ዜና

በሀገረ ጀርመን በርሊን ከተማ የቅዱስ አማኑኤል ቤተ ክርስቲያን ቅዳሴ ቤት ተከበረ

ግንቦት 26 ቀን 2007 ዓ.ም.

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የደቡብ፣ምስራቅና ምዕራብ አውሮፓ ሀገረ ስብከት የበርሊን ቅዱስ አማኑኤል ቤተ ክርስቲያን የተገዛው ሕንፃ ቤተ ክርስቲያን ቅዳሴ ቤት ግንቦት 23 ቀን 2007 ዓ.ም ተከበረ፡፡

berlin-church-1

Read more

በጀርመን ሙኒክ ዐውደ ርእይ ተካሔደ

በጀርመን ማእክል

ግንቦት 20 ቀን 2007 ዓ.ም.

በማኅበረ ቅዱሳን የአውሮፓ ማእከል ግንቦት ፲፭ እና ፲፮ ፳፻፯ ዓ.ም. በጀርመን ሙኒክ ደብረ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን ”ለሁለንተናዊ የቤተክርስቲያን እድገት የድርሻችንን እንወጣ” በሚል ርዕስ የዐውደ ርእይ እና የስብከተ ወንጌል መርሐ ግብር አካሄደ::

munich-exh-1

Read more

፲፭ ኛው የአውሮፓ ማዕከል ጠቅላላ ጉባዔ ሊካሄድ ነው

ግንቦት 19 ቀን 2007 ዓ.ም.

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስትያን ሰ/ት/ቤቶች ማ/መምሪያ ማኅበረ ቅዱሳን የአውሮፓ ማዕከል ፲፭ኛ ጠቅላላ ጉባዔውን በጀርመን ሀገር ፍራንክፈርት ከተማ ሊያካሂድ ነው። ከሰኔ ፳፮ እስከ ፳፰ ቀን ፳፻፯ዓ.ም. በሚቆየው በዚህ ጉባዔ፦

  • የደቡብ ፣ የደቡብ ምሥራቅ እና የደቡብ ምዕራብ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ሙሴ እና የሀገረ ስብከቱ ዋና ጸሐፊ
  • የሰሜን ምዕራብ ሀገረ ስብከት ተወካይ
  • በጀርመን የሚገኙ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን እና አባቶች
  • በተለያዩ የአውሮፓ ሃገራት የሚኖሩ የማኅበረ ቅዱሳን አባላት እንዲሁም ሌሎች ተጋባዥ እንግዶች እንደሚሳተፉበት ይጠበቃል።

Read more

ብፁዕ አቡነ ሙሴ የትንሣኤን በዓል አስከመልክቶ የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት አስተላለፉ

ሚያዚያ 04 ቀን 2007 ዓ.ም.

የደቡብ፣ ደቡብ ምሥራቅ እና ደቡብ ምዕራብ አውሮፓ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ሙሴ የትንሣኤን በዓል አስከመልክቶ የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት አስተላልፈዋል። ብፁዕነታቸው ያስተላለፉትን መልእክት ከዚህ በታች ይመልከቱ።

ወስብሐት ለእግዚአብሔር።

 

በጀርመን ሀገር 2ኛው የሐዊረ ሕይወት ጉዞ ተካሄደ

በአውሮፓ ማዕከል መገናኛ ብዙኀን እና ቴክኖሎጂ አገልግሎት ክፍል

መጋቢት 16 ቀን 2007 ዓ.ም.

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ማኀበረ ቅዱሳን በአውሮፓ ማዕከል የጀርመን ቀጣና ማዕከል አዘጋጅነት የሐዊረ ሕይወት (የሕይዎት ጉዞ) መርሐ ግብር ከመጋቢት 11 እስከ 13 /2007ዓ.ም በክሩፈልባክህ (Kroeffelbach) ከተማ በሚገኘው በቅዱስ እንጦንስ የግብፅ ገዳም (Sankt-Antonius Kloster) ለሁለተኛ ጊዜ ተካሄደ። በመርሐ ግብሩ ላይ ከተለያዩ የጀርመን ከተሞች የመጡ ከ200 በላይ ምዕመናን ተሳትፈውበታል::

fft st Antonie monastry

የጉባኤው ተሳታፊዎች አርብ ምሽት 1 ሰዓት ተኩል ላይ ከፍርንክፈረት 64.5 ኪ.ሜ ላይ እርቀት በሚገኘው የቅዱስ እንጦንስ የግብፅ ገዳም የተገኙ ሲሆን፤ የገዳሙ አባቶችም የመጣውን እንግዳ በትህትና በመቀበልና ለሁሉም የማረፊያ ቦታ ሰጥተዋል።

Read more

የአውሮፓ ማዕከል ሥራ አስፈጻሚ የገጽ ለገጽ ስብሰባውን አካሄደ።

መጋቢት 10 ቀን 2007 ዓ.ም.

በኢ.ኦ.ተ.ቤ.ክ. ማኅበረ ቅዱሳን የአውሮፓ ማዕከል ሥራ አስፈጻሚ ጉባኤ የ፳፻፯ ዓ.ም. የመጀመሪያውን የገጽ ለገጽ ስብሰባ በዴንማርክ ሀገር በኮፐንሀገን ከተማ በቅዱስ ማርቆስ የግብጽ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ከመጋቢት ፬-፮ ቀን ፳፻፯ ዓ.ም. አካሄደ።

የሥራ አስፈጻሚ አባላቱ አርብ መጋቢት ፬ ቀን ፳፻፯ ዓ.ም. ኮፐንሀገን ከተማ የተገኙ ሲሆን፣ ምሽቱን ከዴንማርክ ግንኙነት ጣቢያ አባላት ጋር የጋራ የጸሎት መርሐ ግብር በማድረግ ስብሰባውን ጀምረዋል። ከጸሎቱ በመቀጠል በዴንማርክ የደብረ ምሕረት ቅዱስ አማኑኤል ቤተ ክርስቲያን አስተዳዳሪ የሆኑት መልአከ ምሕረት ቆሞስ አባ ዘሚካኤል ደሬሳ እንኳን ደህና መጣችሁ በማለት አጭር ቃለ ወንጌልና ምክር ሰጥተዋል። በመቀጠልም የማዕከሉ ሰብሳቢ ዲ/ን ሰሎሞን አስረስ የስብሰባውን አላማ ሲገልጹ ሥራ አስፈጻሚ አባላቱ በተለያዩ ሀገራት ሆነው በስካይፕና በስልክ ከሚያደርጉት ስብሰባ በተጨማሪ አባላቱ በአካል ተገናኝተው የበለጠ ተግባብተውና ተቀራርበው አገልግሎቱን ለማፋጠን እና የማእከሉን ያለፉት ስድስት ወራት አፈጻጸም ለመገምገም እና ቀጣይ አቅጣጫዎችን ለማመላከት ይረዳል በሚል ታሳቢነት መሆኑን ገልጸዋል።

Read more

ሀገረ ስብከቱ የመጀመርያውን ሥልጠና ሰጠ

በጀርመን ቀጣና ማዕከል

መጋቢት 4 ቀን 2007 ዓ.ም.

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የደቡብ፣ ደቡብ ምሥራቅና ደቡብ ምዕራብ አውሮፓ ሀገረ ስብከት በአይነቱ ልዩ የሆነ እና የሰበካ ጉባዔ አባላትን አቅም ለማሳደግ የታለመ ሥልጠና በሀገረ ጀርመን በፍራንክፈርት ዙርያ የሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ መቀመጫ በሆነው በሩሰልስሀይም ከተማ የካቲት ፳፰ ቀን ፳፻፯ዓ.ም ሰጠ::

dicesec training2ሥልጠና መርሐግብሩን በጸሎትና በቡራኬ የከፈቱት ብፁዕ አቡኑ ሙሴ የሀገረ ስብከቱ ሊቀጳጳስ ሲሆኑ የስልጠናውን ወቅታዊነት እና አስፈላጊነት አበክረው ተናግረዋል:: በመቀጠልም የሀገረ ስብከቱ ጸሐፊና የስልጠናው ዋና አስተባባሪ የሆኑት መጋቤ ምሥጢር ኅሩይ ኤርሚያስ የእለቱን መርሐግብር በዝርዝር በማስተዋወቅ እና ጥሪውን አክብረው የመጡ ሰልጣኞችን በማመስገን ስልጠናውን አስጀምረዋል::

Read more

የጥምቀት በዓል በለንደን እና በሊቨርፑል ከተሞች በአንድነት ይከበራል

በዩኬ ቀጠና ማዕከል

ጥር 5 ቀን 2007 ዓ.ም.

የ፪፻፯ ዓ.ም የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ የጥምቀት በዓል በታላቋ ብሪታኒያ በለንደን እና በሊቨርፑል ከተሞች በህብረት ይከበራል። በዓሉ በሰሜን ምዕራብ አውሮፓ ሀገረ ስብከት አዘጋጅነት ጥር ፲ እና ፲፩ ቀን ፪፻፯ ዓ.ም በለንደን ደብረ ጽዮን ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን እንዲሁም ጥር ፲፭ እና ፲፮ ቀን ፪፻፯ ዓ.ም በሰሜን ምዕራብ አውሮፓ ሀገረ ስብከት የለንደን ውጭ ወረዳ ቤተ ክህነት አዘጋጅነት በታላቁ የሊቨርፑል ካቴድራል በደማቅ ሥነ ሥርዓት ይከበራል።

Read more

ብፁዕ አቡነ እንጦንስ የልደትን በዓል አስከመልክቶ የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት አስተላለፉ

ታህሣስ 28 ቀን 2007 ዓ.ም.

የሰሜን ምዕራብ አውሮፓ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ እንጦንስ የልደትን በዓል አስከመልክቶ የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት አስተላልፈዋል። ብፁዕነታቸው ያስተላለፉትን መልእክት ከዚህ በታች ይመልከቱ።

ወስብሐት ለእግዚአብሔር።

ሐዊረ ሕይወት (የሕይወት ጉዞ) በሀገረ ጀርመን

ታህሣስ 26 ቀን 2007 ዓ.ም.

በኢ.ኦ.ተ.ቤ.ክ.ሰ.ማ.መ.ማኅበረ ቅዱሳን የጀርመን ቀጠና ማዕከል ሁለተኛውን የሐዊረ ሕይዎት ጉዞ ከመጋቢት 11 – 13 ቀን 2007 ዓ.ም. ወደ ጀርመን ሀገር የሚገኘው ግብጽ ቅዱስ እንጦንስ ገዳም እንደሚያካሂድ አስታወቀ። በዚህ መርሐ ግብር ላይ በሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን ትምህርተ ወንጌል እንዲሁም ከምዕመናን ለሚነሱ ጥያቄዎች መልስ ይሰጥበታል። በጉዞው ላይ ከተለያዩ የአውሮፓ ሀገራት የሚመጡ ምዕመና እንደሚሳተፉ ይጠበቃል። ቀጠና ማዕከሉ ለህዝበ ክርስቲያኑ በጉዞው ላይ በመሳተፍ ቃለ እግዚአብሔርን እንዲመገቡና በስደተኞች መጠለያ ጣቢያ ለሚገኙ ወንድሞች እና እህቶች የሚደረገውን የምክርና የስብከተ ወንጌል አገልግሎት እንዲደግፉ ጥሪውን አስተላልፏል።

Read more