Author Archive for: webteam
About Website Team
This author has yet to write their bio.
Meanwhile lets just say that we are proud Website Team contributed a whooping 188 entries.
Entries by Website Team
“እውነት እውነት እልሀለሁ ሰው ከውሃና ከመንፈስ ካልተወለደ በቀር ወደ እግዚአብሔር መንግሥት ሊገባ አይችልም።” ዮሐ ፫፡፭
ጃንዩወሪ 17, 2013 in ክርስቲያናዊ ሕይወት /by Website Teamበይበልጣል ጋሹ ጥር ፲ ቀን ፳፻፭ ዓ.ም. ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመዋዕለ ስጋዌው በምድር በነበረበት ዘመን ከፈጸማቸው እና ለሰው ልጅ ከሰጣቸው ሚስጢራት አንዱ ጥምቀት ነው። “ጥምቀት” የሚለው ቃል አጥመቀ ከሚለው የግዕዝ ግሥ የተገኘ ሲሆን ትርጉሙም፣ መነከር፣ መዘፈቅ፣ መደፈቅ፣ መላ አካልን በውሃ ውስጥ ማስገባት ማለት ነዉ። በሚስጢራዊ ትርጉም ደግሞ ብዙ ምሳሌዎች አሉት። ከምሳሌዎች መካከልም፦ የአብርሃም ከሃገሩ […]
ሕፃን ተወልደ ለነ ወልድ ተውኅበ ለነ፤ ሕፃን ተወለደልን ወንድ ልጅም ተሰጠን፡፡ ኢሳ 9፣6 (ውዳሴ ማርያም ዘሰኑይ)
ጃንዩወሪ 6, 2013 in ክርስቲያናዊ ሕይወት /by Website Teamዲ/ን ውብዓለም ደስታ ታኅሣስ ፳፰ ቀን ፳፻፭ ዓ.ም. አዳም ትእዛዘ እግዚአብሔርን ተላልፎ አትብላ የተበለውን ዕፀ በለስ በልቶ በሞተ ሥጋ ሞተ ነፍስ፤ በርደተ መቃብር ርደተ ገሃነም ተፈርዶበት ከገነት ከወጣ በኋላ፤ እግዚአብሔርን ያህል ጌታ፤ ገነትን ታህል ቦታ አጥቼ ቀረሁን እያለ ሲያዝን፤ ጌታ ኀዘኑን አይቶ ልመናውን ሰምቶ ‹‹በኀሙስ እለት ወበመንፈቃ ለእለት እትወለድ እምወለተ ወለትከ፣ ወእትቤዘወከ በመስቀልየ ወበሞትየ፤በአምስት ቀን […]
ቅድስት ወለተ ጴጥሮስ
ዲሴምበር 22, 2012 in ቅዱሳን በኢትዮጵያ /by Website Teamአባቷ ባሕር አሰግድ እናቷ ደግሞ ክርስቶስ አዕበያ ይባላሉ። ትውልዷ ከዳሮ /ምስራቅ ኢትዮጵያ/ ወገን ነው። ወንድሞቿ ዮሐንስና ዘድንግል በንጉሥ ሱስንዮስ ጊዜ ታላላቅ ባለስልጣናት ነበሩ። እናት አባቷ በህግ በስርዓት ካሳደጓት በኋላ ሥዕለ ክርስቶስ የሚባል የስስኑዮስ የጦር አበጋዝ ቢትወደድ አግብታ 3 ልጆች መውለድዋን ገድሏ ይናገራል። ይህ ቢትወደድ ይኖርበት የነበረው ግንብ ቤት ፍራሽ እስከ አሁን ድረስ በጋይንት ስማዳ ይታያል።
በስውር የሚያይ አባትህም በግልጥ ይከፍልሃል (ማቴ. 6፣4).
ዲሴምበር 4, 2012 in ክርስቲያናዊ ሕይወት /by Website Teamበዲ.ን ኃይሉ ተረፈ ኅዳር 26 ቀን 2005 ዓ.ም. ለስም አጠራሩ ክብር ምስጋና ይግባዉና ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በኅቡዕ በምንፈጽማቸዉ ሥራዎች ሁሉ እዉነተኞች ተጠቃሚዎች እንድንሆን ሥራዎቻችን ሁሉ በእርሱ ዘንድ ሚዛን የሚደፉና የሚታዩ እንዲሆኑ “በስውር የሚያይ አባትህም በግልጥ ይከፍልሃል” (ማቴ. 6፣4) በማለት ይመክረናል፡፡ እግዚአብሔር ሰዎች ያላዩትን ሁሉ የሚያይ፣ በሰዎች ዘንድ ዋጋ ያልተሰጠዉን እርሱ ግን ዋጋ የሚሰጠዉ፣ ለሁሉም […]
የግቢ ጉባኤያት በእንግሊዝ ፡ ምዝገባ ጀምረናል!
ኖቬምበር 19, 2012 in ዜና /by Website Team«የግቢ ጉባኤ» ምንድን ነው? ማኅበረ ቅዱሳን ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ከሰጠችው ኃላፊነት አንዱ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ውስጥ መደበኛ ትምህርታቸውን በመማር ላይ የሚገኙ ኦርቶዶክሳውያን ወጣቶች የሚኖራቸውን የተጣበበ ጊዜ እና የአኗኗር ዘይቤያቸውን ያገናዘበ ልዩ መርሐ ግብር በማዘጋጀት መንፈሳዊ ትምህርት እንዲያገኙና በኋላ በሥራ ዓለም ሲሰማሩ በሃይማኖት ጸንተው፣ በምግባር ታንጸው በመገኘት በእውቀታቸው፣ በጉልበታቸውና በገንዘባቸው ቤተ ክርስቲያናቸውን እንዲያገለግሉ ማድረግ ነው። ይህንን […]
ቤተ ክርስቲያንን ጠብቋት
ኦክተውበር 17, 2012 in ክርስቲያናዊ ሕይወት /by Website Teamጥቅምት 6 ቀን 2005 ዓ.ም. አባ ዘሚካኤል ቅድሚያ ለቤተ ክርስቲያን እንቁም! ምን እንደምትልም እንጠብቃት (እንስማት)! “ወይእዜኒ ዕቀቡ ርእሰክሙ ዘሎቱ ሤመክሙ መንፈስ ቅዱስ ጳጳሳተ ከመ ትርአዩ ቤተ ክርስቲያኑ ለክርስቶስ እንተ አጥረያ በደሙ፤ በገዛ ደሙ የዋጃትን የእግዚአብሔርን ቤተ ክርስቲያን ትጠብቋት ዘንድ መንፈስ ቅዱስ እናንተን ጳጳሳት አድርጎ ለሾመባት ለመንጋው ሁሉና ለራሳችሁ ተጠንቀቁ” (የሐዋ.20፥28)፡፡ ፓትርያርክ ለመሾም:- ሁሉም ድርሻው እስከምን […]
የዚህን ዓለም ጣዕም ናቁ
ኦክተውበር 13, 2012 in ክርስቲያናዊ ሕይወት /by Website Teamበዲን. ብርሃኑ ታደሰ ጥቅምት 03 ቀን 2005 ዓ.ም. በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ’ዓለም’ የሚለውን ቃል በተለያየ አገባብ እናገኘዋለን። ለምሳሌ፦ ፍጥረትን፥ ሰማይንና ምድርን የሚወክልበት ጊዜ አለ፦ “ዓለም ሳይፈጠር በፊት ቅዱሳንና ነውር የሌለን በፍቅር እንሆን ዘንድ በክርስቶስ መረጠን።”(ኤፌ 1፥4) “ምድርና ሞላዋ ለእግዚአብሔር ናት፥ ዓለምም በእርስዋም የሚኖሩ ሁሉ።” እንዲል። (መዝ 24፥1) በሌላም ስፍራ “ከዚህም በኋላ ዓለም አያየኝም፤ እናንተ ግን ታዩኛላችሁ፤” (ዮሐ 14፥19) […]
ማኅበረ ቅዱሳን የቴሌቪዠን መርሐ ግብር ሊጀምር ነው
ሴፕቴምበር 22, 2012 in ዜና /by Website Teamመስከረም 12 ቀን 2005 ዓ.ም. በዲ/ን ዮሴፍ ይኲኖ አምላክ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን፣ ማኅበረ ቅዱሳን ከጥቅምት 4 ቀን 2005 ዓ.ም ጀምሮ ዘወትር በየሳምንቱ እሑድ ጧት ከ3፡30 እስከ 4፡00 ሰዓት የሚቆይ መርሐ ግብር በኢትዮጵያ ብሮድ ካስቲንግ ሰርቪስ ቴሌቪዠን (EBS TV) ለመጀመር ሙሉ ዝግጅት ማጠናቀቁ ተገለጠ፡፡ በማኅበረ ቅዱሳን ኅትመትና ኤሌክትሮኒክስ ሚዲያ፥ የሬድዮና ቴሌቪዠን ፕሮግራም አስተባባሪ የሆኑት […]
ውጤታማ በመሆን ለውይይት ማመን
ሴፕቴምበር 20, 2012 in ክርስቲያናዊ ሕይወት /by Website Teamመስከረም 10 ቀን 2005 ዓ.ም. በዲ/ን ዶ/ር መርሻ አለኸኝ የአምስተኛው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ፓትርያርክ ሥርዓተ ቀብር ከተፈጸመ ቀናት ተቆጠሩ፡፡ ፓትርያርኩ ዐርፈው መንበረ ፕትርክናው ባዶ መኾኑ ከተረጋገጠበት ዕለት ጀምሮ መንበሩን ለመጠበቅና ለማሰጠበቅ ይበቃል ያለውን አካል የመሾም፤ የቤተ ክርስቲያኗን መንፈሳዊና ማኅበራዊ አገልግሎት የማስቀጠል ሓላፊነት የተጣለበት ቅዱስ ሲኖዶስ አምስት ዋና ዋና ተግባራትን ፈጽሟል፡፡ የመጀመሪያው ፓትርያርኩ ማረፋቸው እንደተሰማና […]
ያግኙን
ኢሜይል አድራሻ ፡
europe@eotcmk.org / eu.pr@eotcmk.org
ድረገጽ:
www.eu.eotcmk.org