፣ እሳት  ጨለማ፣ ብርሃን እና መላእክትናቸው።  

kids2kids3kids4kids5kids6

ሁለተኛው ቀን ሰኞ:- ምድርና ሰማይን ሞልቶ የነበረውን ውኃ ወደ ላይና ወደ ታች በመክፈል ጠፈርን ፈጠረ። በምድር ላይ ያሉ የውሃ ክፍሎች ውቂያኖስ፣ባህር፣ሐይቅ እና ወንዝ ይባላሉ

kids7kids8kids9kids10

በሦስተኛው ቀን ማክሰኞ:- ዕፅዋትን እህልና ጥራጥሬ (አዝርዕት)፣ አትክልት፣ ፍራፍሬዎችን ሁሉ ፈጠረ።

kids11kids12kids13kids14

በአራተኛው ቀን ረቡዕ ፀሐይ፣ ጨረቃንና ከዋክብትን ፈጠረ።

kids15kids16kids17

በአምስተኛው ቀን ሐሙስ:- በባህር የሚኖሩትን እንስሳት ፤ እንዲሁም  አእዋፋትን ማለትም በውሃ ውስጥ እና በውሃ አከባቢ የሚኖሩ ወፎችን ፈጠረ።

kids18kids19kids20

በስድስተኛው ቀን ማለትም አርብ ዕለት:- በየብስ የሚኖሩ እንስሳትን (የቤት እንስሳትና የዱር አራዊት እንዲሁም በሰማይ የሚበሩ አእዋፋትን) ፈጠረ።

kids21kids22kids23kids24

 እግዚአብሔር አምላካችን ከላይ የተዘረዘሩትን ሁሉ አመቻችቶ ከፈጠረ በኋላ አርብ ዕለት ሰውን ማለትም የሁላችን አባት የሆነውን አዳምንና የሁላችን እናት የሆነቺውን ሄዋንን ፈጠረ። እግዚአብሔርም አዳምና ሔዋንን ለፈጠራቸው ፍጥረታት ማለትም ለባሕር እንስሳት፣ ለሰማይ ወፎች፥ ለምድር እንስሳት ሁሉ ገዢ (አዛዥ) አደረጋቸው።

በሰባተኛው ቀን ማለትም ቅዳሜ:- በዚህ እለት ግን ፍጥረት መፍጠሩን ጨርሶ የዕረፍት ቀን አደረገው።

ልጆች በአጠቃላይ እግዚአብሔር ፍጥረታትን የፈጠረው ለአላማ ነው። ሰው/እኛንና መላእክት ስሙን ለመቀደስና ክብሩን ለመውረስ ማለትም እርሱን ለማመስገን እና የመንግስተ ሰማያት ወራሾች ለመሆን ነው። የተቀሩት ፍጥረታት ግን የእግዚአብሔር መኖር መታወቂያ እንዲሆኑና እኛም እንድንማርባቸው፣ ለምግበ ሥጋ የሚያገለግሉ አዝርዕት፣ አትክልት፣ ፍራፍሬዎች፣ ሥጋቸው የሚበሉ እንሥሣት፣ እና ለምግበ ነፍስ ወይም በቤተመቅደስ ለቅዱስ ቁርባን የሚያገለግሉ ስንዴ፣ ወይን፣ ዕጣን ናቸው፡፡ 

በሉ ልጆች አሁን ጥያቄ እንጠይቃችሁና በሌላ ትምህርት እንገናኛለን ሰላም ሁኑ።

  1. እግዚአብሔር ፍጥረትን መቼ መቼ ፈጠረ?
  2. እግዚአብሔር በአጠቃላይ ስንት ፍጥረታትን ፈጠረ?
  3. ሰው ለምን ተፈጠረ?
  4. ከመላእክትና ከሰው ማን ቀድሞ ተፈጠረ?