የመስቀል (ደመራ) በዓል በፊንላንድ ርዕሰ መዲና በሄልሲንኪ ለመጀመሪያ ጊዜ በአደባባይ በድምቀት ተከበረ።
በአውሮፓ ማእከል ኅ/ኤ/ሚ ክፍል
መስከረም 26 ቀን 2009 ዓ.ም
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በሰሜን ምዕራብ አውሮፓ ሀገረ ስብከት የሄልሲንኪ ደብረ አሚን አቡነ ተክለ ሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን አዘጋጅነት በተካሄደው የደመራ በዓል ላይ የደብሩ አገልጋይ ካህናት ዲያቆናት፣ የሰንበት ትምህርት ቤት መዘምራን እና ምዕመናን ተገኝተዋል። በተጨማሪም የሄልሲንኪ ደብረ ሰላም መድኃኔዓለም የኤርትራ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ካህናት እና ምእመናን፣ ከከተማው የተለያዩ መሥሪያ ቤቶች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች እና ጋዜጠኞችም በበዓሉ ላይ ተካፍለዋል። Read more