ዜና

የመስቀል (ደመራ) በዓል በፊንላንድ ርዕሰ መዲና በሄልሲንኪ ለመጀመሪያ ጊዜ በአደባባይ በድምቀት ተከበረ።

በአውሮፓ ማእከል ኅ/ኤ/ሚ ክፍል

መስከረም 26 ቀን 2009 ዓ.ም

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በሰሜን ምዕራብ አውሮፓ ሀገረ ስብከት የሄልሲንኪ ደብረ አሚን አቡነ ተክለ ሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን አዘጋጅነት በተካሄደው የደመራ በዓል ላይ የደብሩ አገልጋይ ካህናት ዲያቆናት፣ የሰንበት ትምህርት ቤት መዘምራን እና ምዕመናን ተገኝተዋል።  በተጨማሪም የሄልሲንኪ ደብረ ሰላም መድኃኔዓለም የኤርትራ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ካህናት እና ምእመናን፣ ከከተማው የተለያዩ መሥሪያ ቤቶች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች  እና ጋዜጠኞችም  በበዓሉ ላይ ተካፍለዋል። Read more

የደብረ መዊ ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያ ቅዳሴ ቤቱ ተከበረ

በአውሮፓ ማእከል ኅ/ኤ/ሚ ክፍል

መስከረም 9 ቀን 2009 ዓ.ም

በስዊድን ሉንድ ከተማ የደብረ መዊ ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያ በብፁዕ አቡነ ሙሴ የደ/ም/ም እና የሰሜን ምዕራብ አውሮፓ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ነሐሴ 29 ቀን 2008 ዓ.ም. ታቦተ ህጉ ተባርኮ ቅዳሴ ቤቱ ተከብሯል።

14205986_1069889456435877_5576623531079840071_o 14232022_1069885853102904_8227531442228237185_o

Read more

በጀርመን በርሊን ዐውደ ርእይ እና ስብከተ ወንጌል መርሐግብር ተካሄደ

በጀርመን ንኡስ ማእከል

ጳጕሜ 3 ቀን 2008 ..

በጀርመን ርእሰ ከተማ በበርሊን ነሐሴ እና ፳፻፰.ም “ለሁለንተናዊ የቤተክርስቲያን እድገት የድርሻችንን እንወጣ” በሚል መሪ ቃል የዐውደ ርእይ እና የስብከተ ወንጌል መርሐግብር ተካሄደ። ይህንን በማኅበረ ቅዱሳን የአውሮፓ ማእከል ከበርሊን ደብረ ገነት ቅዱስ አማኑኤል ቤተ ክርስቲያን ሰበካ ጉባኤ ጋር በመተባበር ያዘጋጁትን መርሐግብር የከፈቱት የደብሩ አስተዳዳሪ መልአከ ገነት ቆሞስ አባ ብርሃነ መስቀል ተድላ ሲሆኑ ዐውደ ርእዩን ብዙ ምእመናን ጎብኝተውታል። ዐውደ ርእዩ ፍኖተ ቤተከርስቲያን፣ ገዳማት እና የአብነት ትምህርት ቤቶች እንዲሁም ማኅበረ ቅዱሳን የሚሉ ሦስት ትዕይንቶችን ያካተተ ነበር። በተለይም የኢትዮጵያ ገዳማትና የአብነት ትምህርት ቤቶች ለእምነትና ለታሪክ መጠበቅ እና ለዕውቀት፣ ትውፊትና ባሕል ከትውልድ ወደ ትውልድ መሸጋገር ያበረከቱትና እያበረከቱት ያለው አስተዋኦ እንዲሁም አሁን ያሉበት ወቅታዊ ችግሮቻቸው በሰፊው የተገለጸ ሲሆን ችግሮቹን ለመፍታት ማኅበረ ቅዱሳን እየወሰዳቸው ያሉ በርካታ ጊዜያዊ እና ዘላቂ መፍትሔዎች በቪዲዮ በታገዘ ማብራሪያ ለጎብኚዎች ቀርበዋል። ከዐውደ ርእዩ በተጨማሪም ከማኅበረ ቅዱሳን ዋናው ማእከል የመጡት መምህር ፈቃዱ ሣህሌ ትምሀርት ሰጥተዋል። Read more

“መዝሙሮቻችን ከየት ወዴት” በሚል ርዕስ በመዝሙራት ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ መርሐ ግብር ተካሄደ

በእንግሊዝ ንዑስ ማዕከል

ነሐሴ 5 ቀን 2008 ..

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ማኅበረ ቅዱሳን አውሮፓ ማዕከል የዩኬ (እንግሊዝ) ንዑስ ማዕከልመዝሙሮቻችን ከየት ወዴት” በሚል ርእስ ሐምሌ ፳፬ ቀን ፳፻፰ ዓ.ም የኖቲንግሃምና የአቅራቢያ ከተሞች ካህናትና ምእመናን፣ የሰንበት ት/ቤት መዘምራንና የንዑስ ማእከሉ አባላት በተገኙበት በኖቲንግሃም ከተማ የግንዛቤ ማስጨበጫ መርሐ ግብር አካሄደ። Read more

በማኅበረ ቅዱሳን አዉሮፓ ማዕከል የዩኬ(እንግሊዝ) ንዑስ ማዕከል አስተባባሪነት የተዘጋጀዉ ጉባዔ ተጠናቀቀ

በእንግሊዝ ንዑስ ማዕከል

ሐምሌ 29 ቀን 2008 ዓ.ም.

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ// ቤቶች ማ/ መምሪያ ማኅበረ ቅዱሳን አዉሮፓ ማዕከል የዩኬ (እንግሊዝ) ንዑስ ማዕከል ከሁለት አጥቢያ አቢያተ ክርስቲያናት ጋር በመተባበር አዘጋጅቶት የነበረዉ የስብከተ ወንጌል ጉባዔ በተሳካ ሁኔታ ተከናውኗል። ጉባዔው ሰኔ ፳፭ እና ፳፮ ቀን ፳፻፰ ዓ.ም በበርሚንግሃም ደ/መድኃኒት ቅዱስ አማኑኤል እንዲሁም ሐምሌ ፪ እና ፫ ቀን ፳፻፰ ዓ.ም በሊድስ ደ/ ስብሐት መድኃኔ ዓለም አቢያተ ክርስቲያናት የተካሄደ ሲሆን በበርሚንግሃም፣ በሊድስ እና በአቅራቢያ ከተሞች የሚኖሩ በራካታ ምዕመናን ተካፍለዋል። Read more

የአውሮፓ ማእከል ፲፮ኛ ጠቅላላ ጉባኤ ተካሔደ

በአውሮፓ ማእከል ኅትመትና ኤሌክትሮኒክስ ሚዲያ ክፍል

ሐምሌ 15 ቀን 2008 ዓ.ም.

ገገገገገ-1-450x252

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ማኅበረ ቅዱሳን የአውሮፓ ማእከል ፲፮ኛ ጠቅላላ ጉባኤ ከሐምሌ ፩-፫ ቀን ፳፻፰ ዓ.ም በስዊድን አገር ስቶክሆልም ከተማ ተካሔደ።

በጠቅላላ ጉባኤው በተለያዩ የአውሮፓ አገሮች የሚኖሩ ከሰባ በላይ የማእከሉ አባላት፤ የዋናው ማእከልና የሰሜን አሜሪካ ማእከል ተወካዮች፤ እንደዚሁም ጥሪ የተደረገላቸው ካህናትና ምእመናን ተሳትፈዋል።

Read more

በጀርመን ድሶልዶርፍ የጻድቁ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ቤተ ክርስቲያን ቅዳሴ ቤቱ ተከበረ።

በጀርመን ን/ማእከል ኅትመትና ኤሌክትሮኒክስ ሚዲያ ክፍል

ግንቦት 24 ቀን 2008 ..

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን በደቡብ ምሥራቅ እና ምዕራብ አውሮፓ ሀገረ ስብከት በጀርመን ድሶልዶርፍ የጻድቁ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ቤተ ክርስቲያን በሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ በብፁዕ አቡነ ሙሴ ሚያዚያ 16 ቀን 2008 .. በእለተ ሆሳዕና ተባርኮ ቅዳሴ ቤቱ ተከበረ።

Read more

ሀገረ ስብከቱ የመጀመሪያውን “ዝክረ ቅዱስ ያሬድ“ መርሐግብር አካሄደ

በጀርመን ን/ማእከል ኅትመትና ኤሌክትሮኒክስ ሚዲያ ክፍል

ግንቦት 20 ቀን 2008 ..

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን በደቡብ፣ ምሥራቅ እና ምዕራብ አውሮፓ ሀገረ ስብከት የቤተ ክርስቲያናችን የዜማ አባት የሆነውን ቅዱስ ያሬድን ሕይወቱን እና ሥራዎቹን የሚዘክር “ዝክረ ቅዱስ ያሬድ“ የተሰኘ መርሐግብር በጀርመን ካርልስሩኸ ምዕራፈ ቅዱሳን አቡነ ተክለ ሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን ከግንቦት 12-14 2008 ዓ.ም. በደማቅ ስነ ሥርዓት አከበረ። በሀገረ ስብከቱ አስተባባሪነት እና በካርልስሩኸ ም/ቅ አቡነ ተክለሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን አዘጋጅነት በቀረበው መርሐግብር ላይ ከተለያዩ ሃገራት የተጋበዙ መምህራን፣ ጥናት አቅራቢዎች፣ በጀርመን እንዲሁም በፈረንሳይ ፓሪስ ያሉ የአጥቢያ ቤተ ክርስቲያን አስተዳዳሪዎች፣ ምእመናን እና መዘምራን እንዲሁም ጀርመናዉያን እንግዶች በአጠቃላይ 400 የሚደርሱ ታዳሚዎች ተገኝተዋል።

Read more

የጀርመን ንዑስ ማእከል 3ኛውን የሐዊረ ሕይወት መርሐ ግብር አካሔደ

በጀርመን ን/ማእከል ኅትመትና ኤሌክትሮኒክስ ሚዲያ ክፍል

ሚያዚያ 17 ቀን 2008 ..

germany-3-hhበማኅበረ ቅዱሳን አውሮፓ ማእከል የጀርመን ንዑስ ማእከል 3ኛውን የሐዊረ ሕይወት መርሐ ግብር በጀርመን ክሮፍልባህ ከተማ በሚገኘው ቅዱስ እንጦስ


የግብጽ ገዳም ከሚያዝያ 7- 9 ቀን 2008 ዓ.ም አካሔደ።

ሚያዝያ 7 ቀን 2008 ዓ.ም የመርሐ ግብሩ የመጀመሪያ ቀን የካርስሩህ ምእራፈ ቅዱሳን አቡነ ተክለ ሃይማኖት እና የክሮንበርግ ቅዱስ ዑራኤል ቤተ ክርስቲያን አስተዳዳሪ በሆኑት በመልአከ ስብሐት ተክሌ ሲራክ የመክፈቻ ጸሎት የተጀመረ ሲሆን፣ በጀርመን ንዑስ ማእከል ሰብሳቢ አቶ ወርቁ ዘውዴ የእንኳን ደህና መጣችሁ መልእክት ተላልፏል፡፡ በመቀተልም የወንጌል ትምህርት በዲ/ን ሄኖክ ኃይሌ ተሰጥቷል፡፡

Read more

በጀርመን የክሮንበርግ ቅዱስ ዑራኤል ቤተ ክርስቲያን ቅዳሴ ቤቱ ተከበረ።

በጀርመን ንዑስ ማእከል

የካቲት 13 ቀን 2008 ዓ.ም.

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን በደቡብ፣ ምሥራቅ እና ምዕራብ አውሮፓ ሀገረ ስብከት የክሮንበርግ(ጀርመን) ቅዱስ ዑራኤል ቤተ ክርስቲያን በሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ በብፁዕ አቡነ ሙሴ የካቲት 6 ቀን 2008 ዓ.ም. ተባርኮ ቅዳሴ ቤቱ ተከብሯል። የቤተክርስቲያኑ መመሥረት በፍራንክፈርትና አካባቢው ከተወሰኑ ዓመታት ወዲህ በዓታ ለማርያም የፅዋ ማኅበርን በማቋቋም ተሰባሰበው ይገለገሉ በነበሩ ምዕመናን ጥረት የተጀመረ መንፈሳዊ እንቅስቃሴ ውጤት መሆኑ በዕለቱ ተገልጸል።

pic2

ይህ ለፍራንክፉርት ከተማ አቅራቢያ በምትገኘው በክሮንበርግ ከተማ የተተከለው ቅዱስ ዑራኤል ቤተ ክርስቲያን በጀርመን አገልግሎት በመስጠት ላይ የሚገኙ በኢ//// አብያተ ክርስቲያናት ቁጥር አሥራ ሦስት አድርሶታል።

Read more