• እንኳን በደኅና መጡ !

“ስብሐት ለእግዚአብሔር በሰማያት ወሰላም በምድር ሥምረቱ ለሰብእ፤ በሰማያት ምስጋና ተደረገ በምድርም እርቅ ተወጠነ ‹‹ሰላም ሆነ፡፡›› (ሉቃ. ፪፥፲፬)

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን፡፡ እንኳን ለብርሃነ ልደቱ በሰላም አደረሳችሁ! ለአዳም የሰጠውን ተስፋ ሊፈጽም በነቢያት አድሮ ያናገረው ትንቢት ሲደርስ ሰው የሆነ አምላክ የተወለደበት ዕለት (የልደት በዓል) እነሆ ደረሰና እኛም በዓሉን አክብረን ከበረከተ ልደቱ እንድንሳተፍ አበቃን፡፡ አምላካችን ለእኛ ላደረገልንና ለሚያደርግልን የቸርነት ሥራው ሁሉ ከምስጋና በቀር ሌላ አቅም ኖሮን መክፈል የምንችለው ነገር የለንም፡፡ ምክንያቱም […]

በአውሮፓ ተወልደው ላደጉ የአብነት ተማሪዎች ሢመተ ዲቁና ተሰጠ

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በስዊድንና ስካንዴኒቪያን ሀገረ ስብከት የኦስሎ መካነ ቅዱሳን ቅዱስ ገብርኤል ወአቡነ ተክለሃይማኖት ቤተክርስቲያን በአውሮፓ ተወልደው ላደጉ ሰባት የአብነት ተማሪዎች ዲቁና ተሰጠ።  ለ 4 ዓመታት የአብነት ትምህርታቸውን ሲከተታሉ ለነበሩት ሰባት አዳጊ የአብነት ተማሪዎች ኅዳር 28 ቀን 2012 ዓ.ም. በሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ በብጹዕ አቡነ ኤልያስ ማዕርገ ዲቁና ተሰጥቷል፡፡  የኢጣሊያና አካባቢው ሀገረ ስብከት […]

በፍራንክፈርት ከተማ ዐውደ ርእይ ተካሄደ

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ማኅበረ ቅዱሳን በአውሮፓ ማእከል የጀርመን ንኡስ ማእከል አዘጋጅነት “ኦርቶዶክሳዊት ተዋህዶ ቤተክርስቲያንን አስተምህሮዋን እንጠንቅቅ፤ ድርሻችንን እንወቅ” በሚል መሪ ቃል ኅዳር 28 ቀን 2012 ዓ.ም. በፍራንክፈርት ምስካየ ኅዙናን መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን ዐውደ ርእይ ተካሄደ:: ዐውደ ርእዩን የጀርመን እና አካባቢው ሀገረ ስብከት ሥራ አስኪያጅና የደብሩ አስተዳዳሪ መልአከ መዊዕ ልሳነ […]

በቅድስት ቤተ ክርስቲያን እየደረሰ ያለውን ጥቃት በመቃወም በተለያዩ የአውሮፓ አገራት ሰላማዊ ሰልፍ ተደረገ፡፡

መንግሥት የዜጎችን ደኅንነት የማስጠበቅ ግዴታ ያለበት በመሆኑ በአገር ቤት በምትገኘው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን እና በልጆቿ ላይ እየደረሰ ያለውን ጥቃት የኢትዮጵያ መንግሥት እንዲያስቆም፣ አብያተ ክርስቲያነቱን ያቃጠሉ በልጆቿ ላይም ግፍን ያደረጉ ሰዎችን ለፍርድ እንዲያቀርብ ለመጠየቅ በአውሮፓ በሚገኙ ሦስቱ አህጉረ ስብከት (የስዊድንና የስካንዴኒቪያን ሀገረ ስብከት ፣ ጀርመንና አካባቢው ሀገረ ስብከት እና የጣልያንና አካባቢው ሀገረ ስብከት) አስተባባሪነት […]

ሁለቱ እንስሶች

በአስናቀች ታመነ ምንጭ: ስምዐ ጽድቅ ጋዜጣ ከሰኔ 16 – 30/ 2011 ዓ.ም. ዕትም ሰላም ልጆች እንደምን አላችሁ? ደኅና ናችሁ ለዚህ ቀን ያደረሰን እግዚአብሔር ይመስገን! አሜን! ልጆች ዛሬ ከሌላው ቀናት የተለየ ታሪክ ይዘንላችሁ ቀርበናል። ጽሑፉን ከማንበባችሁ በፊት አስቀድማችሁ እስቲ ገምቱ ስለምን ይመስላችኋል፧ ስለቅዱሳን ሰዎች ካላችሁ እንደዛ አይደለም። ስለምን እንደሆነ ልንገራችሁ ስለ እንስሳት ነው። ስለየትኞቹ እንስሳት ካላችሁኝ […]


ይህን በመጫን ይለግሱ

የቤተ ክርስቲያንን አገልግሎት ይደግፉ!



የስብከተ ወንጌል ማስፋፊያ  


ገዳማትና አብነት ት/ቤቶች 


የቴሌቪዥን እና ራዲዮ አገልግሎት 

ማስታወቂያ

Nothing Found

Sorry, no posts matched your criteria

©2019. Mahibere Kidusan Europe Center - All Rights Reserved. Website by MK-IT