ልዩ መርሐ ግብር በእንግሊዝ አገር፣ ሊድስ ከተማ

 

መስከረም  18 ቀን 2006 ዓ.ም.

በሰሜን ምዕራብ አውሮፓ ሀገረ ስብከት የሊድስ ደብረ ስብሐት መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን እና በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ማኅበረ ቅዱሳን ትብብር ገቢው ለአብነት ት/ቤቶች መርጃ የሚውል ልዩ መርሐ ግብር ሊዘጋጅ ነው።

”በእንተ ስማ ለማርያም” በሚል መሪ ቃል የተሰየመው ይህ መርሐ ግብር ቅዳሜ መስከረም ፳፭ ቀን ፳፻፮ ዓ.ም (5 Oct 2013) እንደሚካሄድ ከዝግጅቱ አስተባባሪዎች የተገለጸ ሲሆን መርሐ ግብሩም በሊድስ ደብረ ስብሐት መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን ከቅዳሴ አገልግሎት በኋላ እንደሚካሄድ ለመረዳት ተችሏል።

Read more

የደቡብ፣ የደቡብ ምሥራቅና ምዕራብ አውሮፓ ሀ/ስብከት ዓመታዊ ጉባኤውን አካሄደ

ጳጉሜን 02 ቀን 2005 ዓ.ም. 

 በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የደቡብ፣ የደቡብ ምሥራቅና ምዕራብ አውሮፓ ሀ/ስብከት ከነሐሴ 24 – 25፣ 2005 ዓ.ም በጀርመን ሀገር በሚገኘው የግብፅ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ እንጦንስ ገዳም ዓመታዊ ጉባኤውን አካሄደ፡፡ በዕለቱም ብፁዕ አቡነ ሙሴ የሀ/ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ እና የቅዱስ ሲኖደስ አባል፣ የአድባራት አስተዳዳሪዎች፣ የሰበካ ጉባኤያት እና የመንፈሳዊያት ማኅበራት ተወካዮች በአባልነት ተገኝተዋል፡፡ ጉባኤው በብፁዕነታቸው ቡራኬ በጸሎት ከተከፈተ በኋላ ከቀረቡ አጀንዳዎች መካከል ሀገረ ስብከቱን ማዋቀር፣ የመንበረ ጵጵስና ጽ/ቤት መቀመጫ መወሰን እና በሀገረ ስብከቱ ሥር ባሉ አጥቢያ አብያተክርስቲያናት ወቅታዊ ችግሮች ተወያይቶ መወሰን የሚሉ ሦስት አጀንዳዎችን መርጦ በማጽደቅ ውይይቱን ጀምሯል፡፡

His Grace Abune Mussie

ብፁዕ አቡነ ሙሴ

Read more

የ6ኛው ፓትርያርክ ሥርዓተ ሢመት ተፈጸመ

የካቲት 24 ቀን 2005 ዓ.ም.

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን 6ኛ ፓትርያርክ ሆነው የተመረጡት የብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ሥርዓተ ሢመት በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል የካቲት 24 ቀን 2005 ዓ.ም. ተፈጸመ፡፡

ከዋዜማው ጀምሮ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን የማኅሌት ጸሎት በማድረስ የተጀመረው ሥርዓተ ጸሎት ከሌሊቱ 10፡00 ሰዓት ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ከአቃቤ መንበረ ፓትርያርኩ ብፁዕ አቡነ ናትናኤል፤ እንዲሁም ብፁዐን ሊቃነ ጳጳሳት ጋር በመሆን በመንበረ ጸባዖት ቅድሥት ሥላሴ ካቴድራል በመገኘት ሥርዓተ ጸሎቱ ቀጥሏል፡፡

Read more

የግቢ ጉባኤያት በእንግሊዝ ፡ ምዝገባ ጀምረናል!

«የግቢ ጉባኤ» ምንድን ነው?

ማኅበረ ቅዱሳን ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ከሰጠችው ኃላፊነት አንዱ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ውስጥ መደበኛ ትምህርታቸውን በመማር ላይ የሚገኙ ኦርቶዶክሳውያን ወጣቶች የሚኖራቸውን የተጣበበ ጊዜ እና የአኗኗር ዘይቤያቸውን ያገናዘበ ልዩ መርሐ ግብር በማዘጋጀት መንፈሳዊ ትምህርት እንዲያገኙና በኋላ በሥራ ዓለም ሲሰማሩ በሃይማኖት ጸንተው፣ በምግባር ታንጸው በመገኘት በእውቀታቸው፣ በጉልበታቸውና በገንዘባቸው ቤተ ክርስቲያናቸውን እንዲያገለግሉ ማድረግ ነው። ይህንን ትምህርት የሚከታተሉበት እያንዳንዱ መንፈሳዊ ጉባኤ ወይም አንድነት ደግሞ «የግቢ ጉባኤ» በመባል ይታወቃል።

Read more

ማኅበረ ቅዱሳን የቴሌቪዠን መርሐ ግብር ሊጀምር ነው

መስከረም 12 ቀን 2005 ዓ.ም.
በዲ/ን ዮሴፍ ይኲኖ አምላክ
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን፣ ማኅበረ ቅዱሳን ከጥቅምት 4 ቀን 2005 ዓ.ም ጀምሮ ዘወትር በየሳምንቱ እሑድ ጧት ከ3፡30 እስከ 4፡00 ሰዓት የሚቆይ መርሐ ግብር በኢትዮጵያ ብሮድ ካስቲንግ ሰርቪስ ቴሌቪዠን (EBS TV) ለመጀመር ሙሉ ዝግጅት ማጠናቀቁ ተገለጠ፡፡
በማኅበረ ቅዱሳን ኅትመትና ኤሌክትሮኒክስ ሚዲያ፥ የሬድዮና ቴሌቪዠን ፕሮግራም አስተባባሪ የሆኑት ዲያቆን ሄኖክ ኀይሌ ለመካነ ድራችን በሰጡት መግለጫ፡- ማኅበሩ ከተመሠረተበት ጊዜ አንሥቶ ላለፉት ሃያ ዓመታት በልዩ ልዩ የኅትመት ውጤቶች እንዲሁም በመካነ ድር (website) እና በሬድዮ አማካኝነት በሃይማኖታዊና ማኅበራዊ ጉዳዮች ላይ ሰፊ ትምህርት ሲሰጥ መቆየቱን አስታውሰው፤ አሁን ደግሞ በልዑል እግዚአብሔር ፈቃድ በሳምንት አንድ ጊዜ የ30 ደቂቃ መርሐ ግብር ለመጀመር ትናንት መስከረም 11 ቀን 2005 ዓ.ም  ከኢ.ቢ.ኤስ ቴሌቪዥን የሥራ ሓላፊዎች ጋር ለአንድ ዓመት የሚቆይ ስምምነት ማኅበሩ መፈራረሙን  ገልጸዋል፡፡
ዲያቆን ሄኖክ በዚሁ ገለጻቸው፥ በአውሮፓና አሜሪካ እንዲሁም በሀገር ውስጥ በ17515 ኪሎ ኸርዝ፣ በ16 ሜትር ባንድ አጭር ሞገድ ዘወትር አርብ ከምሽቱ 3፡30 እስከ 4፡30 ድረስ የሚተላለፈውን የሬድዮ ዝግጅት በመከታተልና ገንቢ አሰተያየት በመስጠት ምእመናን ላደረጉት ተሳትፎ በማመስገን በአዲሱ የቴሌቪዥን መርሐ ግብር ላይም ተመሳሳይ ተሳትፎ እንዲያደርጉ ጠይቀዋል፡፡
ማኅበሩ ከጥቅምት 2003 ዓ.ም አንሥቶ በአጭር ሞገድ  የሬድዮ መርሐ ግብር መጀመሩ ይታወሳል፡፡
በዲ/ን ዮሴፍ ይኲኖ አምላክ
መስከረም 12 ቀን 2005 ዓ.ም.
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን፣ ማኅበረ ቅዱሳን ከጥቅምት 4 ቀን 2005 ዓ.ም ጀምሮ ዘወትር በየሳምንቱ እሑድ ጧት ከ3፡30 እስከ 4፡00 ሰዓት የሚቆይ መርሐ ግብር በኢትዮጵያ ብሮድ ካስቲንግ ሰርቪስ ቴሌቪዠን (EBS TV) ለመጀመር ሙሉ ዝግጅት ማጠናቀቁ ተገለጠ፡፡

Read more

የማኅበረ ቅዱሳን 10ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ

መስከረም 3 ቀን 2004 ዓ.ም.
በእንዳለ ደምስስ
ሪፖርታዥ
የማኅበረ ቅዱሳን 10ኛ ጠቅላላ ጉባኤ በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ስብከተ ወንጌል አዳራሽ ብፁዐን ሊቃነ ጳጳሳት፤ የጠቅላይ ቤተ ክህነት፤ የመምሪያ ሓላፊዎች፤ ቀሳውስትና ካህናት፤ የፌደራል ጉዳዮች የሃይማኖት ተወካዮችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት ነሐሴ 30 ቀን 2004 ዓ.ም.በድምቀት ተጀመረ፡፡
በእንዳለ ደምስስ
መስከረም 3 ቀን 2004 ዓ.ም.
ሪፖርታዥ
TAKLL2004_534
የማኅበረ ቅዱሳን 10ኛ ጠቅላላ ጉባኤ በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ስብከተ ወንጌል አዳራሽ ብፁዐን ሊቃነ ጳጳሳት፤ የጠቅላይ ቤተ ክህነት፤ የመምሪያ ሓላፊዎች፤ ቀሳውስትና ካህናት፤ የፌደራል ጉዳዮች የሃይማኖት ተወካዮችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት ነሐሴ 30 ቀን 2004 ዓ.ም.በድምቀት ተጀመረ፡፡

ብፁዕነታቸው አዲሱን ዓመት አስመልክቶ ቃለ ምዕዳንና ቡራኬ ሰጡ፡፡

በዲ/ን ዮሴፍ ይኲኖ አምላክ
ጳጉሜን 5 ቀን 2004 ዓ.ም.
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ዐቃቤ መንበረ ፓትርያርክና የአርሲ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ናትናኤል ለመላው ኢትዮጵያውያንና ኢትዮጵያውያት ባስተላለፉት መልእክት፡- “የዘመናት ጌታ እግዚአብሔር አምላካችን እንኳን ከዘመነ ዮሐንስ 2004 ዓ.ም. ወደ ዘመነ ማቴዎስ 2005 ዓ.ም. በሰላም አደረሳችሁ፤ ለሚቀጥለውም ዘመን በቸርነቱ ጠብቆ በሰላምና በጤና እንዲያደርሳችሁ ቤተ ክርስቲያናችን ዘወትር ያለ ማቋረጥ ጸሎቷን ወደ ፈጣሪ ታቀርባለች” ካሉ በኋላ ሁሉም ኅብረተሰብ መልካም ታሪክን ለማስመዝገብ በተሰለፈበት ዓላማ የሚጠበቅበትን ድርሻ ማበርከት እንደሚገባው አሳስበዋል።

የማኅበረ ቅዱሳን 10ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ ተጠናቀቀ

ጉሜን 5 ቀን 2004 ዓ.ም.
በእንዳለ ደምስስ
ነሐሴ 30 ቀን 2004 ዓ.ም. የተጀመረው የማኅበረ ቅዱሳን መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ በታቀደለትና በወጣለት መርሐ ግብር መሰረት በማካሔድ ጳጉሜን 2 ቀን 2004 ዓ.ም. ከለሊቱ 9፡00 ስዓት በድምቀት ተጠናቀቀ፡፡
ጳጉሜን 2 ቀን 2004 ዓ.ም.  ለሊት በተካሔደው  የጠቅላላ ጉባኤው ቀጣይ ውይይት በቀኑ መርሐ ግብር የአራት ዓመት ስልታዊ እቅድ ረቂቅ ላይ የተካሔደውን የቡድን ውይይት ውጤት በየቡድኖቹ ሰብሳቢዎችና ጸሐፊዎች አማካይነት እንዲቀርቡ በማድረግ በጠቅላላ ጉባኤው ውይይት ተካሒዶበት ጸድቋል፡፡ በቀጣይነትም የማኅበረ ቅዱሳን ዋና ዋና የአገልግሎት ክፍሎች ስለክፍሎቻቸው እንቅስቃሴ ለጠቅላላ ጉባኤው ግንዛቤ የማስጨበጥና አሁን ያሉበትን ደረጃ አቅርበዋል፡፡
በእንዳለ ደምስስ
ጉሜን 5 ቀን 2004 ዓ.ም.
ነሐሴ 30 ቀን 2004 ዓ.ም. የተጀመረው የማኅበረ ቅዱሳን መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ በታቀደለትና በወጣለት መርሐ ግብር መሰረት በማካሔድ ጳጉሜን 2 ቀን 2004 ዓ.ም. ከለሊቱ 9፡00 ስዓት በድምቀት ተጠናቀቀ፡፡
ጳጉሜን 2 ቀን 2004 ዓ.ም.  ለሊት በተካሔደው  የጠቅላላ ጉባኤው ቀጣይ ውይይት በቀኑ መርሐ ግብር የአራት ዓመት ስልታዊ እቅድ ረቂቅ ላይ የተካሔደውን የቡድን ውይይት ውጤት በየቡድኖቹ ሰብሳቢዎችና ጸሐፊዎች አማካይነት እንዲቀርቡ በማድረግ በጠቅላላ ጉባኤው ውይይት ተካሒዶበት ጸድቋል፡፡ በቀጣይነትም የማኅበረ ቅዱሳን ዋና ዋና የአገልግሎት ክፍሎች ስለክፍሎቻቸው እንቅስቃሴ ለጠቅላላ ጉባኤው ግንዛቤ የማስጨበጥና አሁን ያሉበትን ደረጃ አቅርበዋል፡፡

ማኅበረ ቅዱሳን የሥራ አመራር ጉባኤ ምርጫ አካሄደ

በእንዳለ ደምስስ

ጳጉሜን 2 ቀን 2004 ዓ.ም.

ከነሐሴ 30 ቀን 2004 ዓ.ም. ጀምሮ እየተካሄደ የሚገኘው የማኅበረ ቅዱሳን 10ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ በመጠናቀቅ ላይ ነው፡፡

mk_10th_general_assembly

ጳጉሜን 1 ቀን 2004 ዓ.ም. ጠዋት በተካሄደው የጠቅላላ ጉባኤው ስብሰባ “በማኅበረ ቅዱሳን የአገልግሎት ጉዞ የአባላት ተሳትፎና የወደፊት ሁኔታ” በተመለከተ ጥናት የቀረበ ሲሆን በአባላት ሰፋ ያለ ውይይት ተካሂዷል፡፡ ከሰዓት በኋላ በቀጠለው ስብሰባም “ስልታዊ ለውጥ ለሁለንተናዊ የቤተ ክርስቲያን እድገት ከማኅበረ ቅዱሳን ተልእኮና አቅም አንጻር” በሚል በዲ/ን ያረጋል አበጋዝና ዲ/ን ብርሃኑ አድማስ ጥናታዊ ጽሑፍ ቀርቦ በአባላት ውይይት ተደርጎበታል፡፡ በመጨረሻም የጽ/ቤት ግንባታ ሪፓርት ቀርቦ የመርሐ ግብሩ ፍጸሜ ሆኗል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ

ቅዱስ ሲኖዶስ ጸሎተ ምህላ እንዲደረግ ወሰነ

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤት ነሐሴ 30/2004 ዓ.ም. ለመገናኛ ብዙኅን በሰጠው መግለጫ ከጳጉሜ 1 ቀን 2004 ዓ.ም. እስከ መስከረም 10/2005 ዓ.ም. ድረስ ምእመናን ለሁለት ሱባኤያት በመላዋ ኢትዮጵያና በውጭ ሀገር በሚገኙ አህጉረ ስብከቶች በሚገኙ ገዳማት፣ አድባራትና አብያተ ክርስቲያናት ጸሎተ ምህላ እንዲደረግ ወስኗል፡፡ ቅዱስ ሲኖዶስ ጸሎተ ምኅላውን ያወጀበት ምክንያት ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ በነበሩበት ዘመን በሃይማኖታዊና ማኅበራዊ ጉዳዮች ላይ ሰፊ ሥራ የሠሩ አባት እንደነበሩ ጠቅሶ ለቤተ ክርስቲያኒቱ ሁለንተናዊ ዕድገት ፤ ለሀገሪቱ ሰላምና አንድነት የሚበጅ ተተኪ አባት(ፓትርያርክ) እግዚአብሔር ባወቀ መርጦ እንዲያስቀምጥ ካህናትና ምእመናን በጸሎተ ምኅላው እንዲሳተፉ አሳስቧል፡፡

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤት ነሐሴ 30/2004 ዓ.ም. ለመገናኛ ብዙኅን በሰጠው መግለጫ ከጳጉሜ 1 ቀን 2004 ዓ.ም. እስከ መስከረም 10/2005 ዓ.ም. ድረስ ምእመናን ለሁለት ሱባኤያት በመላዋ ኢትዮጵያና በውጭ ሀገር በሚገኙ አህጉረ ስብከቶች በሚገኙ ገዳማት፣ አድባራትና አብያተ ክርስቲያናት ጸሎተ ምህላ እንዲደረግ ወስኗል። ቅዱስ ሲኖዶስ ጸሎተ ምኅላውን ያወጀበት ምክንያት ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ በነበሩበት ዘመን በሃይማኖታዊና ማኅበራዊ ጉዳዮች ላይ ሰፊ ሥራ የሠሩ አባት እንደነበሩ ጠቅሶ ለቤተ ክርስቲያኒቱ ሁለንተናዊ ዕድገት ፤ ለሀገሪቱ ሰላምና አንድነት የሚበጅ ተተኪ አባት(ፓትርያርክ) እግዚአብሔር ባወቀ መርጦ እንዲያስቀምጥ ካህናትና ምእመናን በጸሎተ ምኅላው እንዲሳተፉ አሳስቧል።

ምንጭ፡- ማኅበረ ቅዱሳን – ዋናው ማዕከል ድረ ገጽ