Entries by Website Team

ሠለስቱ ደቂቅ

እንደምን ሰነበታችሁ ልጆች?ደህና ናችሁ ልጆች? ዛሬ ስለ ሦስቱ ልጆች ታሪክ እንነግራችኋለን በደንብ ተከታተሉን እሺ፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚነግረን፣ በድሮ ጊዜ እግዚአብሔርን የማይፈራ ናቡከደነፆር የሚባል የባቢሎን ንጉሥ ነበር፡፡ይህም ንጉሥ ከወርቅ የተሰራ ትልቅ ጣኦት አቁሞ ሕዝቡንም ሁሉ ሰበሰበና ለጣኦቱ እንዲሰግዱ አዘዘ፡፡ ለጣኦት ያልሰገደ ግን በእሳት ውስጥ ይጣላል ብሎ አዋጅ አስነገረ፡፡

የምእመናን ድርሻ በቤተ ክርስቲያን

መግቢያ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ በተለያየ ጊዜ ካህናት እና ምእመናን የእግዚአብሔር ማደሪያ ቤት በተባለች ቅድስት ቤተ ክርስቲያን እንዴት ሊኖሩ እንደሚገባ ድርሻቸውም ምን እንደሆነ ያስተምራቸው ነበር:: ለምሳሌ የመንፈስ ልጁ የሆነ ቅዱስ ጢሞቴዎስን በእግዚአብሔር ማደሪያ ቤት ሲኖር ምን ማድረግ እንዳለበት እንዲህ በማለት መክሮታል:-“በእግዚአብሔር ማደሪያ ቤት መኖር እንዴት እንደሚገባ ታውቅ ዘንድ እጽፍልሃለሁ፤ ቤቱም የእውነት ዐምድና መሠረት የሕያው እግዚአብሔር ቤተ […]

ማኅበረ ቅዱሳን ማን ነው?

ማኅበረ ቅዱሳን ማን ነው? ምንስ እየሠራ ነው?   የተዛባ አመለካከት የማይጋርደው ገሐድ እውነታ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ሊቃውንት ብራና ዳምጠው፤ ቀለም በጥብጠው፣ ብዕር ቀርጸው በየአብያተ ክርስቲያናቱ የመቃብር ቤቶች ውስጥ በማስተማር ትውልዱ የሀገር መሪ፣ የቤተክርስቲያን አለኝታ፣ የእግዚአብሔር ቅን አገልጋይ እንዲሆን ያበረከቱት አገልግሎት ከዘመን ዘመን እየተሸጋገረ ለትውልድ ሲተላለፍ የኖረና የሚኖር ነው፡፡ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ለሀገራችን ሥልጣኔ […]

የጌታችን ትንሣኤ

ልጆች ስለ ጌታ ከሞት መነሣት ሰምታችሁ ታውቃላችሁ? እስቲ ትንሽ ስለ ትንሣኤው ልንገራችሁ:: ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን አይሁድ ዓርብ ቀን በሐሰት ሰቅለው ከገደሉት በኋላ ዮሴፍና ኒቆዲሞስ ሥጋውን ከመስቀል ላይ አውርደው በንጹህ በፍታ ገንዘው በአትክልት ቦታ በሚገኝ አዲስ መቃብር ውስጥ ቀበሩት። ትልቅ ድንጋይም አንከባለው የመቃብሩን አፍ ዘጉት። በአይሁድ የታዘዙ ብዙ ጭፍሮች (ወታደሮች) የጌታችንን መቃብር ይጠብቁ ነበር። ልጆች፣ […]

ኢትዮጵያዊዉ ጃንደረባ

በዓለም የክርስትና ታሪክ የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ቀዳሚውን ስፍራ የያዘችና ሐዋርያዊት ለመሆንዋ ምስክር ከሚሆኑ ታላላቅ የቤተ ክርስቲያን አባቶች መካከል ባኮስ ቀዳማዊ ነው። ኢትዮጵያውያን ከዘመነ ብሉይ ጀምሮ ሕዝበ እግዚአብሔር ከሚባሉ እስራኤል ጋር በአምልኮተ እግዚአብሔር የሚኖሩ ሕዝብ ስለመሆናቸው ቅዱስ መጽሐፍ ይመሰክራል። አያሌ የታሪክ መዛግብትና የአርኪዮሎጂ ምርምር ውጤቶችም ይህንን እውነት ያረጋግጣሉ። እኛም በዚህ የቅዱሳን ታሪክ ዓምድ፣ ጌታችን አምላካችንና መድኃኒታችን […]

ዕውቀት እንዳይሞት

ቤተ ክርስቲያን ሰማይና ምድር ከመፈጠራቸው በፊት ነበረች። ዓለማት ከተፈጠሩ በኋላ በዓለመ መላእክት፣ በዓለመ መሬት በሕገ ልቡና እና በሕገ ኦሪት እግዚአብሔር በመረጣቸው ነቢያትና ካህናቱ አማካኝነት ሰዎችን ከእግዚአብሔር ጋር ስታገናኝ ኖራለች። በዘመነ ሐዲስ ደግሞ በደመ ክርስቶስ ተዋጅታ ሕገ ወንጌልን ስትናኝ እና አምልኮተ እግዚአብሔርን ስታስፋፋ ኖራለች። በነዚህ አዝማናት ሁሉ ስለ እርሷ ሳይፈሩና ሳያፍሩ አንገታቸውን ለሰይፍ፣ ጀርባቸውን ለግርፋት፣ እግራቸውን […]

ሕይወት በባዕድ ምድር (፪ጴጥ. ፪፥፰)

የርዕሳችን መነሻ የሆነው በ፪ኛ ጴጥሮስ ምዕራፍ ፪ ላይ የምናገኘው ታሪክ ነው። “ጻድቅ ሎጥም እያየና እየሰማ፣ አብሮአቸውም እየኖረ በክፉ ሥራቸው ዕለት ዕለት ጻድቅት ነፍሱን ያስጨንቃት ነበር።” ፪ጴጥ. ፪፥፰ ሎጥ ኃጢአትን የዕለት ከዕለት ተግባራቸው ካደረጉ ሰዎች ጋር ለመኖር የተገደደው በዘፍ ፲፫ ላይ እንደምናነበው ከአጎቱ ከአብርሃም ጋር ይኖርበት የነበረው ቦታ ስለጠበባቸው በእረኞቻቸው መካከልም እየተፈጠረ የነበረው ጥላቻ ወደ እነርሱ […]

የአውሮፓ ማዕከል በአጭሩ ሲቃኝ

ማኅበረ ቅዱሳን እግዚአብሔር ያከበራቸዉ የነቢያት፣ የሐዋርያት፣ የጻድቃን፣ የሰማዕታት፣ በአጠቃላይ የቅዱሳን ገድል፣ ትሩፋትና አማላጅነት የሚዘከርበት ማኅበር ነው። በ1977 ዓ.ም. በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ሲማሩ የነበሩ ጥቂት የቤተ ክርስቲያን ወጣቶች በጽዋ ማኅበር ስም በመሰባሰብ ትምህርተ ሃይማኖትን መማማር ጀመሩ። ይህ እንቅስቃሴ በየዓመቱ የክረምት ወራት በዝዋይ ሐመረ ብርሃን ቅዱስ ገብርኤል ገዳም ካህናት ማሰልጠኛ ይሰጥ በነበረው ስልጠና ተጠናክሮ ቀጠለ። ከዚያም በ1983 […]