ዜና

ክፍት የሥራ ማስታወቂያ

በማኅበረ ቅዱሳን የአውሮፓ ማእከል ጽ/ቤት

ታህሳስ 3 ቀን 2008 .

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምርያ ማኅበረ ቅዱሳን የአውሮፓ ማእከል እየሰጠ ያለውን አገልግሎት አጠናክሮ መስጠት ያስችለው ዘንድ በመደበኛነት የሚያገለግል የጽ/ቤት ረዳት ሆኖ እገዛ የሚሰጥ አገልጋይ ይፈልጋል፡፡

Read more

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የደቡብ ምሥራቅና ምዕራብ አውሮፓ ሀገረ ስብከት”የግብጽ እና የኢትዮጵያ ሲኖዶስ ተቋቋመ” ተብሎ እየተናፈሰ ስላለው አሉባልታ መግለጫ ሰጠ።

ገረስብከቱ በቅርቡ የተሳካ ዓመታዊ ስብሰባ፣ የትምህርተ ወንጌልና የዐውደ ጥናት ጉባኤ አካሂዷል።

በጀርመን ንዑስ ማእከል

መስከረም 11 ቀን 2008 ዓ.ም

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የደቡብ ምሥራቅና ምዕራብ አውሮፓ ሀገረ ስብከት ሰሞኑን “በጀርመን የሆክስተር ከተማ ነሐሴ 14 ቀን 2007 ዓ.ም የግብጽ እና የኢትዮጵያ ሲኖዶስ ተቋቋመ” ተብሎ እየተናፈሰ ነው ስላለው አሉባልታ መግለጫ አወጣ:: ሀገረ ስብከቱ መግለጫውን ያወጣው የሐሰት መረጃው ለጥቂት ግለሰዎች በኢሜይል እና ዓለሙ አምላኩ በተባለ የብዕር ስም ጎልጉል በተባለ ድረ ገጽ ላይ እየተሰራጨ መገኘቱን ምክንያት በማድረግ እንደሆነ ጠቅሶ በተለይም ሀሰተኛው ወሬ በማጠቃለያው “ሦስተኛ ሲኖዶስ ተቋቋመ፤ ዳግመኛ የግብጽ ተገዢዎች ልንሆን ነው፤ ሊቀ ጳጳሱ የአጥቢያ አስተዳዳሪዎችን በተለይም 30 ዓመት ያስተዳደሩትን ሊቀ ካህናት ሳያማክሩ ቤተ ክርስቲያኒቱን ችግር ውስጥ ከተቷት፤ የመንግሥት እጅ አለበት ወዘተ..” የሚል ከእውነት የራቀ አሉባልታ ዘገባ እንደተደረገ ሀገረ ስብከቱ ደረሶበት እንደሆነ ይገልጻል።

Read more

ሀገረ ስብከቱ የመጀመሪያውን ልዩ የትምህርተ ወንጌል ጉባኤና ዐውደ ጥናት እንደሚያካሂድ አሳወቀ፡፡

በወርቁ ዘውዴ

ነሐሴ 19 ቀን 2007 ዓ.ም.

በኢ/ኦ/ተ/ቤተ ክርስቲያን የደቡብ፣ ምሥራቅና ምዕራብ አውሮፓ ሀገረ ስብከት ከነሐሴ ፴ እስከ ጷጉሜን ፩ ቀን ፳፻፯ ዓ.ም. የሀገረ ስብከቱ ጽ/ቤት በሚገኝበት በጀርመኗ ሮሰልሳይም ከተማ የትምህርተ ወንጌል ጉባኤ እና ዐውደ ጥናት ለማካሄድ ዝግጅቱን ማጠናቀቁን አሳወቀ፡፡ ሀገረ ስብከቱ በአዲስ መልኩ ተዋቅሮ የመንበረ ጵጵስና መቀመጫውን በጀርመን ካደረገበት ጊዜ አንስቶ አስተዳደራዊ መዋቅሩን በማጠናከር የቤተ ክርስቲያኗን መንፈሳዊ አገልግሎት የሚደግፍና የሚያግዝ ጠቃሚ ተግባራትን በማከናወን ላይ እንደሚገኝ ከሀገረ ስብከቱ ጽ/ቤት የተገኘው መረጃ ያስረዳል፡፡

Read more

በፓርማ አውደ ርእይ ተካሄደ

በጣሊያን ንዑስ ማእከል

ሐምሌ 26 ቀን 2007 ዓ.ም.

የፓርማ ቤዛ ብዙኃን ቅድስት ኪዳነ ምህረት ቤተክርስቲያን ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ ከማኅበረ ቅዱሳን የአውሮፓ ማእከል ጋር በመተባበር ያዘጋጀው አውደ ርእይ በጣሊያን ፓርማ ከተማ ተካሄደ።parma-1

Read more

በዴንማርክ ዐውደ ርእይ ተካሄደ

በዴንማርክ ግኑኝነት ጣቢያ

ሐምሌ 10 ቀን 2007 ዓ.ም.

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ሰ/ት/ቤቶች ማ/መምሪያ ማኅበረ ቅዱሳን አውሮፓ ማዕከል የዴንማርክ ግንኙነት ጣቢያ ከዴንማርክ የደብረ ምሕረት ቅዱስ አማኑኤል ቤተክርስቲያን ሰበካ ጉባኤ ጋር በመተባበር በኮፐንሃገን ከተማ ዐውደ ርእይ አካሄደ። ዐውደ ርእዩ በመልአከ ምሕረት ቆሞስ አባ ዘሚካኤል ጸሎት እና የመግቢያ ንግግር እንዲሁም ለአውሮፓ ማዕከል ፲፭ኛ ጠቅላላ ጉባኤ ከዋናው ማዕከል ተወክለው በመጡት በአቶ ፋንታሁን ዋቄ ለሕዝቡ ክፍት ሆኗል። ዐውደ ርእዩ የተካሄደው ሐምሌ ፫ እና ፬ ፳፻፯ ዓ.ም. ሲሆን በሁለቱ ቀን መርሐ ግብር ከመቶ ሰው በላይ ተገኝቷል።dk exhibition 1

Read more

የአውሮፓ ማዕከል ፲፭ኛ ጠቅላላ ጉባኤውን በፍራንክፈርት ፥ ጀርመን አካሄደ

በብዙኀን መገናኛ እና ቴክኖሎጂ አገልግሎት ክፍል

ሐምሌ 02 ቀን 2007 ዓ.ም.

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የሰንበት ት/ቤቶች ማደረጃ መምሪያ ማኅበረ ቅዱሳን የአውሮፓ ማዕከል አስራ አምስተኛ ጠቅላላ ጉባኤውን በጀርመን ሀገር በፍራንክፈርት ከተማ በምትገኘው በደብረ ፀሐይ ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን ከሰኔ ፳፮ እስከ ፰ ቀን ፳፻፯ ዓ.ም. አካሄደ።

GA 15 1

Read more

ጉባኤያቱ እንደቀጠሉ ናቸው።


በብዙኀን መገናኛ እና ቴክኖሎጅ አገልግሎት ክፍል

ሰኔ 23 ቀን 2007 ዓ.ም.

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በሰ//ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ማኅበረ ቅዱሳን የአውሮፓ ማእከል በተለያዩ የአውሮፓ ሀገራት ካሉ አብያተ ክርስቲያናት ጋር በመተባበር «ለሁለንተናዊ የቤተክርስቲያን እድገት የድርሻችንን እንወጣ» በሚል መሪ ቃል እያካሄደ ያለው ጉባኤ እንደቀጠለ ነው። ከማዕከሉ ያገኘው መረጃ እንደሚያመለክተው በሰኔ ፮ ቀን ፳፻፯ ዓ.. ለመጀመሪያ ጊዜ በስዊዘርላድ ሀገር በርን ከተማ ከጽርሐ አርያም ቅድስት ሥላሴ ወአቡነ ተክለ ሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን ጋር በመተባበር፤ እንዲሁም ከሰኔ ፲፫ – ፲፬ ቀን ፪፲፻፯ ዓ.ም በግሪክ የአቴና ምክሐ ደናግል ቅድስት ኪዳነ ምሕረት ቤተክርስቲያን ጋር በመተባበር ጉባኤያትን አካሂዷል።

በጉባኤያቱ ላይ «ፍኖተ ቤተክርስቲያን፣ ገዳማት እና የአብነት ትምህርት ቤቶች እንዲሁም ማኅበረ ቅዱሳን» በሚሉ ሶስት ትእይንቶች የተከፋፈለ ዐውደ ርዕይ ተካሂዷል። እንዲሁም ከማኅበረ ቅዱሳን ዋናው ማዕከል በመጡት ልዑካን ሰፊ ወንጌል ትምህር የተሰጠ ሲሆን ለገዳማት እና አብነት ትምህርት ቤቶች ድጋፍም የገንዘብ ማሰባሰቢያ መርሐ ግብር ተከናውኗል።

በስዊዘርላንድ በተካሄደው ጉባኤ ላይ ከ፹ በላይ ምዕመናን እና ካህናት የተሳትፉበት ሲሆን በግሪክ ከ፫፻፶ በላይ ምዕመናን በጉባኤው እንደተሳተፉ ለመረዳት ችለናል።

በአቴና ከተማ የተካሄደውን ጉባኤ ኪዳን ጸሎት አድርሰው ባርከው የከፈቱት ቀሲስ ዶ/ር አየለ ወ/ጻድቅ፣ ቀሲስ ሰሎሞን ገ/መድህን እና መሪጌታ ዶ/ር መርዓዊ መለሰ ምዕመናን ለቤተ ክርስቲያናቸው አገልግሎት እንዲተጉ ምክራቸውን አስተላልፈዋል።

በስዊዘርላንድ የተካሄደውን ጉባኤ በጸሎት ባርከው የጀመሩት በስዊዘርላንድ የኢ///ቤተ ክርስቲያን አስተዳዳሪ የሆኑት መልአከ ገነት ቆሞስ አባ ኃይለ ጊዮርጊስ ባስተላለፉት ቃለ ምዕዳን ይህ መርሐግብር አንዲሳካ ድጋፍ ያደረጉትን ሁሉ አመስግነው ምዕመናንም ገዳማትን ለመርዳት የሚያደርጉትን ጥረት አጠናክረው አንዲቀጥሉ አሳስበዋል።

ማእከሉ ሁሉም ጉባኤ በተሳካ ሁኔታ እንዲካሄዱ አስተዋጽኦ ላደረጉት በስዊዘርላንድ የጽርሐ አርያም ቅድስት ሥላሴ ወአቡነ ተክለ ሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን እና በግሪክ የአቴና ምክሐ ደናግል ቅድስት ኪዳነ ምሕረት ቤተክርስቲያን ሰባካ አስተዳደር ጉባኤዎች እንዲሁም በጉባኤው ላይ በመገኘት ድጋፋቸውን ላደረጉ ምዕመናን ሁሉ ምስናጋውን ያቀርባል።

በጀርመን ሀምቡርግ ከተማ ዐውደ ርእይ ተካሄደ

በጀርመን ቀጣና ማእከል

ሰኔ 3 ቀን 2007 ዓ.ም.

በጀርመን ሀገር በሀምቡርግ ከተማ ግንቦት ፳፱ እና ፴ ፳፻፯ ዓ.ም. ”ለሁለንተናዊ የቤተክርስቲያን እድገት የድርሻችንን እንወጣ” በሚል መሪ ቃል የዐውደ ርእይ እና የስብከተ ወንጌል መርሐግብር ተካሄደ። ዐውደ ርእዩን በማኅበረ ቅዱሳን የአውሮፓ ማእከል ከሀምቡርግ ደብረ መድኃኒት ቅድስት ኪዳነ ምሕረት ቤተ ክርስቲያን ሰበካ ጉባኤ ጋር በመተባበር ያዘጋጀው ሲሆን መርሐግብሩን የከፈቱት የደብሩ አስተዳዳሪ መልአከ ገነት ቆሞስ አባ ብርሃነ መስቀል ተድላ ናቸው።

Hamburg-2

 

Read more

ማኅበሩ ስብከተ ወንጌል በአውሮፓ ሊያካሂድ ነው

ግንቦት 30 ቀን 2007 ዓ.ም.

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ሰ/ት/ቤቶች ማ/መምሪያ ማኅበረ ቅዱሳን የአውሮፓ ማዕከል ትምህርትና ሐዋርያዊ አገልግሎት ክፍል በየዓመቱ በምዕራባውያኑ የበጋ ወቅት የሚያካሂደውን የስብከተ ወንጌል አገልግሎት በቅርቡ እንደሚጀምር አስታወቀ።

Read more

በፓሪስ የደ/ም/ቅ/ማርያም ቤተክርስቲያን የምሥረታ በዓል ብጹዕ አቡነ ዮሴፍ በተገኙበት ተከበረ

በፈረንሳይ ግንኙነት ጣቢያ

ግንቦት 27 ቀን 2007 ዓ.ም.

በፈረንሳይ ሀገር የመጀመሪያ የሆነችው በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ የደ/ም/ቅ/ማርያም ቤ/ክ ፲ኛ ዓመት የምሥረታ ክብረ በዓል እና የንግሥ በዓል ከግንቦት ፳፩ እስከ ፳፫ ቀን ፳፻፯ ዓ.ም. በድምቀት ተከበረ። በመጀመሪያ ጥቂት ምእመናን በእመቤታችን በቅድስት ማርያም ሥም በጽዋ ማኀበር ተሰባስበው ለብዙ ዓመታት ከቆዩ በኋላ በ፲፱፻፺፯ ዓ.ም. ግንቦት ወር በወቅቱ የአውሮፓ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በነበሩት አቡነ ዮሴፍ መልካም ፍቃድ ደብረ ምጥማቅ ቅድስት ማርያም በመባል ቤተክርስቲያኗ ተመሠረተች፡፡

paris-10-1

Read more