ዜና

የስዊዘርላንድ ግንኙነት ጣቢያ አዉደ ርዕይ አካሄደ።

 በስዊዘርላንድ ግንኙነት ጣቢያ

መስከረም 1 ቀን 2010 ዓ.ም.

ነሐሴ ፳ እና ፳፩ ፳፻፱ በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤ/ማ/ መምሪያ ማኅበረ ቅዱሳን አዉሮፓ ማእከል የስዊዘርላንድ ግንኙነት ጣቢያ ከስዊዘርላንድ የሎዛን ደብረ ኃይል ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን ጋር በመተባበር በስዊዘርላንድ ሀገር ለሁለተኛ ጊዜ ልዩ የአብነት እና የገዳማት ቀን በሎዛን ከተማ አካሂዷል። የዕለቱ መሪ ቃል ”ኑ አብረን እንስራ፤ ለውጥም እናመጣለን” የሚል ነበር። መርሐ ግብሩን በስዊዘርላንድ የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ ክርስቲያን አስተዳዳሪ የሆኑት መልአከ ገነት ቆሞስ አባ ኃይለ ጊዮርጊስ መሪነት በጸሎተ ተጀምሯል።  ከጸሎቱ መርሐ ግብር በኃላ መልአከ ገነት ቆሞስ አባ ኃይለ ጊዮርጊስ የእንኳን አደረሳችሁ ንግግር ያደረጉ ሲሆን በንግግራቸውም ከኢትዮጵያ የመጡትን ልዑካን አመስግነው ቤተክርስቲያናችን ዛሬ ያለንበት ድረስ ለመድረስ ገዳማት እና የአብነት ትምህርት ቤቶች ያደረጉትን አስተዋፅኦ ገልፀው አውደ ርዕዩን በይፋ ከፍተዋል። Read more

በእንግሊዝ ሀገር የመጀመሪያው ሐዊረ-ሕይወት ተካሄደ

በዩናይትድ ኪንግደም ንዑስ ማእከል

ነሐሴ 8 ቀን 2009 ዓ.ም.

በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤ/ማ/ መምሪያ ማኅበረ ቅዱሳን አዉሮፓ ማእከል የዩናይትድ ኪንግደም ንዑስ ማእከል ያዘጋጀዉ የመጀመሪያ ዙር የሐዊረ-ሕይወት መርሐ ግብር ሐምሌ 29 ቀን 2009 ዓ.ም. በዩናይትድ ኪንግደም የግብጽ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ማእከል (ስቲቪኔጅ) ተካሄደ። በተለያዩ የእንግሊዝ ከተሞች የሚኖሩ ከ200 በላይ የሚሆኑ ምእመናን መነሻቸዉን ለንደን እና በርሚንግሃም ከተሞች ባደረጉ አራት አዉቶቡሶች ወደ ቦታዉ ተጉዘዋል። Read more

በማኅበረ ቅዱሳን የአውሮፓ ማዕከል 17ኛውን ጠቅላላ ጉባኤውን አካሄደ።

በአውሮፓ ማእከል ኅ/ኤ/ሚዲያ ክፍል

ሐምሌ 8 ቀን 2009 ዓ.ም.

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደረጃ መምሪያ ማኅበረ ቅዱሳን የአውሮፓ ማእከል አስራ ሰባተኛውን ጠቅላላ ጉባኤ “ታገኙ ዘንድ ሩጡ “፩ቆሮ ፱÷፳፬  በሚል መሪ ቃል በጀርመን ክሮፍልባህ የግብፅ ቅዱስ እንጦስ ገዳም የአካባቢው አቢያተ ክርስቲያናት አስተዳዲሪዎች ፣ የሀገረ ስብከቱ ተወካይ፣ የማኅበሩ አባላት እና ተጋባዥ እንግዶች በተገኙበት ከዓርብ ሰኔ ፴ እስከ እሁድ ሐምሌ ፪ ቀን አካሄደ። Read more

የጣሊያን ንዑስ ማእከል አውደ ርእይ አካሄደ

በጣሊያን ንዑስ ማእከል

ሰኔ 25 ቀን 2009 ዓ.ም.

ማኅበረ ቅዱሳን የጣሊያን ንዑስ ማእከል ግንቦት ፲፱ እና ፳ ፳፻፱ ዓ/ም ከሮም ደብረ ጽዮን ቅድስት ማርያም እና ቅዱስ ኡራኤል ቤተክርስቲያን ጋር በመተባበር “ አብረን እንስራ ለውጥም እናመጣለን!” በሚል መሪ ቃል ዐውደ ርእይ አካሄደ። ዐውደ ርእዩ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በሕገ ልቡና በሕገ ኦሪትና በሕገ ወንጌል ያደረገችው ጉዞ፣ የገዳማትና አብነት ትምህርት ቤቶችን ታሪክ እና አሁን ያሉበትን ነባራዊ ሁኔታ፣ ዝክረ ቅዱስ ያሬድ እና ማኅበረ ቅዱሳን በሚሉ አራት ዓቢይ  ክፍሎች የተከፈለ ነበረ። Read more

በኖርዌይ ንዑስ ማእከል የመጀመሪያው ሐዊረ ሕይወት ተካሄደ

በኖርዌይ ንዑስ ማእከል

ሰኔ 20 ቀን 2009 ዓ.ም.

በማኅበረ ቅዱሳን አውሮፓ ማእከል፣ የኖርዌይ ንዑስ ማእከል ከክርስቲያንሳንድ ቅድስት ማርያም ቤተክርስቲያን ጋር በመተባበር በሀገረ ኖርዌይ የመጀመሪያውን የሐዊረ ሕይወት መርሐ ግብር በክርስቲያንሳንድ ከተማ መጋቢት ፳፫ እና ፳፬  ቀን ፳፻፱ ዓ.ም አካሔደ። በሐዊረ ሕይወቱ ላይ ከክርስቲያንሳንድ ከተማ እና በአቅራቢያው ከሚገኙ ሌሎች ከተሞች የተሰባሰቡ ቁጥራቸው ከ40 እስከ 50 የሚደርሱ ምእመናን ተሳትፈዋል። Read more

የጀርመን ንዑስ ማእከል አራተኛውን የሐዊረ ሕይወት አካሄደ

በጀርመን ንዑስ ማእከል

ሰኔ 20 ቀን 2009 ዓ.ም.

የጀርመን ንኡስ ማእከል ከመጋቢት ፲፯ እስከ መጋቢት ፲፱ ቀን ፳፻፱ ዓ.ም አራተኛውን የሐዊረ ሕይወት መርሐ ግብር በጀርመን የግብፅ አቡነ እንጦንስ ገዳም አካሄደ፡፡ በዚህ ሐዊረ ሕይወት ከጀርመን እና ከሌሎች አውሮፓ ሀገራት የተውጣጡ ካህናት፣ ዲያቆናት እና ምዕመናን የተሳተፉ ሲሆን በጠቅላላ የተጓዦች ብዛት 250 ነበር።  የጕዞ መነሻውን መጋቢት ፲፯ ከቀኑ 11 ሰዓት ከፍራንክፈርት ዋናው ባቡር ጣቢያ በማድረግ ወደ ገዳሙ የአንድ ሰዓት ተኩል ጉዞ በባቡርና ከዛም የቻለ በእግር  የ30 ደቂቃ መንገድ በመጓዝ ወደ ገዳሙ ተደርሷል። በተዘጋጀው መርሐ ግብር መሠረት ዓርብ ምሽት በመጋቤ ሐዲስ ቀሲስ አባተ “የሕይወት ጉዞ” በሚል ርዕስ ትምህርት ለመእመናን ተሰጥቷል። በመቀጠልም ቅዳሜ ጠዋት 11፡30 ኪዳንና ቅዳሴ እንደሚኖር ማሳሰቢያ ከተሰጠ በኋላ የዕለቱ መርሐ ግብር በጸሎት ተዘግቷል። Read more

የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ ክርስቲያን መዝሙራት ከየት ወዴት በሚል ለሦስተኛ ጊዜ የተዘጋጀ የግንዛቤ ማስጨበጫ መርሐግብር በእንግሊዝ ለንደን ከተማ ተካሄደ።

በእንግሊዝ ንዑስ ማእከል

ሰኔ 16 ቀን 2009 ዓ.ም.

በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ ክርስቲያን ስም የሚወጡ መዝሙራት ቁጥር እየተበራከቱ ቢሄዱም በተለይ በቅርብ ጊዜ የወጡ አንዳንድ መዝሙራት ግን ከያሬዳዊ ዜማ ይልቅ ለዓለማዊ ዘፈን ያደሉ መሆናቸዉን ተከትሎ ማኅበረ ቅዱሳን ባካሄደዉ ጥናት እየታዩ ያሉትን ችግሮችና የመፍትሔ ሐሳቦችን በመረጃ በማስደገፍ አቅርቦ ነበር። የዚህ ጥናት ዉጤት በተለያዩ የሀገር ዉስጥና የዉጭ ሀገራት ጉባኤያት ላይ የቀረቡ ሲሆን በማኅበረ ቅዱሳን የዩኬ (እንግሊዝ) ንዑስ ማእከል ከሚመለከታቸዉ የቤተ ክርስቲያን አካላት ጋር በመተባበር በ2008 ዓ.ም በበርሚንግሃም እና በኖቲንግሃም ከተሞች በእያንዳንዳቸዉ የተሳካ መርሐ ግብር ተካሂዶ ነበር። Read more

በሆላንድ ሐዊረ ሕይወት ተካሔደ።

በሆላንድ ንዑስ ማእከል

መጋቢት 26 ቀን 2009 ዓ.ም

በማኅበረ ቅዱሳን አውሮፓ ማእከል የሆላንድ ንዑስ ማዕከል የመጀመሪያውን ሐዊረ ሕይወት በሆላንድ ሊቨልደ ግዛት በሚገኘው የግብፅ ኮፕት ቅዱስ ቴዎድሮስ ኦርቶዶክስ ገዳም መጋቢት ፱ ፳፻፱ ዓ.ም. አካሔደ።

ሐዊረ ሕይወቱ በአባቶች ጸሎት የተከፈተ ሲሆን በመቀጠልም የመጀመሪያ የሆነው የነገረ ክርስቶስ ትምህርት በመጋቤ ምስጢር ኅሩይ ኤርምያስ ተሰጥቷል። ከሰአት በኋላ ከተሳታፊዎች ለተነሱ መንፈሳዊ ጥያቄዎች በአባቶች በኩል መልስ ተመልሷል።ከዚያም በኋላ በዲ/ን መስፍን ኃይሌ ነገረ ቅዱሳን የሚመለከት ትምህርት ለጉባዔው ቀርቧል ። Read more

በቩርዝቡርግ ቅዱስ ማርቆስ ቤተ ክርስቲያን ዐውደ ርእይ ተካሔደ።

በጀርመን ንዑስ ማእከል

መጋቢት 26 ቀን 2009 ዓ.ም

በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ የሰ/ት/ቤ/ማ/መምርያ ማኅበረ ቅዱሳን አውሮፓ ማእከል የጀርመን ንዑስ ማእከል እና የቩርዝቡርግ ቅዱስ ማርቆስ ሰበካ ጉባዔ በመተባበር ከየካቲት ፳፭ እስከ የካቲት ፳፮ ቀን ፳፻፱ ዓ.ም ዐውደ ርእይ እና የስብከተ ወንጌል መርሐ ግብር አካሄዱ። ዐውደ ርእዩ የቩርዝቡርግ ቅዱስ ማርቆስ ቤተ ክርስቲያን አገልጋይ በሆኑት በቀሲስ ገብረማርያም እና የአውሮፓ ማእከል ሰብሳቢ በሆኑት በቀሲስ ዶ/ር ያብባል ሙሉዓለም የተከፈተ ሲሆን ፍኖተ ቤተ ክርስቲያን፣ ዝክረ ገዳማት ወቤተ ጉባኤ እና ማኅበረ ቅዱሳን የሚሉ ሦስት ክፍሎችን ያካተተ ነበረ። Read more

የሰሜን ምዕራብ አውሮፓ ሀገረ ስብከት ሁለት የወረዳ ቤተ ክህነት ጽሕፈት ቤቶችን አዋቀረ።

በአውሮፓ ማእከል ኅ/ኤ/ሚ ክፍል

የካቲት 2 ቀን 2009 ዓ.ም

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰሜን ምዕራብ አውሮፓ ሀገረ ስብከት የወረዳ ቤተክህነት ጽሕፈት  ቤቶችን  አዋቀረ። ሀገረ ስብከቱ የመላው አውሮፓ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ እና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል ብፁዕ አቡነ ሙሴ መቀመጫ በሆነችው በጀርመን ሀገረ በምትገኘው የሮሰልስሃይም ከተማ ጥር 19 እና  20 ቀን 2009 ዓ.ም ጉባኤውን  አካሂዷል። በጉባኤው ላይ የአህጉረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ፣ በሸንገን ስቴት ውስጥ ባሉ የአውሮፓ ሀገራት ያሉ የሀገረ ስብከቱ አጥቢያ አብያተ ክርስቲያናት አስተዳዳሪዎች እና ተወካዮች የተገኙ ሲሆን በተለያዩ አጀንዳዎች ላይ ተወያይቶ ውሳኔዎችንም አሳልፏል። Read more